ሰበር ዜና…..

ዋልያ ከናይጄሪያ ሊጫወት ነዉ፡፡በአንድ አመት ለ4ተኛ ጊዜ!!! ናይጄሪያ ጥሪ አቅርባለች፡፡ከቻን ዉድድር በፊት እንጋጠም ብላለች ዋልያን…ለቻን ዉድድር ይረዳን ዘንድ ለእናንተም ለኛም ይረዳናልና ወደ አቡጃ ኑና እንጫወት ብለዋል አረንጓዴ ንስሮች፡፡ደብዳቤዉ ለኢትዬጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደርስዋል፡፡አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉም ጥያቄዉ ቀርቦላቸዉ በጥሩነቱ እንደተቀበሉት ተነግርዋል፡፡ ሀሳቡ እንደዚህ ነዉ፡፡ቻን የሚጀመረዉ በጃንዋሪ 11 ነዉ፡፡የወዳጅነት ጨዋታዉ ቀን ደግሞ ከዲሴምበር 30 እስከ ጃንዋሪ 5 ድረስ ባሉት ቀናት ነዉ፡፡ምርጫዉ ለዋልያዉ ተትትዋል፡፡የጨዋታዉ ቦታ አቡጃ ነዉ፡፡የናይጄሪያ ፌዴሬሽን ዋልያዉ ናይጄሪያ ከገባ ጀምሮ ያለዉን ሙሉ ወጪ ይሸፍናል፡፡ለ30አባላት ለ2ቀናት ያህል በናይጄሪያ ቆይታቸዉ ወጪ ይሸፈንለታል፡፡ዋልያዉ ማሟላት ያለበት ከአዲስ አበባ አቡጃ ያለዉን ወጪ መሸፈን ነዉ፡፡ይህንን በነጻ የማይገኝ ወዳጅነት ጨዋታ ፌዴሬሽኑ የትራንስፖርት ብቻ ከፍሎ ለመጫወት ፍቃደኛ እንደሆነ ታማኙ ምንጭ ነግሮኛል፡፡ እናም ዋልያዉ ናይጄሪያን ከባለፈዉ አመት የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊገጥም ነዉ ማለት ነዉ፡፡ከሶስቱ በ3ቱም ፔናልቲ አግኝተዋል፡፡አሁንስ ያገኙ ይሆን??በአዲስ ህንፆ–ሲሳይ ባንጫ እና ጀማል ጣሠዉ ላይ አግብተዋል፡፡አሁንስ??ድምሩ ዉጤት 6ለ1 ያሣያል፡፡የዳኛ ችግር በሚል የተነሱት ነገሮች በአሁኑ የወዳጅነት ጨዋታ ስለሚቀሩ በርግጥ የዋልያዉ ደረጃ ከናይጄሪያ አኳያ ምንድነዉ የሚለዉን ለማየት ይጠቅማል፡፡ቱሳ ብቸኛዉ የናይጄሪያን መረብ የደፈረ ሰዉ ነዉ፡፡አሁንስ የሚለዉ ይጠበቃል፡፡ለማንኛዉም የኢትዮጵያ ዋናዉ ቡድን የናይጄሪያን ሀገር በቀል የቻን ቡድን ከ10 ቀናት በኋላ ይገጥማል የሚለዉ ሰበር ወሬ ነዉ!!!!

2 thoughts on “ሰበር ዜና…..

Leave a Reply

Your email address will not be published.