ለወሳኞቹ የማጣሪያ ጨዋታዎች ተጨዋቾች ተመርጠዋል፤ አዳዲስ ተጨዋቾች ተካተዋል

ethiopia-in-bamako-648x430

Photo credit: soka25east.com

Photo credit: soka25east.com

የት እንደሚዘጋጅ ባልታወቀው የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታዎቹን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያደረጋቸውን ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በምድብ ተፎካካሪዎቹ ሶስት ቡድኖች መሸነፉን ተከትሎ ከፉክክሩ ውጪ እንደሆነ ቢታሰብም በመጨረሻው ጨዋታ ወደ ባማኮ ተጉዞ በአስር ተጨዋቾች ፍፁም ያልተጠበቀ ድል ይዞ መምጣቱ አነስተኛም ቢሆን የማለፍ ተስፋ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ በሳምንታት ውስጥም የማሸነፍ ግዴታን ተሸክሞ በአልጄርስ ከአልጄሪያ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከማላዊ ጋር ወሣኝ የመጨረሻ ጨዋታዎቹን ያደርጋል፡፡ አሰልጣን ማሪያኖ ባሬቶም ለነዚህ ጨዋታዎች ከወዲሁ ተጨዋቾችን መርጠዋል፡፡ ባሬቶ በዋሊያዎቹ የአሰልጣኝነት ቆይታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የመረጧቸውን የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ፋሲካ አስፋው እና የሲዳማ ቡናው ተከላካይ አብዱልከሪም መሀመድን ጨምሮ ባጠቃላይ 29 ተጨዋቾችን (4 ግብ ጠባቂዎች፣ 9 ተከላካዮች፣ 9 አማካዮች እና 7 አጥቂዎች) በዚህ ምርጫቸው አካተዋል፡፡ ጨዋታዎቹ ሲቃረቡ የሚቀነሱ ተጨዋቾች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ምርጫ የተካተቱት ተጨዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ግብ ጠባቂዎች፡- ሲሳይ ባንጫ፣ ታሪክ ጌትነት፣ ጀማል ጣሰው እና አሰግድ አክሊሉ

ተከላካዮች፡- አበባው ቡታቆ፣ ብርሃኑ ቦጋለ፣ ቢያድግልኝ ኤሊያስ፣ ቶክ ጄምስ፣ አብዱልከሪም መሀመድ፣ ግርማ በቀለ፣ ዴቪድ በሻህ፣ ሰልሃዲን ባርጊቾ እና ዋሊድ አታ
አማካዮች፡- ምንተስኖት አዳነ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ታደለ መንገሻ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ፋሲካ አስፋው፣ ኤሊያስ ማሞ እና ሄኖክ ካሳሁን

አጥቂዎች፡- ኡመድ ኡኩሪ፣ ሳልሀዲን ሰኢድ፣ ዩሱፍ ሳላህ፣ ዳዋ ሆቴሳ፣ ኤፍሬም አሻሞ፣ አሚን አስካር እና ዳዊት ፍቃዱ

  • የቡድኑ ወሳኝ አጥቂ ጌታነህ ከበደ በባማኮ ማሊን በረታንበት ጨዋታ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ የሚታወስ ሲሆን ማዳጋስካራዊው አርቢትር ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት የካፍ ዲሲፕሊን ቦርድ ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎችን ቀጥቶታል፡፡ በዚህ የተነሳ በሁለቱም ወሳኝ ጨዋታዎች አይኖርም ማለት ነው፡፡ መልካሙ ዜና ግን ሌላኛው የቡድኑ ወሳኝ አጥቂ እና አምበል ሳልሀዲን ሰኢድ ከሁለቱ የማሊ ጨዋታዎች ውጪ አድርጎት ከነበረው ጉዳት አገግሞ በመጪዎቹ ጨዋታዎች ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑ ነው፡፡
  • ሌሎቹ የቡድኑ ቋሚ ተሰላፊዎች ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው፣ ተከላካዩ ዋሊድ አታ እና አጥቂው ኡመድ ኡኩሪ በማሊው ጨዋታ የማስጠንቀቂያ ካርዶችን የተመለከቱ ሲሆን በአልጄርስ ጥንቃቄ ካላደረጉ በአዲስ አበባ ማላዊን ከምናስተናግድበት ጨዋታ ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
  • ከላይ የተዘረዘሩት በባሬቶ የተመረጡት ተጨዋቾች በእኛ ጥቅምት 22 ወይም በፈረንጆቹ ኖቬምበር 1 ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩም ተገልፅዋል፡፡

8 thoughts on “ለወሳኞቹ የማጣሪያ ጨዋታዎች ተጨዋቾች ተመርጠዋል፤ አዳዲስ ተጨዋቾች ተካተዋል

  1. Tikikilegna berregna lemagignet melelo,melelo legs yehonu wetatochin fellugo and hayawun 20 wun maseltigna lehulet sosit amet masgebbat bichal, hulet 2 Degea,Cischizeney,Courtiousen magignet yichalal.Yitasebibet,yitasebibet.

Leave a Reply

Your email address will not be published.