ለአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ የመጨረሻዉ ልምምድ?????ዳኜ ወደ ዳሸን????

pics of ethiopia 026

የሱማሌ ጨዋታ የአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ በዋና አሰልጣኝነት የጀመሩበት ጨዋታ ነበር፡፡ከዛ በፊት ግን በቶም ሴንት ፊት ምክትልነት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎችን አድርገዋል፡፡

ዛሬ ሰዉነት በልምምድ ሜዳ ላይ ለ2 አመት ከ6ወር የቖየዉ የአሰልጣኝነት ዘመናቸዉ የሚያበቃ ሊሆን ይችላል የሚስብል ነዉ፡፡ከዉስጥ አዋቂ ምንጭ እንዳገኘሁት መረጃ ሰዉነት ሊለቁ ወስነዋል፡፡እዚህ ደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ደጋፊዎች እና አዲስ አበባ ደዉለዉ ከሰምዋቸዉ ነገሮች በመነሳት አሁን የዋያልያዉ ጉዞ ማብቂያ ላይ ደርሰዋል፡፡

በዚህ ስሌት ዛሬ የሰሩት ልምምድ የመጨረሻዉ ነዉ፡፡እንደተለመደዉ ነበር ትሬኒንጉ፡-የእርስ በርስ ጨዋታዉ በግማሽ ሜዳ ተደርግዋል፡፡ማን ቤስት ላይ ማን ቤንች ላይ አንደሚሆን ፍንጭም ማግኘት ይከብዳል፡፡ምከንያቱም ተቀላቅለዉ ነዉ የሚሰሩት..አንዳንዶቹ በጨዋታ ቀን በሚገቡበት ቦታ ልምምድ ላይ አይጫወቱም፡፡ሳላሀዲን ባርጌቼ ከኮንጎ ጨዋታ በፊት በመሀል ተጫዋችነት ልምምድ ላይ ሰርትዋል፡፡የኮንጎ ቀን ግን በተከላካይነት አገልግልዋል፡፡እናም ልምምዱ የጨዋታ ማሳያ መሆኑ የቀረ ይመስላል፡፡

ጀማል ካጋጠመዉ የጡንቻ ጉዳት አገግሞ ትላንት እና ዛሬ ልምምድ ሰርትዋል፡፡እናም ነገ እሱ ይገባል ተብሎ ነዉ የሚጠበቀዉ፡-ተከላካዮች ሳላሀዲን ባርጌቾ-ቢያድግልኝ ኤልያስ-አበባዉ–አሉላ

መሀል ላይ አስራትን ማን እንደሚተካዉ አልታወቀም፡-ምንተስኖት አዳነ በአስራት ቦታ ሊገባ እንደሚችል ግምት አለ፡-አዳነ-ምንያህል ቱሳ እና ፋሲካ፡-ከዳዊት ኡመድ በአጥቂነት አንዱን  አልያም ማናዬ ፋንቱን ሊያሰልፉ ይቸላሉ፡፡እንደአፍሪካ ዋንጫዉ ካሰቡ ደግሞ ላልተጫወቱት አድል የሚሰጡ ከሆነ መሀል ላይ ታደለ መንገሻ ምንተስኖት አዳነን አልያም ሳላሀዲን ባርጌቾን አድርገዉ ቶክ ጀምስን በሊብሮነት ሊያሰልፉ የሚችሉበትም እድል አለ፡፡ሰዉነት መግለጫ አልሰጥም ስላሉ ስለቅያሪና ተመሳሳይ ነገር ማወቅ ከባድ ሁንዋል፡፡ምናልባት ዛሬ ከሰአት በስታድየም ለካፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ስለሚሰጡ እሱ ላይ የሚተነፍሱት ነገር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡

በነገራችን ላይ አሰልጣኝ ሰዉነት ከአሰልጣኘነትም እራሳቸዉን እንደሚያገሉ የዉስጥ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ምክትላቸዉ ዳኜ ከኒያላ ክለብ ጀምሮ በጋራ ሰርተዋል፡፡አሁን በቀጣይነት ዋልያዉን ትቶ ወደ ዳሸን ሊያመራ ይችላል፡፡ምክንያቱም ሰዉነት የዳሸን አማካሪ እና አምባሳደር ሁነዉ ስለሚያገለግሉ ነዉ፡፡እናም ሰዉነት ወደ ንግድ አለም ሊገቡ እንደሚችሉ ፍንጮችም አሉ፡፡ለማንኛዉም የዛሬ ልምምድ እና የነገ የጋና ጨዋታ ለዋልያዉና ለአነጋጋሪዉ አሰልጣኝ የመጨረሻ እንደሚሆን ይጠበቃል!!!!

12 thoughts on “ለአሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ የመጨረሻዉ ልምምድ?????ዳኜ ወደ ዳሸን????

  1. you know what i think sewnet bishaw is a very lucky person in the Africa cup of nations he had a training time more than a month and also the players know each other because they played almost in one team like saint George so in every game they play we have seen no technical skills from the couch i know the players can fit any team but the couch haven’t showed them the right way and also he didn’t teach them ethics all in all he blew his big chance of bringing a big result this team deserve more than this don’t try to compare it to the past we have much better squad than the past so i prefer not to see sewnet and his worse interviews again

  2. Sewenate B.is a nice, cleaver ,……primary coach in Ethiopia.so, wish you long live in all remain time .

  3. Denkoro neh…ke amaregna astemarinet wede sport reporter zelh gebteh atzebarek…. I hate you seeid kiar.

  4. ersu le ageru yerasun tiret adrigual.bizu lewtochinena menekakaten yameta sew new.Eskahun leseraw limesegen yegebawal .sew degmo hulgizie wutetama hono lizelik aychilem .somewhere he faces a setback.so it is natura.Friends let’s ask ourselves”What did we contribute to our country-our beloved mother?” yehin kalmelesk facebook lay yekura chuhet new eyechoh yalehew!! Sewunet is a hero .Enwodhalen!!

  5. yemigermew egna ethiopian le ethiopian kibr keminsetna tiru yeserutn keminadenk yilk diablosn kidus new binl yikelenal. who was born perfect?????????????????? realy Ato sewnet,he plays a great role and contribute his own that z country Ethiopia needs from him:please we,the rest of him try to contribute a little other than discourage such a good man. Ato sewnet wish u all z bests zat u want to have.

  6. If he leaves we owe him a big thank you from all of us. He gave his best, as a result he achieves a lot and he fails in some. After all who is born perfect in this world? We Ethiopians don’t know thank you.

  7. Eadlune rasacheaowne beger kuwase hiwote lasalfu wetate aseltgnoche biste melkame yimeslgnale wubetu abate kalhonem le zelalem shifraowe

Leave a Reply

Your email address will not be published.