Connect with us

Sports

የኢትዮጲያ እግር ኳስ: በስሜትና በእዉነት መካከል!

Published

on

national team 11

“ከታሪክ መማር የማይፈልግ ሰዉ ታሪካዊ ስህተትን ለመድገም የተረገመ ነዉ”

በሰኢድ ኪያር

እንደመግቢያ

አሁን ሰማይ የተሰቀሉ ስሜቶች ቀዝቅዘዋል፤በጭፍን ዋልያዉን ከማሞገስና ከመስቀል በእዉነታዎች ላይ መወያየት ተጀምርዋል፤በመጀመሪያዉ ጎን ደግሞ ናይጄሪያን በመልስ ጨዋታ ስለማሸነፍ መዘመሩን ቀጥልዋል፤ይህ ሚድያዉን ያጠቃለለ ፉከራ ከጥቅምት 3ቱ በጥቂት ግን ወሳኝ ነገር ለየት ይላል፤ቢያንስ ቢያንስ ”እንዴት???” የሚለዉን ቀም ነገር ማካተት ጀምረዋል፤ይህ ጽሁፍም ያልተስተዋለዉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስሜት ዝብርቅርቅ ይዳስሳል..ከእዉነት ይልቅ ስሜትን ስለተከተሉት ወቅቶች………

የዛን ቀን ደስታ ልዩ ነበር፤ከዳሪሰላም ታንዛኒያ ሲቃ የተሞላባቸዉ ድምጾች የኢትዮጲያን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አበሰሩ፤ለእግር ኳሱ ትንሳኤ ቀን እንደሆነም በመነገሩ አዲስ አበባ እና መላ ኢትዮጲያም ተነቃንቀዋል፤በለንደን ኦሎምፒክ ወንዶቹ ሲያቅታቸዉ እንስቶቹ ግን የተለመደዉን ወርቅ አምጥተዉ ህዝቡን አኩርተዋል፤እናም በእግር ኳሱ የዉጤት ማማ ሴቶች ነገሱበት፤”የሴቶች እግር ኳሱ መነቀቃት”ም በይፋ ተነገረ!!በየመንገዱ ሉሲ– በየራድዮ ጣቢያዉ- ጋዜጦች እና የቲቪ መስኮቶች የሉሲ ገድል ዝማሬ ጣሪያዉን ነካ፤ሉሲዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸዉ ይበል የሚያሰኝ ነገር ነዉ፤እንዴት አለፉ የሚለዉ ግን በሞራልና በጮቤ ረገጣዉ መሀል ተሸሽገዉ ቦታ አላገኙም፤ሁሉም ቀርቶ ሉሲዎቹ ከዚህ በፊት ለአፍሪካ ዋንጫ ባለፉባቸዉ ዉድድሮች እንኩዋን ምን ገጠማቸዉ የሚለዉን ማየት አልተቻለም፤አላማችን ለአለም ዋንጫ ማለፍ ነዉ—ስሜት የነገሰበት የሁሉም የርእይ ስንቅ ነበር፤ ዉድድሩ ሲጀመር ግን ይህ ሁላ የስሜት ሰቀላ ዉሀ ተቸለሰበት፤ከመጀመሪያዉ ደቂቃ አንስቶ ኮትዲቫሮች ግብ ማምረት ጀመሩ፤5-0 ጨዋታዉ አለቀ፤እዚህ ላይ ቡድኑ ልምድ የለዉም እንዳይባል 3ተኛ የአፍሪካ ዋንጫቸዉን የሚጫወቱ–ለ2ተኛ ጊዜ ሉሲን በአህጉሪቱ መድረክ የሚወክሉ…በተለያዩ ማጣሪያዎች ልምድ ያላቸዉ ተጫዋቾች የተሰባሰቡበት ቡድን ነዉ፤ግን አልቻለም፤ያቃተዉ ደግሞ የኮትዲቫሮችን ማጥቃት ማቆም ብቻ አይደለም መሀል ሜዳዉን አልፎ መሄድ የዳገት ያህል ለሉሲዎቹ ከበደ፤ናይጄሪያ ቀጣዩን ጨዋታ 3-0 ረታች፤ከካሜሩን ጋር 0-0 የሉሲዎቹ መጨረሻ ከ8ቱ ቡድኖች 8ተኛ ..ብዙ ግቦች ያስተናገዱ ግን አስደንጋጭ ሙከራ እንኳን ያላደረጉ ሁነዉ ተሸኙ፤ከምንም በላይ ‘’ተነቃቃ’’ የተባለዉ እግር ኳስ አሸለበ፤የያኔዉ አይነት ጎሮ ሸባዮ አሁን በሉሲዎቹ አከባቢ የለም፤አርቴፊሻሉ መነቃቃት በክለቦች የዋንጫ ጨዋታ እንኳን አይኖችን መግዛት አልቻለም፤”ብዙ ትምህርት አግኝተንበታል “–የተለመደዉ ሽንፈት ሰራሽ መልስ ተከተለ፤ ይህ ከሆነ 1 ድፍን አመት ሁኖታል፤ስለ ሉሲ ያኔ የተዘመረዉን ያህል አሁን ስለ ሉሲ የሚያወራም የለም፤እንደእምቧይ ካብ በሚናዱ የስሜት ዝብርቅርቆች መሀል ከተገኙት የኢትዮ ቡድኖች አንዱ ሆኑ ..ሉሲዎች ዋልያ…. ከኢትዮጲያና ሱዳን ጨዋታ በፊት–ግዮን ሆቴል –“የኢትዮጲያ እግር ኳስ እንዴት ከወደቀበት እናንሳ?’’ በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ፤ፌዴሬሽኑ ነዉ የጥናት ባለቤቱ..እናም ከትምህርት ተቋማት የተዉጣጡ ዶክተሮችም ሳይቀሩ ተሳትፈዉበታል፤ማጠቃለያዉ –የኢትዮጲያ ኳስ እንዲያድግ መሰራት የሚገባቸዉ ነገሮች ተብለዉ…. –አደረጃጀትን ዘመናዊ ማድረግ —-ፕሮጀክት በስፋት እንዲኖሩ –ወጥ ስልጠና ማንዋል ማዘጋጀት —አካል ብቃት ላይ በሚገባ መስራት..ወዘተ…. በሚል ጥናቱ አስቀመጠ፤ለዚህም ተሰብሳቢዉ ማረጋገጫ ቃሉን ሰጥቶ ተለያየ፤ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት ቢያንስ ቢያንስ አመታት ይፈጃሉ፤አጥኚዎቹም ሆኑ ተሳታፊዎቹ ይህንን ነገር አላምጠዉ ሣይጨርሱ ዋልያዉ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ፤እዚህ ላይ ሁነኛ መነጋገሪያዎች መነሳት ይገባቸዉ ነበር፤ወይ ጥናቱ ፉርሽ ነዉ!! አልያም ጥናቱ ትክከል ሆኖ ቡድኑ በአጋጣሚ አለፈ፤ካልሆነም ደግሞ ጥናቱ እንደችግር ያስቀመጣቸዉ ሀሳቦች እንዳሉ ሆነዉ ጠንካራ ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ቡድን ሊሰራ ይችላል….!!.ስሜት መር የሆነዉ እግር ኳሱ ግን ጆሮ ዳባ ብሎ ጉዞዉን ቀጠለ! ቤኒን ጋር አቻ..ሱዳንም ጋር አቻ ወጥቶ ዋልያዉ ደቡብ አፍሪካ ደረሰ፤ይህ በርግጥም ከታሪክ አንጻር ትልቅ አጋጣሚ ነዉ፤ግን ከስሜት ምህዋር ያልወጣ ያለጊዜዉ የደረሰ አልያም የማይደገም ስለመሆኑ ማሳያዉ በዉድድሩ ላይ የታየዉ ቡድን ነበር፤”ዋንጫ እንደርሳለን—ባይሆን እንኳን 4ቱ ዉስጥ ከገባን በቂያችን ነዉ!!”የሚል እቅድም ተነድፎ ነበር፤ ከዛምቢያ ጋር አቻ የወጣዉ ቡድን ሜዳ ላይ ባሉ መነጻጸሪያዎች ሁሉ(ካርድንም ሳይጨምር) ተበልጥዋል፤በስሜት በሚነጉደዉ እይታ ግን ይህ ቡድን የአፍሪካ ባርሴሎና ተባለ፤ቀጠለና በቡርኪና ፋሶ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ እናም 4ት ግቦች አስተናገደ፤በስሜት የተወጠሩት ልቦች አሁን ተንፈስ አሉ፤ናይጄሪያም ብልጫዉን ወስዶ 2-0 አሸነፈ፤ከተሳታፊ ቡድኖች በአነስተኛ ነጥብ በአነስተኛ ሙከራ እናም በብዙ ግቦች በማስተናገድ ግምባር ቀደም ሁኖም ተመለሰ፤”እንደጀማሪ የነጻ ትግል ተፋላሚ”!!! ይህ ነገር በዚህ ትዉልድ ብቻ የተከሰተ አይደለም፤እግር ኳሱ— ከዚህ በፊት የነበሩት ቡድኖች አንዴ ብልጭ ካዛም ድርግም በሚሉ ዉጤቶች ተጭበርብሮ በግድ የኢትዮጲያን እግር ኳስ ትንሳኤ መስክሯል፤

አዘናጊዎቹ ድሎች

3ተኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጲያ ትልቁ ታሪክ ነዉ፤ሉቻኖ ቫሳሎ ከንጉሱ እጅ ታሪካዊዉን የአፍሪካ ዋንጫ ከተቀበለ ወዲህ ማንም ኢትዮጲያዊ ያንን መድገም አልቻለም፤ይሔ ድል ለያኔዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን” ኳስ ድሮ ቀረ” ለሚለዉ መካካለኛዉ የእግር ኳስ ዘመን ሰዎችም እንደማሳያ ይቆጠራል፤የያኔዉ ድል እንዴት ተገኘ?የሚለዉን ዋነኛ ነገር ያልመረመረዉ ትዉልድ ለተከታታይ ዉድቀቶቹ ምክንያት እስኪያጣ ድረስ ግራ ተጋብትዋል፤አስኪ ዋንጫ የበላ ቡድን እንዲህ አይነት የሽንፈት ጉዞ ሲከተለዉ ምን ይባላል፤—ዉጤት ያመጣበትን ምክንያት አለማወቁ ከማለት ዉጭ!!!ተከታዩ ዉጤት ታሪካዊዉ ድል አድራጊ የኢትዮጲያ ቡድን የአፍሪካን ዋንጫ ካነሳ በሁዋላ ባሉት አመታት ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች ናቸዉ!! ከ4ተኛዉ እስከ 13ተኛዉ የሊቢያ አፍሪካ ዋንጫ 6ት ዉድድሮችን ተካፍሎ..ካደረጋቸዉ 19 ጨዋታዎች 14ቱን በሽንፈት 1ዱን አቻ 4ቱን በማሸነፍ አጠናቅዋል፤41 ግቦች አስተናግዶዋል 20 ብቻ አስቖጠወርዋል..21 እዳ ማለት ነዉ ሲወራረድ፤ያስከበረዉ የበላይነት አልያም ያስጠበቀዉ ክብርም አልነበረም፤ጭራሽኑ ከ13ተኛዉ በሁዋላ 31 አመታት እልም ብሎ ጠፍትዋል፤መነቃቃትን ፈጥሮ የነበረዉ ቡድን የተከተለዉ ታሪክ እንግዲህ ይህ ነዉ!!!! ነገርየዉ ይቀጥላል፤የሲካፋ ዋንጫ በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ ኢትዮጵያ ዋንጫ አነሳች..ጎሮ ወሸባዉ ቀልጦ በቀጣይ ሽንፈቶች ደግሞ እንደበረዶ መቅለጥ ተከትለዋል፤የክለቦችም ወግ ቢሆን ከዚህ እላፊ አልሄደም፤

አለም ዋንጫ…

“ አርጀንቲና አትሄዱም”….. “አርጀንቲና አትሄዱም”…. የሚሉ የተስፋ መቁረጥ ድምጾች በአዲስ አበባ ስታድየም የተሰሙት በጋርዚያቶ ተመርቶ ለአለም ዋንጫ ባለፈዉ የወጣት ቡድን ላይ ነበር፤በህዝብ እና በካፍ ቀና እርዳታ ወደ አለም ዋንጫዉ ማለፉን ያረጋገጠዉ ወጣት ቡድን በጥሎ ማለፋ በአንጎላ 5-2 በደረጃ ጨዋታ በግብጽ 2-0 በጨዋታ ብልጫ ጭምር ሲሸነፍ ህዝቡ ወደ አለም ዋንጫ የማለፍ ትርጉም አልባ መሆኑን በማሰብ ነዉ.አርጀንቲና አትሄዱም ያለዉ!! አሁን ከ13 አመታት በሁዋላ የያኔዉን ለአለም ዋንጫ ያለፈ ቡድን ስናየዉ በርግጥም ተመልካቹ ትክክል እንደነበር ማረጋገጥ እንችላለን፤ቡድኑ እንደምንም ማጣሪያዉን አልፎ(ከ5ጨዋታ 1ዱን በልዩ ህግ አሸንፎ) በአለም ዋንጫዉ በታናናሾቹ 3ቱንም ጨዋታ ተሸንፎ ተመለሰ፤(ከ8 አንድ አሸንፎ ማለት ነዉ)!ወጣት የተባሉቱ በዋናዉ ቡድን ይህንን መድገም አልቻሉም፤ጭራሽም ለረጅም አመታት ለመጫወት የበቁት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸዉ፤ እዚህ ላይ ዋናዉ ነገር ተጫዋቾቹ ያገኙትን ድል ማንኳሰስ አይደለም፤ለሁሉም ኢትዮጲያን በአለም ዋንጫ ለወከሉ..ማጣሪያዉን ለተጫወቱ..ላሰለጠኑ ላገዙ—ለሁሉም ትልቅ ክብርና ምስጋና ሊቸር ይገባል፤ዋናዉ ቁም ነገር ግን የያኔዉ ድክመት ለዛሬዉ ማስተማሪያ ስለሚሆን ዋነኛ ድክቶቹን ነቅሶ ማዉጣት ነዉ፤እናም ኢትዮጲያ ዛሬ ላይ ሁና የዛሬ 13 አመት ለአለም ዋንጫ ያለፈዉ ቡድንዋ ምን እንደጠቀማት መናገር አለመቻልዋ ነዉ! አለም ዋንጫን ማለፍ ሁነኛ ጥቅም ከሌለዉ የወራት ሆይ ሆይ ሆይታ እናም ቀጥሎ ሀዘን የሚያስከትል ከሆነ ዋጋ ቢስነቱ ያይላል!!በተደጋጋሚ የመሳተፍ የሚያስችል ቁመና ያለዉ ጠንካራ ቡድን ከሆነ በሴካፋ ዉድድርም ቢሆን ጥንካሬዉ ሲገነባ ለነገ ተስፋ ይሠጣል፤

የአሁኑ ዋልያ…

የላይኛዎቹ መነሻዎች አሁን ካለዉ ቡድን ጋር ለማያያዝ ጠቃሚ ይሆናሉ፤የዋልያዉ የአፍሪካ ዋንጫ ሂደት ሲገመገም ከማለፍ በስተቀር በዉድድሩ ላይ ያሳየዉ ነገር ጠንካራ እንዳልሆነ ምስክር አያስፈልገዉም፤ከዛ በሁዋላ ባደረጋቸዉ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችም ቦትስዋናን እና ሴንትራል አፍሪካን በደርሶ መልስ ደቡብ አፍሪካን አዲስ አበባ ላይ ማሸነፍ ቢችልም ጨዋታዎቹ ለቡድኑ ጥንካሬ ምስክር መሆን አልቻሉም፤አዲስ አበባም ላይ ሆኑ ዉጭ የተደረጉቱ ጨዋታዎች አስጨናቂ ነበሩ፤የጨዋታዎቹ ፍጻሜ ፊሽካ እስኪነፋ ድረስ ደረትን ነፍቶ የቡድኑ ጠንካራ ነገር ይህ ነዉ ለማለት አዳጋች ነበር፤የተጋጣሚዎች መቅለል–ማለትም እንደከዚህ ቀደሞቹ ቡድኖች አይነት የነ ግብጽ-ካሜሮን–ቱኒዚያ አይነት ጠንካራ ቡድኖች ጋር አለመጫወቱ–እንዲሁም በዉጤት ደረጃ ጥሩ ባይሆንም በማሸነፍ እድለኛነት እዚህ ደርስዋል ቀደም ብለን እንዳየናቸዉ ቡድኖች አንዴ ታይቶ ብን ብሎ የሚጠፋ ክስተት እንዳይሆን አሁን ላይ ያሉትን ህጸጾች ነቅሶ ማዉጣት ግድ ይላል፤ዋልያዉ የዛሬ 2ት አመት ከተሳተፈበት ሴካፋ ጀምሮ ተጋጣሚን እንዴት እንደሚቀርብ ለማወቅ ከባድ ነዉ፤በአብዛኛዉ ከአሰልጣኞቹ እንደሚሰማዉም..ተጋጣሚ ከተከላከለ የሚያጠቃ— ካጠቃ ደግሞ የሚከላከል ስለመሆኑ ነዉ፤ይህ ነገር ማሸነፍን እንዴት እንደሚመጣ አልያም ሽንፈት በምን ምክንያት እንደመጣ የሚያስተምር አይደለም፤ቄሱም መጽሀፉም ዝም ብሎ ከመቀጠል ዉጭ! የአሁኑ ዋልያ አጨዋወት ግምት ላይ የተመሰረተ ረጅም ኳሶችን አዘዉታሪ መሆኑ በጨዋታዎች ላይ ተመልክተናል፤ይህ ደግሞ አሁን አለም እየተቀየረበት ካለዉ አጨዋወት በሚልየን ምይሎች ርቀት ላይ ያስቀምጠዋል፤ተከላካዮች ኳስን ተጫዉቶ ከመዉጣት ይልቅ በረጅሙ ጠልዞ እንደገና የመጠቂያ ምንጭ እንደሆኑ በተደጋጋሚ አይተናል፤አማካዩ ክፍል ለፈጠራ ዝግ ነዉ፤አለም ትቶት የወጣዉን በተከላካይ አማካዮችን አብዝቶ ያለጨዋታ አቀጣጣይ አነስተኛ ፈጠራ ያላቸዉን ተጫዋቾች መጠቀም የአሁኑን ዋልያ መሀል ሜዳ እጅጉን ደካማ ያደርገዋል፤3ት ቅብብል ለማድረግ የሚቸገር አማካይ ክፍል በንጽጽር ጥሩ ለሚባሉት አጥቂዎች የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ኢምንት ነዉ፤በዚህ ቦታ በተደጋጋሚ የአሰልጣኞች ምርጫ ያልነበረዉ ሽመልስ በቀለ ለብቻዉ ኢትዮጲያ ምን አይነት ተጫዋቾች እንደሚያስፈልጋት የሚያሳይ ሁኑዋል፤ እነዚህና እና መሰረታዊ የሚባሉ የቡድን ዉህደት ችግር ያለበት ዋልያ ከምንም በላይ አቆለጳጵሶ፤ከአቅሙ በላይ አወድሶ፤የህዝብን ስሜት አንሮ በስተመጨረሻ አሸማቃቂ አይነት ብልጫ ሲመጣ ምክንያት መደርደር ብልህነት አይሆንም፤ብዙዎች ዋልያዉ ነገ ከሚያደርገዉ ጨዋታ በፊት የወዳጅነት ጨዋታ አለማድረጉ እንደሚጎዳዉ ይናገራሉ፤ነገር ግን ዋልያዉ እስካሁን ካሸነፈባቸዉ ጨዋታዎች ምንም አይነት ድክመት ለማሻሻል ሳይችል ሌላ ጨዋታ ማድረግ ትርጉም አልባነቱ ይጎላል፤ አርቆ ማሰብ በዋልያዉ አከባቢ መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ነዉ፤ናይጄሪያን ማሸነፍ ይቻላል፤አለም ላይ ያለን ጠንካራ ቡድንንም እንዲሁ…ነገር ግን ምንም ጥንካሬ ሳይኖር ትልቁን ሆነ ትንሹን ቡድን ማሸነፍ ዋጋቢስ ነዉ፤ከዚህ በፊት የነበሩት ድንገቴ ቡድኖች እንዳመጡት የሚረሳ ዉጤት ከመመስከር በስተቀር!!

ናይጄሪያ…የኋላን ማስተዋል….

ስለ ናይጄሪያ ጨዋታ ሲነሳ ሰዎች የኋላን ማየት አስፈላጊ አለመሆኑን ሲናገሩ ነበር፤ምክንያቱም ናይጄሪያ ምን ያህል በሽንፈት እንዳቆሰለን ስለሚታወቅ…ነገሩ ግን ህልም ተፈርቶ….እንደሚባለዉ ነዉ፤ናይጄሪያ በልጦ እስከዛሬ አሸንፎናል፤ይህ ሀቅ ነዉ..ዛሬም ቢወራ ከታሪክነት ባለፈ ለምን እንደበለጠን መማሪያ ይሆናል፤ትላንት የበለጠበትን መንገድ የያኔ ተጫዋቾች (አሁን በአሰልጣኝነት እና ዙሪያዉ ያሉ) በሚገባ አስረድተዉ አሁን ዋልያዉ እንዴት መብለጥና ማሸነፍ እንዳለብን ማስረዳት ይችላሉ፤አለበለዚያ ግን የኋላን ትቶ አልያም ማንሳቱን ፈርቶ የአሁኑን ብቻ ማሰብ ጎዶሎነት ይሆናል፤ጸሀፊዉ ዳንኤል ክብረት እንዳስቀመጠዉ…. ’’ከታሪክ መማር የማይፈልግ ሰዉ ታሪካዊ ስህተትን ለመድገም የተረገመ ነዉ፤እንዲህ የሚያደርግ ግን እንስሳ ብቻ ነዉ፤እንስሳት ታሪክ የላቸዉም፤ታሪክ ስለሌላቸዉ የዛሬ 1ሺ አመት አንድ በሬ የሰራዉን ስህተት የዛሬዉ በሬ ይደግመዋል፤የዛሬ 3 አመት አንድ በግ የሰራዉን ስህተት ዛሬም ያዉ በግ ሊሰራዉ ይችላል፤የዛሬ 600 አመት ምድርን ስትጭር የነበረችዉ ዶሮ ዛሬም እንደምትጭረዉ ማለት ነዉ፤ዶሮዋ ለመጫር ነዉ እንጂ ለመብረር ልታስብ አትችልም፤ሰዉ ግን ከዚህ ዉጭ ነዉ፤ሰዉ ከትላንት ይማራል..ስህተቱን ያርማል……ስለዚህ የሰዉ ልጅ የትላንቱን ጥሩ ይዞ እንዲቀጥልና መጥፎዉን እንዲያርም የጎበጠዉን እንዲያቀና…ተብሎ የታሪክ ትምህርት የሚሰጠዉ..’’

ከስሜት ወደ እዉነት…

ኢትዮጲያ እንድታሸንፍ የማይፈልግ የለም፤አስተማማኝ ቡድን ቢኖራት ምን ግዜም የምትታወቅበት ጥንካሬ ብታሳይ የሁሉም ምኞት ነዉ፤ነገር ግን ነገ በማይደገም አካሄድ ቡድንዋ በዉጤት ሲደለል ዝም ማለትም ተገቢ አይሆንም፤ዉጤት ያመጡ ሰዎች ክብር ይገባቸዋል፤ሽልማትም ቢጎርፍላቸዉ አስፈላጊ እና የሚበረታታ ነዉ፤ነገር ግን ዉጤት ያመጡበትን መንገድ መመርመር ደግሞ እዉቅና ከመስጠት የተለየ እይታን ይጠይቃል፤ጥሩ ያልሆነን ቡድን እላይ ሰቅሎ ሲፈጠፈጥ ከመሳቀቅ ከመነሻዉ እያሸነፈም ቢሆን በድፍረት ስህተቱን መጠቆም አስፈላጊ ነዉ፤ የባለፈዉ ሳምንት ጨዋታንም በዚህ መነጽር መቃኘቱ ጠቃሚ ነዉ፤የመጀመሪያዉ ነገር ከጨዋታዉ በፊት ይነገሩ የነበሩ የሁለቱ በድኖች ልዩነቶች አሁንም እንዳሉ ተረጋግጥዋል፤ናይጄሪያ በኬሺ የተጫዋችነት ዘመን የመንግስቱ ወርቁን ቡድን በአካል ብቃት ጥንካሬ እንደበለጡት ዛሬም የሰዉነትን ቡደን ከ30 አመታት በሁዋላም በልጠዋል፤ይህን ነገር ከእኔ ከጻሀፊዉ..ከናንተ አንባቢዎቸ እና ከአሰልጣኞች በላይ ተጫዋቾቹ ያቁታል፤ሁሌም በተደጋጋሚ ይናገሩታል፤ለዚህም ይመስላል ያለወትሮዉ በግምት ይላኩ የነበሩ ኳሶች የቀነሱት…ተጫዋቾቹ ኳስዋን በሚችሉት መንገድ በመሬት በአጭር ቅብብል ለመብለጥ ጥረዋል፤ከሌላዉ ጊዜ በተለየም ከተከላካዮቹ ደፍሮ የሚቀበል አማካይ ብቅ ብልዋል፤እሱም አዳነ ግርማ ነዉ፤የዋልያዎቹን ልምምድ ላለፉት 2ት አመታት በቅርበት ስከታተል የኳስ ብልጫን ለመዉሰድ የሚያስቸል ልዩ ስልጠና አላየሁም፤እናም አዳነ እና ጓደኞቹ ያደርጉ የነበሩት እንቅስቃሴ በትሬኒንግ የተነደፈ ስላለመሆኑ የቅብብላቸዉ መጨረሻ ያሳብቃል፤ለ6ት በራሳቸዉ ሜዳ ይቀባበላሉ..ከዛም በግምት ኳሶች ይጣሉና አጥቂዎቹ አላስፈላጊ ድካም ዉስጥ ይገባሉ፤ያም ቢሆን ግን ናይጄሪያን በፈለገዉ መጠን እንዳይንቀሳቀስ አድርገዋል፤የዚህ ነገር መነሻ የሆነዉ ተጫዋች በጊዜ ከተቀየረ ደግሞ ከርሞም ይህ አይነቱ አጨዋወት ተፈላጊ አለመሆኑን ያሳያል፤አሰልጣኝ ሰዉነት ከጨዋተዉ በሁዋላ ከአንድ ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ..”አሁን ጊዜዉ የመጫወት ነዉ፤ተጫዉቶ ማሸነፍ ያስፈልጋል፤ይህንንም ለመተግበር ሞክረናል” የሚል አንደምታ ያለዉ አስተያየት ሰጥተዋል ፤የመጀመሪያዉ ነገር መጫወት ከተፈለገ..እናም በመጫወት ብልጫ መዉስድ እንደሚቻል ከተረጋገጠ መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾችን ለምን አልተካተቱም ?ይሆናል ጥያቄዉ…….ለማስረጃ ያህል መሀል ክፍሉን ለ90 ደቂቃ ተፈራርቀዉ ከተጫወቱት አስራት..አዳነ..አዲስ..እና ምንያህል ..ዉስጥ አንዳቸዉም በክለባቸዉ የጨዋታ አቀጣጣይነት ሚና ኑርዋቸዉ አያቅም፤አዳነ አጥቂ..አስራት እና አዲስ ቀሚ..ምንያህል የክንፍ ተጫዋቾች ናቸዉ፤እናም የመሀል ክፍል ብልጫ ያለመሀል ተጫዋች..ለዚያዉም የመፍጠር ብቃቱ ደካማ የሆነን ይዞ ማሰብ ከባድ ይሆናል፤ሀገሪቱ ደግሞ የአማካይ ተጫዋች ደሀ አይደለችም..ሌላዉን እንተወዉና የአዲስ አበባ ስታድየም መጫወቻ ሜዳ ሁሌም የመሀል ክፍሉ ሳር በቶሎ መበላት ለዚህ የማይናገር ምስክር ነዉ!!! ናይጄሪያ ጋር እንዴት መጫወት እንዳለብ እና እንዴት መጫወት እንደሌለብን በጨዋታዉ ታይትዋል፤የዚህ ቀን ችግር ግን የተጀመረዉ ዋልያዉ አሸናፊ ሆኖ ከማንም በላይ በተባለባቸዉ የቦትስዋና..ሴንትራል አፍሪካ..ደቡብ አፍሪካ ጨዋታዎችም ጭምርም ነበር፤በነዚህ ጨዋታዎች በየደቂቃዉ የሚጠልዝ..ኳስ ከእግሬ ዉጭልኝ በሚል መንፈስ የሚጫወት ቡድን ነበር፤ያም ቢሆን ግን ስላሸነፈ ከነስህተቱ ተንቆለጳጰሰ፤ድል ማድረግ እናም መመስገን በጣሙን ጥሩ ነገር ነዉ፤ነገር ግን ምንም ላይ ያልተመሰረተ ድል ነገ ምንም ላይ ሲጥል የናይጄሪያ አይነት ዱብ እዳ ያስከትላል፤

መፍትሄ…

ችግር የመፍትሄ ቁልፍ ነዉ፤እናም ኢትዮጵያ እግር ኳሴ አድግዋል ባለችበትም ሆነ በደከመችበት ጊዜ ያለመታከት የሚያሸነፍኑን የምእራብና ሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን ለመብለጥ ወደ እዉነታዉ መምጣት አለብን፤”እኔ ጢቅ ጢቅ ጨዋታ የሚጫወት አልፈልግም.የሚጋጭ የሚፋለጥ እንጂ” የሚል አስተሳብ ያለዉ አሰልጣኝ ናይጄሪያም ሲመጣ ተጋጥቶና ተፋልጦ አሸንፎ ማሳየት ይኖርበታል፤አልያም ደግሞ አስቀድሞ በኳስ መብለጥ አለብን የሚለዉን መያዥ ይኖርበታል፤እኔ ይህንን የምጽፈዉ ላለፈዉ ቡድን አይደለም፤ከዚህ በኋላ ለሚመጣዉ ነዉ፤እንኳን አሰልጣኙና ባለሙያዉ ቀርቶ ተመልካቹ እንኳን ለይቶ ኳስ የሚጫወቱ የዉጭ ቡድኖችን የነፍሱ ያህል በሚወድበት ሀገር ለጥለዛ ና አካል ግዝፈት የሚሰጠዉ ትኩረት መቅረት አለበት፤እከሌ ምን ያህል ኳሶችን አጨናገፈ ሳይሆና እከሌ ምን ያህል ኳሶችን አስተካክሎ ሠጠ መመዘኛ መሆን አለበት፤፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ክህሎት ያልዋቸዉ ተጫዋቾች ሀገር መሆንዋ ለክርክር ማቅረብ ጉንጭ ማልፋት ነዉ፤አለምም በዚህ በዉብ እግር ኳስ ቅኝት እየተመራ መሆኑ ለእግር ኳሱ ትልቅ እድል ነዉ፤አለም ተጫዉቶ ስለማሸነፍ እያዜመ ነዉ፤ጀርመን ከጉልበት ወደ ጥበብ መንገዱን ጠርግዋል፤ስፔን እግር ኳሱን በአጭር ቅብብል መደብ አናቱ ላይ ከወጣች ቆይታለች፤ዋልያዉስ???አፍሪካን ለመቆጣጠር ጊዜዉ አሁን ነዉ!!ከፍለጠዉ ቁረጠዉ አጨዋወት ወደ ጭንቅላት ጨዋታ መቀየር..ለዚህ ደሞ በቂ ተጫዋቾች በኢትዮጲያ ይገኛሉ፤እናም ለዋልያዉ ትንሳኤ በመልሱ የካላባር ጨዋታ ሆነ በቀጣየቹ ዉድድሮች ይህንን መሞከሩ በእዉር ድንብር ከመሄድ በእዉቀት አለምን መከተልን ያስገኝለታል!!!!

Continue Reading
4 Comments

4 Comments

 1. Anonymous

  January 23, 2014 at 2:33 am

  Interesting article, thank you Saied! It sinks in when you write a detailed article like this one, than generally blaming one individual for the whole problem. I guess everyone should pitch in his part for us to see changes in our national team! As you beautifully pointed out, we need to take a lesson from our failure!

 2. Anonymous

  January 22, 2014 at 5:09 pm

  Good job, Saied. I’m always proud of you. I could say a lot but talking about our problem requires me more time. You are amazing and I am with you! Please keep on.

 3. Anonymous

  January 22, 2014 at 4:41 pm

  I have no idea how you guys,”on the opposite side of Coach Sewnet ” are thinking.
  Before saying something about our football , I would like to say the negative attitude we developed in our culture knowingly or unknowingly. When we like someone/something,we give 100%; on the contrary when we dislike something,we give 0 (zero); which is totally unhealthy and distributive way of thinking. To be honest, such attitude exists everywhere and at every step in our society be it religious , political or other affairs.
  For the readers; I would like to give one simple example: IT IS A RECENT HISTORY THAT THE MAJORITY OF THE SOCIETY TOOK LIDETU AYALEW (The Politician ) was named as “Ethiopias Mandela” BEFORE THINGS CHANGED THEIR WAY AND THE SO CALLED “KINIJIT” IS DEMOLISHED AND SENT TO GRAVE. THEN IT DIDDNT TAKE TIME TO EQUATE LIDETU AYALEW WITH “DEVIL” .
  We can also count thousands of concrete examples if in need be in our religious and other aspects of life. I personally believe that, we as a nation are far behind the rest of the world. Every individual is not ready to accept differences ; We dont really know who we are, what is our capacity…and so on.
  Our football was totally out of international tournaments . Though the representatives that we have to day lose ever game even 100 to null ; WE HAVE TO APPRECIATE THAT.
  I want to mention one good quote here:
  IF YOU WANT TO GO FAST, GO ALONE; IF YOU WANT TO GO LONG,GO TOGETHER.
  Please my brothers and sisters, we lost yesterday, we lost today. STOP POINTING ON SPECIFIC PEOPLE. APPRECIATE THOSE WHO DID WHAT THEY COULD AND SACRIFICED THEIR POWER AND TIME IN THE NAME OF OUR COUNTRY`S FLAG. ACCEPT DIFFERENCES DONT EXPECT PERFECTIONS AND THINGS TO HIT CLIMAX IN ONE NIGHT.
  I see one dangerous thing around the football like our stupid polities “METEFAFAT” ….please lets stop it here!!!! please lets give credit to those who did what they can, please stop insulting and pointing on individuals..

 4. Anonymous

  January 22, 2014 at 1:22 pm

  zim bleh atwura dedebe bemetchetik eko gobze ayidelkim egna jemari enji end spain chaf lay enhun alalinim

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የ5000ሜ ፉክክር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በአሸናፊነት አጠናቀዋል

Published

on

Dawit-Seyaum-1
ትላንት ምሽት በኖርዌይ ኦስሎ በተከናወነው የዳይመንድ ሊግ 5000 ሜ. ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉትን ደረጃዎች በመቆጣጠር አሸንፈዋል፡፡ 

በዝናባማ የአየር ሁኔታ ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፉክክር ዳዊት ስዩም በመጨረሻዎቹ መቶ ሜትሮች ውስጥ ፍጥነቷን በመጨመር ጉዳፍ እና ለተሰንበትን ቀድማ አንደኛ ወጥታለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሪገን 2022 የአለም ሻምፒዮና ከመረጣቸው ዕጩ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተችው ዳዊት በኦስሎ ያሸነፈችበት 14፡25.84 የሆነ ሰአት የራሷ ምርጥ ሲሆን እጅጋየሁ ታዬ (14.12.98) እና ለተሰንበት (14፡24.59) ባለፈው ወር በዩጂን ካስመዘገቧቸው በመቀጠልም የዘንድሮ የአለም ሶስተኛው ፈጣን ነው፡፡ በውድድሩ ላይ ከነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን መካከል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርቀቱ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ያደረገችው አልማዝ አያና በ14:32.17 ስድስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ ሀዊ ፈይሳ በ14:33.66፣ ፅጌ ገብረሰላማ በ14:43.90፣ እና አበራሽ ምንሴዎ በ14:47.98 በቅደም ተከተል ሰባተኛ፣ አስረኛ እና አስራ አንደኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ ሶስቱም ያስመዘገቡት ሰዓት የራሳቸውን ምርጥ ያሻሻሉበት ሆኗል፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ እ.ኤ.አ. በጁን 2008 ዓ.ም. ያስመዘገበችውና 14:11.15 የሆነው የኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 5000 ሜትር የውድድር ስፍራ ሪከርድ ይሰበራል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡  
ዳዊት ስዩም ውድድሩን በድል ካጠናቀቀች በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠችው አስተያየት ‹‹ዛሬ ለእኔ ደስታን ስላመጣልኝ በውድድሩ ሰዓት የነበረውን ዝናብ ወድጄዋለሁ ማለት እችላለሁ፡፡ ጠንካራ ተፎካካሪዎች የነበሩበት ከባድ ውድድር ነበር እናም ሁሉንም ለማሸነፍ በቅቻለሁ። በርቀቱ የራሴን ምርጥ ሰዓት ማሻሻል መቻሌም አስፈላጊ ነበር፡፡ በስታድየሙ ውስጥ በከፍተኛ ስሜት ድጋፍ ይሰጡን የነበሩ ወገኖቻችን ነበሩ። ለሰጡን ድጋፍ እናመሰግናለን።›› ብላለች፡፡
 
በኦስሎ የወንዶች 5000 ሜትር የመጨረሻ ፉክክሩ በኢትዮጵያውያኑ ጥላሁን ሀይሌ እና ሳሙኤል ተፈራ መካከል የነበረ ሲሆን ጥላሁን የ1500 ሜትር ስፔሻሊስቱ ሳሙኤልን በአጨራረስ ፍጥነት ቀድሞ በ13:03.51 በአንደኛነት አጠናቋል፡፡ ሳሙኤል ተፈራ የራሱ ምርጥ በሆነ 13:04.35 ሁለተኛ ሲወጣ ጌትነት ዋለ የግሉ የዓመቱ ምርጥ በሆነ 13:04.48 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። በውድድሩ ላይ የነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሚልኬሳ መንገሻ በ13:05.94 አምስተኛ እንዲሁም አሊ አብዱልመናን የራሱ ምርጥ በሆነ 13:16.97 አስረኛ ወጥተዋል፡፡
ጥላሁን ሀይሌ ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠው አስተያየት ‹‹ሶስት ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘን መጨረስ መቻላችን ጥሩ አፈጻጸም ነበር። እየጠነከርኩ እንደሆነ የተሰማኝ ሲሆን በውድድሩ እና ባስመዘገብኩት ሰዓትም ተደስቻለሁ። ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ ስለነበኩ ወደ አሸናፊነቱ መመለስ መቻሌ በጣም ጥሩ ነው።›› ብሏል፡፡

በኦስሎ የሴቶች 800ሜ. ውድድር ላይ ተፎካካሪ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ድሪቤ ወልቴጂ በ1፡58.69 አምስተኛ ሆና አጠናቃለች።
Continue Reading

Articles

የዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ሻምፒዮና በእኔ እይታ

Published

on

IMG_0110
ከመጋቢት19-24/2014 ዓ.ም በሐዋሳ አለም አቀፍ ስቴድዮም የተደረገው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሞላ ጎደል ስኬታማ በሚባል ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ከአምስት አመት በኋላ በድጋሚ በአካል በመገኘት ስለተከታተልኩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና የግል ምልከታዬን እንደሚከተለው አጠናቅሬዋለሁ፡፡

የበለጠ ትኩረትን በሳቡት ውድድሮች ዙሪያ የተመዘገቡ ውጤቶችን በወፍ በረር በመዳሰስ ስጀምር ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የመጨረሻ ቀን የወንዶች 5000ሜ. የአለም ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና የ3000ሜ የብር ሜዳልያ አሸናፊው አሊ አብዱልመና 13፡45.0 በሆነ ሰዓት ከጥላሁን ሀይሌ፣ ጌትነት ዋለ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ቀድሞ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የፉክክሩ አካል የነበረው እና የርቀቱ የወቅቱ የአለም ሻምፒዮን ሙክታር እድሪስ ስድስተኛ ወጥቷል። 

ከ20 ዓመት በታች የ3000ሜ የአለም ሻምፒዮኑ ታደሰ ወርቁ በ28፡12.0 የወንዶች 10,000ሜ. ሻምፒዮን ሲሆን በ1996 ዓ.ም. በአትሌት ስለሺ ስህን ተመዝግቦ የነበረውን 28፡16.23 የሆነ የሻምፒዮናው ሪኮርድ ለማሻሻልም በቅቷል፡፡ በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፉክክር ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በቀዳሚነት የጨረሰችበት 31፡21.5 የሆነ ሰዓት አዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በርቀቱ የከዚህ ቀደሙ ሪኮርድ ለተሰንበት ግደይ ከሶስት ዓመት በፊት ያስመዘገበችው 32፡10.13 የሆነ ሰዓት ነበር፡፡

ሳሙኤል ፍሬው በዘንድሮ የወንዶች 3000ሜ. መሰናክል አፈፃፀም ከአለም ሁለተኛው ፈጣን በሆነ 8፡22.5 ሰዓት አሸናፊ ሲሆን ጌትነት ዋለ ከአራት ዓመት በፊት አስመዝግቦት የነበረውን 8፡28.98 የነበረ የሻምፒዮናው ሪኮርድም አሻሽሏል፡፡ በሴቶች 3000ሜ. መሰናክል ከ800ሜ ወደ ረጅም ርቀት የተሸጋገረችው ወርቅውሃ ጌታቸው በ9፡41.8 ሰዓት መቅደስ አበበን (9:43.8) በማስከትል በአሸናፊነት አጠናቃለች። 

አድሃና ካህሳይ (3:51.0) የወንዶች 1500ሜ ፉክክሩን በበላይት ሲያጠናቅቅ በሴቶች 1500 ሜ አያል ዳኛቸው (4:10.0) ተጠባቂዋ ዳዊት ስዩምን (4:11.1) በመቅደም በአንደኛነት አጠናቃለች። በ800ሜ. ወንዶች ቶሌሳ ቦደና (1:47.1) በሴቶች ወርቅነሽ መሰለ (2:02.1) አሸናፊ ሆነዋል።
ዮብሰን ብሩ በ400ሜ/400ሜ መሰናክል (45.9/50.5) ድርብ ድል ሲቀዳጅ፣ በወንዶች ጦር ውርወራ ኡታጌ ኡባንግ ብሔራዊ ሪኮርድ በሆነ 73.28ሜ. አሸንፏል፡፡ የኋልዬ በለጠው እና ዮሃንስ አልጋው በእርምጃ ሩጫ የሻምፒዮንነት ክብርን ተቀዳጅተዋል።

ጥቂት አስተያየቶች፡-
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪ እንደሆነ እና ለዕድገቱ እንደሚቆረቆር ሰው በብሔራዊ ሻምፒዮናው ላይ ስለተመለከትኳቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ጥቂት አስተያየቶቼን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡-

አዎንታዊ ጎኖች
• ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉትን ተግዳሮቶች በሙሉ በመቋቋም ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ከአዲስ አበባ ውጭ አካሂዶ በሰላም ማጠናቀቅ መቻሉ አንደኛው ስኬቱ ነው፡፡

• በሻምፒዮናው ላይ ጥቂት የማይባሉ ታዋቂ አትሌቶች በሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ፉክክር ላይ ተሳታፊ ሆነው ሲወዳደሩ መመልከት የተቻለ ሲሆን በተለይም በወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ላይ የታየው የኮከብ አትሌቶች ፉክክር ልዩ ነበር፡፡

• በውድድሩ ወቅት ለአትሌቲክስ ዳኞች የብቃት ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱም የውድድሩን ጥራት ለማሳደግ የሚረዳ እንደመሆኑ እሰየው የሚባል ነው፡፡
 
• እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሉት ክለቦች ለአትሌቲክስ ስፖርት የበለጠ ትኩረት በመስጠትና ተጠናክሮ በመቅረብ ከዚህ ቀደም በጠንካራነታቸው ከሚታወቁት መከላከያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የቅርብ ተፎካካሪ ሆነው መታየት፤ የኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ፖሊስ እና ሲዳማ ቡና ክለብ አትሌቶችም ጠንካራ ተሳትፎ ሳይዘነጋ የሻምፒዮናው ፉክክር ድምቀት ነበሩ፡፡ 
• የአንዳንዶቹ ተገቢነት አጠያያቂ ቢሆንም ብዛት ያላቸው የሻምፒዮናው ሪኮርዶች የተሻሻሉበት ውድድርም ነበር፡፡ 

አሉታዊ ጎኖች
• የሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ውድድር ውጤት አሁንም በኤሌክትሮኒክስ የሰዓት መቆጣጠሪያ የማይደገፍ መሆኑ በተለይም በአጭር ርቀት እና በሜዳ ላይ ተግባራት ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ልፋት ተገቢውን እውቅና እንዳያገኝ እያደረገ ይገኛል፡፡ የሻምፒዮናውን ውጤቶች በዘመናዊ እና ዓለም አቀፉን መለኪያ በሚያሟላ መልኩ አለመያዝ በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ ለተሳትፎ የሚያበቁ ውጤቶችን በማስመዝገቡ ረገድ የሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ አሁንም መፍትሄ ያልተበጀለት ጉዳይ ነው፡፡ 
 
• የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ሚዲያ/ለአጠቃላዩ ሕዝብ የሚያስተላልፈው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶችን ውጤት ብቻ መሆኑ አወዳዳሪው አካል የሚያደርገውን የራሱን ውድድርም ሆነ አትሌቶቹ የለፉበትን ውጤት ከማስተዋወቅ አኳያ በቂ አይደለም፡፡
 
• በወንዶች የጦር ውርወራ እና የሴቶች ምርኩዝ ዝላይ ብሔራዊ ሪኮርዶች እንደተመዘገቡ ይታመናል፤ በሴቶች 100ሜ መሰናክል እና የወንዶች 400ሜ መሰናክል የተመዘገቡት ሰዓቶችም የምንግዜውም ፈጣን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውድድሩ በኤሌክትሮኒክስ ታይሚንግ ያልተደገፈ እና የንፋስ ንባብ ያልነበረው መሆኑ ውጤቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።

• በ20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታዎች የተመዘገቡት ሰዓቶች ከሚጠበቀው በላይ እጅግ በጣም ፈጣን እና እውነታዊ አለመምሰላቸው በውድድሩ ላይ የተፈጠረ አንዳች ስህተት መኖሩን የሚያመላክቱ መሆኑ፡፡ እንዲህ አይነት ለማመን የሚከብዱ እና ጥርጣሬን የሚፈጥሩ አይነት ውጤቶች ሲመዘገቡም የተፈጠረ ስህተት መኖር አለመኖሩን ለማጣራት አለመሞከሩ፡፡
   
• የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ ለውድድር የማይፈቀድ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማን በመጠቀም የተመዘገበ ውጤት በሪኮርድነት ጭምር ተይዞ መፅደቁ። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከተከለከሉ ጫማዎች ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ሕገ ደንቦችን ማወቅና መተግበር ቢገባውም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ የተከሰተው ነገር የውድድር ሕገ ደንቦቹ መረጃ በፌዴሬሽኑ ውስጥ በትክክል የተሰራጩ እንዳልሆነ የሚያመላከት ነው፡፡ 

• በሴቶች 1500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይ አትሌት ዳዊት ስዩም የሻምፒዮናውን ሪኮርድ ያሻሻለችበት ውጤት እንደተመዘገበ በውድድሩ ወቅት በተደጋጋሚ ሲነገር ከተደመጠ በኋላ ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውጤቱ በሐዋሳው ውድድር ላይ ተሻሻሉ ከተባሉት የሻምፒዮናው አዲስ ሪኮርዶች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም የፌዴሬሽኑን ግልፀኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ለረጅም ግዜ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች በቅርበት ከመከታተሌ አንፃር በራሴ እይታ ያስቀመጥኳቸው እንደመሆናቸው አንዳንዶቹ ሀሳቦች አከራካሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የውድድር ደንቦችን በአግባቡ ከማስፈፀም አኳያ በታዩት ክፍተቶች ዙሪያ ምንም የሚያከራክር ጉዳይ ስለሌለ በወቅታዊ የውድድር ደንቦች ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት ላለባቸው የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ አስፈላጊውን ገለፃ እና ትምህርት መስጠት የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት ነው፡፡ ከውድድር ጋር የተያያዙ ደንቦችን ከመጣስ አኳያ በሀገር ውስጥ በሚደረጉ ውድድሮች እንደቀላል ነገር የሚታለፉ ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም ተደግመው እንደግል አትሌቶችን እንደቡድን ሀገርን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍሉ ይችላሉና አስፈላጊው ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ባለፈው መስከረም ወር በቪየና ሲቲ ማራቶን ውድድሩን በአሸናፊነት ጨርሶ የነበረው ኢትዮጵያዊው ደራራ ሁሪሳ የገጠመውን አንዘንጋው! 

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመልካም ጎኑ ስሟ እንዲነሳ በሚያደርገው እና በትልልቅ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ የኩራታችን ምንጭ በሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት እንደጎረቤታችን ኬንያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ የብቃት ደረጃ ላይ ደርሰን ማየት የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንም የውድድሮቹን ጥራት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ።   
   
የ10,000ሜ. አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር (Photo by EAF)

በመጨረሻም በሀዋሳ በተካሄደው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመሮጫ ጫማ ጋር የተያያዙ ደንቦችን በማስከበሩ ረገድ የተፈጠረውን ክፍተት እንደማስተማሪያ ብንጠቀምበት በሚል የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ፡-

የመሮጫ ጫማ ደንቦች ለትራክ ውድድር

64 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የዘንድሮ የራስ አል ካይማህ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በሐዋሳ በተከናወነው 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 31 ደቂቃ ከ21.5 ሰከንድ  በመግባት የ10,000ሜ. አሸናፊ ሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ዓለም አቀፉን ደንብ ከግምት ባላስገባ ሁኔታ ውጤቱን በአዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድነት ጭምር አፅድቆት አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ መጋቢት 20/2014 በተደረገው የሴቶች የፍፃሜ ፉክክር ላይ በኢትዮጵያ ምድር የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሰዓት የሆነው ውጤት በአለም አትሌቲክስ ዘንድ እውቅና ሊሰጠው የማይችል ነው።

ለምን?

አትሌቷ የሶል ውፍረቱ 40ሚሜ የሆነ ዙምኤክስ ቬፐርፍላይ (ZoomX Vaporfly) ጫማ አድርጋ በመወዳደሯ ምክንያት።

ደንቡ ምን ይላል?

በትራክ ውድድሮች ላይ የሚፈቀደው ከፍተኛው የሶል ውፍረት ፡-
– 20ሚሜ ከ 800ሜ በታች ለሆኑ ውድድሮች እና ለሁሉም የሜዳ ላይ ተግባራት (ከስሉስ ዝላይ በስተቀር)

– 25ሚሜ ለ800ሜ እና ከዛ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ

– 40ሚሜ ለትራክ ላይ የእርምጃ ውድድሮች

እነዚህ ደንቦች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 31, 2024 ድረስ በሥራ ላይ ይውላሉ። ከኖቬምበር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ለ800ሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ የሚፈቀደው ከፍተኛ የሶል ውፍረትም ወደ 20 ሚሜ ዝቅ የሚል ይሆናል።

የትራክ ላይ መወዳደሪያ ስፓይክ ጫማ ከሌለኝስ?  

ደንቡ የጎዳና ላይ የመሮጫ ጫማዎች በትራክ ላይ እንዳይደረጉ አይከለክልም ነገር ግን በ25 ሚሊ ሜትሩ ገደብ ምክንያት 30 ሚሜ ወይም 40 ሚሜ የሆኑ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማዎች በትራክ ውድድሮች ላይ እንዲደረጉ አይፈቅድም፡፡

ለበለጠ መረጃ :-
https://www.worldathletics.org/news/press-releases/new-athletic-shoe-regulations-approved-2022

Continue Reading

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Trending