Opinions
የሚያሳፍር ይዘዝብህ!!

መስከረም 12፣ 2007 | በደመቀ ከበደ
አስቸኳይ ፕሮጀክት ለማስረከብ ዛሬ ቀጠሮ አለብኝና በጠዋት ነው የተነሳሁት፡፡ ከሲኤምሲ መገናኛ እና ከመገናኛ – ብሔራዊ – ሜክሲኮ በሚጭኑ ሁለት ታክሲዎች ነው ቢሮዬ የምደርሰው፡፡
ከሲኤምሲ መገናኛ ባለው ጉዞዬ አንድ ወዳጅ ታክሲ ውስጥ አጋጠመኝና የወዳጅነቴን ከፈልኩ፡፡ ደረስን አመስግኖኝ ወረደ – ወረድኩ፡፡
ሁለተኛውን ታክሲ ያዝኩ – ከመገናኛ ብሔራዊ ሜክሲኮ የሚያደርሰኝን፡፡
ሰው በጠዋቱ ነቅሶ ወጥቷልና እስከ አፍ ጢሟ ጫነን፡፡
ከጥቂት ጉዞ በኋላ ረዳቱ ሂሳብ መቀበል ጀመረ፡፡
ሁሉም እያወጣ ከፈለ፡፡
አገር ሰላም ብዬ እጄን ወደ ኪሴ ሰሰድኩ፡፡
ጠላታችሁ ክው ይበልና እንደ ግንቦት ዋልካ መሬት ሰውነቴ ከላይ እስከታች ተሰነጣጠቀ፡፡
ቀኝ ኪሴን ፈተሸኩ – ብሮቼ የሉም፡፡
ግራውንም አየሁት – የሉም፡፡
የጃኬቴንም በረበርኩ – ፈፅሞ!
እንደዚህ ዓይነት ‹‹ቅሌት ወይ ውርደት ይሉት ነገር›› ሲያጋጥመኝ የመጀመሪያ ነውና ደንግጫለሁ፡፡
በግንባሬ የተንቸፈቸፈውን ላቤን በግራ እጄ እያባበስኩ ረዳቱን ‹‹ስንደርስ ልክፈል…›› አልኩት፡፡
‹‹ከኪሱ አውጥቶ ለመክፈል ባይመቸው ነው ›› በሚል ይመስላል ሌሎቹን ወደማስከፈከሉ ሄደ፡፡
ስልኬስ??
ቀኝ ኪሴ ገባሁ – እሱም የለም፡፡ አመዴ ቡን አለ፡፡
ዋሌቴስ ??
ወደ ኋላ ኪሴ ገባሁ – አለ፡፡
አፍታ ቆይቼ በተረጋጋ መንፈስ ሳስተውል ግራ እጄ ላይ አለ – ስልኬ፡፡ እፎይ አልኩ፡፡
ግን ብሮቼስ!
ጥሎብኝ ብዙ ብርም ቢሆን በዋሌት መያዝ አልወድም – በቃ ያለኝን ሁሉ በቀኝ ኪሴ ነው የምይዘው፡፡
ካሳንቺስ ስንደርስ ‹‹ወራጆች ወረዱ››፡፡
ለሶስት ተቀምጠንበት ከነበረው ወንበር አንድ ሰው ተቀነሰ፡፡
‹‹አሁን ለማውጣት ይመችሃል ክፈል›› አለኝ – ረዳቱ፡፡
አፌ ተያያዘ፡፡
‹‹እ… እ›› እያልኩ እንደገና ወደኪሴ ገባሁ፡፡
አፍጥጦ ያየኛል፡፡
‹‹በቃ ስንደርስ ኤ ቲ ኤም ሸበሌ ሆቴል ጋር አውጥቼ እሰጥሃለሁ፡፡ ብሮቼ ወይ ከኪሴ ስልኬን ሳወጣ ወድቀዋል ወይ ሌባ ሰርቆኛል፡፡›› አልኩት፡፡
‹‹ባክህ ክፈል – ይሄ የተበላበት ስልት ነው…›› አለኝ በማጓጠጥ፡፡
‹‹ፕሊስ ተረዳኝ – የምሬን ነው፡፡›› መለማመጥን የመሰለ አስጠሊታ ነገር በምድር የለም፡፡
‹‹ሰውዬ ትከፍል እንደሁ ክፈል – ታዲያ ገንዘብ ሳጥይዝ ዘው ብለህ ለምን ገባህ..›› ጮኸ፡፡
የተሳፋሪው ሁሉ ዓይን እኔ ላይ አፈጠጠ፡፡
ይሄኔ ‹‹አንዴ በቦክስ በለው.. ሌባ!!›› የሚሉት መሰለኝ – በሆዳቸው፡፡
እኔ ደግሞ ያኔ በደህናው ቀን ‹‹መልስ የለኝም፤ ዝርዝር የለኝም እያሉ ረዳቶች ሁሉ ሳይመልሱ የተውኩሏቸውን በተለያዬ ቀን የከፈልኳቸውን ብሮች እያሰብኩ ‹‹እርም ቁራጭ ሳንቲም ብተውላችሁ›› እያልኩ ነበር፡፡
‹‹ሰውዬ….!!›› አለ – የታክሲዋ ሁለመና በሚበታትን ድምፅ፡፡
ልሳን አጣሁ – ሽምቅቅ አልኩ፡፡
‹‹አቦ ተወኛ ወጣት አይደለህ – ወይ እመነኝ ወይ ተወኝ!!›› አልኩት፡፡
ተሳፋሪው ሁሉ አፍጥጦ ከማየት በቀር የተነፈሰ አለመኖሩ አበገነኝ፡፡ ሾፌሩም አንዳች ቃል አልወጣውም፡፡
አንዲት ወጣት ሴት ..
‹‹አንተ ምን ሆነሃል – አምስት ብር ከኪስህ ወድቆ አያውቅም እንዴ በፈጣሪ – እየነገረህ አይደል ያጋጠመውን – ይሄው እኔ እከፍልለታለሁ፡፡›› አለችና ወረወረችለት፡፡
ለቀም አድርጎ አጉተመተመና ዝም አለ፡፡
መናገሪያየን ሁሉ ነው የቆለፈብኝ – የከፈለችልኝን ልጅ እንኳን የማመስገን ድፍረት አጣሁ፡፡
አይደረስ የለም ደረስን – ለወትሮው ብሄራዊ አካባቢ ነበር የምወርደው – ታክሲ መጨረሻው ድረስ ‹‹ሽምቅቅ ብዬ›› ሄድኩ፡፡ ወረድን፡፡
ስወርድ…
ሾፌሩ ብር አወጣና ‹‹ሶሪ እንዲህ ያጋጥማል – ቀጣይ ታክሲ መሳፈሪያ ስለማይኖርህ እንካ ›› ብሎ ዘረጋልኝ፡፡
አሁንማ ሸበሌ አወጣለሁ – ግን አመሰግናለሁ፡፡
እንደወረድን የከፈለችልኝን ልጅ ፈለኳት – የለችም ሄዳለች፡፡
ብሮዬ እንደገባሁ ይሄን ፃፍኩ፡፡
አንቺ የማላውቅሽ የማታውቂኝ ወጣት ‹‹አመሰግንሻለሁ!!››
News
EthioTube ወቅታዊ – ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወዴት? | Ethiopia and United States Relations
Articles
የ40 /60 ፈተና – በአርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን

አዲስ አበባ ከተማን ሰንገው ከያዝዋት ችግሮች መካከል የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚስተካከለው ያለ አይመስለኝም፡፡ ዜጎች ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገቢያቸውን ለቤት ኪራይ ስለሚያውሉ ቀጣይነት ያለው ሃብት መፍጠሪያ አቅም ነስቷቸዋል፡፡ የኽም ኑሮአችንን በመከራ የተሞላ አድርጎብናል፡፡ ይኽንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት የቤቶች ግንባታ ፕሮገራም መንደፉ የሚያስመሰግነው ቢሆንም ወደ መሬት ያወረደበት መንገድ ግን አነጋጋሪ ሆኖ የሚቀጥል ይመስለኛል፡፡
ከነኚህ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው በተለምዶ 40/60 በመባል የሚታወቀው የቤቶች ግንባታ በመሠረታዊ የዲዛይን ስህተቶች የተሞላ እና ስህተቶቹን ለማረም የተኬደበት መንገድም ሌላ ተጨማሪ ስህተት የፈጠረ ይመስለኛል፡፡ ለመሆኑ ስህተቶቹ ምንድናቸው?
1) ፕሮግራሙ እና የተሠሩት ቤቶች አይተዋወቁም፡፡ ዜጎች ‹‹ታገኙታላችሁ›› በተባሉት አጠቃላይ የወለል ስፋት መሠረት በባንክ መቆጠብ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በጥድፊያ እንዲገነቡ የተደረጉት አፓርታማዎች ግንባታቸው ከተጋመሰ በኋላ የወለል ስፋታቸው የተዛነፈ መሆኑ በመታወቁ እንደምንም ተብቃቅተው መንግስት ከዜጎች ጋር በተፈራረረመው ውል መሰረት እንዲስተካከሉ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ (በአጭሩ ለማስረዳት ጃኬት ለማሰፋት ለተዋዋለ ደንበኛ ካፖርት ከሠፉ በኋላ ስህተቱን ለማረም ካፖርቱን በመቆራረጥ ሌሎች ጃኬቶች ለማውጣት እንደመሞከር ያለ ነው፡፡ከካፖርት ጃኬት ይወጣ ይሆናል፡፡ ግን የተጨማደደ እና የተጣበበ መሆኑን መቀበል ይኖርብናል፡፡ በ40/60 እየሆነ ያለውም ይኼው ነው፡፡)
2) የአደጋ ጊዜ ማለጫ የላቸውም፡፡ ግንባታቸው ከተጋመሰ በኋላ የታወቀውን የአደጋ ጊዜ ማመለጫ ደረጃ ቀድሞ ባልታሰበበት ሁኔታ ‹‹እንደምንም ብላችሁ አንድ ጥግ ፈልጉለት›› በማለት ለመፍታት መሞከር መፍትሔውን ሰንካላ ማድረጉ አይቀሬ ነው፡፡
3) የቆሻሻ ማስወገጃ ሊኖራቸው ይገባ ነበር፡፡ 12 ፎቅ ተገንብቶ ነዋሪዎች የሚያስወግዱትን ደረቅ ቆሻሻ በፌስታል ቋጥረው እንዲወርዱ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ በቀላሉ የቆሻሻ ማንሸራተቻ (Trash shooter) ማሰብ ይገባ ነበር፡፡
4) ለሁሉም በሽታ አንድ ክትባት! እንኳንስ ህንጻ ዛፍ እንኳን ሲተከል ከቦታ ቦታ የተለያየ እና ተስማሚ ዓይነት ይመረጣል፡፡ አሁን የሚሠሩት አፓርታማዎች ግን ለሁሉም የንፋስና የፀሐይ አቅጣጫዎች፣ ለአፈር እና ለድንጋይ ዓይነቶች እንዴት አንድ ዲዛይን ይሠራል? ይህን ያህል ጥድፊያስ ም ለማትረፍ ነው?
5) ንድፉ አያምርም፡፡ ይህን የመሰለ ከፍተኛ በጀት እና ጉልበት የሚፈስበት ብሔራዊ ዕቅድ በቂ የባለሙያዎች ክርክር እና ጥናት ሳይደረግበት በጥድፊያ በተሞላ ውሳኔ ወደ ተግባር መገባት አልነበረበትም፡፡ ሲሆን ሲሆን ከፍተኛ አማካሪዎች የተሳተፉበት የዲዛይን ውድድር ተደርጎ የተሻለው ሊመረጥ ይገባ ነበር !
የእነኚህ ሁሉ ችግሮች ምንጮች ሁለት ናቸው፡፡ ጥድፊያ እና አነስተኛ ግምት ! መፍትሔው ከዚሁ ይመነጫል፡፡ ሰከን ብሎ ማሰብ እና ተገቢው ትኩረት! ሀሳቡ የፓርቲ ሳይሆን የመላእክት እንኳን ቢሆን አፈጻጸሙ ከተበላሸ ፈተናውን ወደቀ ማለት ነው ፡፡
Source: አርኪቴክት ዮሐንስ መኮንን
Keenya ስለእኛ
የወገኔ “Amarika”

ያገሬ ሰዉ ፤ ከቀየዉ ቢሻለኝ ቀን ቢያወጣልኝ ብሎ ነፍሱን ሸጦ የፈለሰበትን ምድር ስም ተይብ ቢባል የሚያስፍራቸዉ ፊደላት ናቸዉ፤ Amarika….ብዬ ብጀምር ማጋነን ይሆንብኛል :: ወገኔ በ Amarika ድህነትን ሊያራግፍ ሀብት ሊሸምት ግዞትን አሽቀንጠሮ ነፃነትን ሊሸክፍ ተስፋን ሰንቆ ከተተ በAmarikaም ከተመ፡፡ ከወገን ኖሮ ከመራብ በሀገር ኖሮ ከመሰደብ በመሸበት አድሮ ከባየተዋር ምድር ጥጋብ እና ክብርን ሽቶ ሮጠ፤ ተሰደደ፡፡ ሆነለት፡፡ የቀን ሶስት ሩብ እየለፋ ከምን እንደተሰራ በማይታወቅ እንጀራ ሆዱን እየነፋ እነ እማማን እነ አባባን እነ ኩቺን እነጢሎን ዶላር ያስመረዝራል፤ ቀን ያወጣላቸዋል፤ ከጎረቤት በላይ ያደርጋቸዋል፡፡ እሱ የመኪና ተራ እያስጠበቀ እነ እማማን እነ ጢሎን ባለጋቢና ያደርጋቸዋል፡፡ ሳይማር አሜሪካ የላከዉን ህዝብ ሳይማር ወግ ያስተምረዋል፡፡ ለነ ኩቺም ያሜሪካ ወንድማቸዉ ከእግዜር በታች ከኦባማ ጎን ነግሶ የትንሽ ስራ መራቂያ ያሜሪካ መናፈቂያ የጎረቤት ማስፈራሪያ ሆኖ ይኖራል፡፡ ወገኔም ይህን ያዉቀዋል፤ ጎረቤታቸዉን እነ ቡለቲን አፍ ማስያዙ ያኮራዋል፡፡ ስራዉን ኑሮዉን ደብቆ የስራ ትንሽ እንደሌለ ቤተሰቡን ይመክራል፡፡ ስለወገኔ ኑሮ ዝርዝር ሁኔታ በስልክም ሆነ ባካል ከሱ ጋር መነጋገር አያስፈልግም የሴት ዕድሜ የሱ ስራ አይጠየቅማ፡፡ የቤቱ ትልቅነት የመኪናዉ ዘመናዊነት በአሜሪካዊዉ ወገኔ በዝርዝር ሊወሳ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን የሱ ቤት የሱ መኪና ነዉ ማለት ላይሆን ይችላል፤ አይጠየቅም፡፡
ነገ ያቺ ሙሉ ቀን ስትመጣ ከስምንት ሻንጣ ጨርቅ እብድ ከሚያክል ስልክ እና የአሜሪካ ሰንደቅ ካለበት ካኒቴራ ጋር ቦሌ ይደርሳል እነኩቺም ካስራ አምስት ዘመድ አዝማድና ዳጎስ ካለ ብድር ጋር ይቀበሉታል…እንኳን ላፈርህ አበቃህ…ከዛማ የአንድ ወር ቆይታው በፌሽታና በአሜሪካ ኑሮ ትረካ የተሞላ ይሆናል፡፡ እንደዛ ሲሰራ ሲለፋ ለኖረው ወገኔ መዝናናት ሲያንስ ነው::
ችግር፤ ተስፋ ማጣት፤ ፖለቲካ፤ ጭቆና…ብዙ ብዙ ምክንያት ከምንወዳት ሀገራችን ያፈናቅሉናል፤፤ አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች የሰለጠነዉ አለም የተሻለ አማራጭ ሆነዉ እናገኛቸዋለን፡፡ ለማንኛዉም ምክንያት ይሁን ሀገር ቀይሮ መኖር የግለሰብ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ሊከበርም ይገባዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የምንሄድበትን ቦታ፤ የምናልመዉን ኑሮ በሚገባ መረዳት ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ የተሻለ ለዉጥን መፈለግ ድንቅ ነዉ፡፡ ለመለወጥ ግን ማወቅ ይቀድማል፡፡
አሜሪካን በእንግሊዝኛ ተይብ ቢባል አብዛኛዉ በትክክል እንደሚፅፍ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን ምን ያህሉ ሊኖርባት የመረጣትን ሀገር ቋንቋ ለመግባቢያ እንኳን በሚጠቅም ደረጃ ያዉቃል ብትሉኝ በጣም ጥቂቱ ይሆናል መልሴ፡፡ የተወሰኑ ቃላትን በአሜሪካዊያን ዘይቤ ይጠራ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ሙሉ አረፍተ ነገር በተሟላ መልኩ ቀምኖ አያቀርብም፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ ታዲያ ከታክሲ ሹፌርነት እና ከመኪና ጠባቂነት ያለፈ ህልም እንዴት ይኖረዋል፡፡ ቀን ሲሞላ ተመልሶ ወይንም በስልክ ስለአሜሪካ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች እና ህዝብ ገድል ከማዉራት ያለፈ ህልም ልንሰንቅ እንችላለን? ሁሌ ከህንፃዉ ዙሪያ ያሉትን ጥቃቅን ስራዎቸን ሰንሰራ መኖርን ከማለም፤ ለወገናችን የተሳሳተ(ያልተሟላ) መረጃን ከመስጠት፤ ራሳችንን አለአግባብ ከመኮፈስ አልፈን ህንፃዉ ዉስጥ ካሉት ሰዎች ራሳችንን እንደአንዱ የማየት፤ ህንፃዉንም ሆነ ዉስጡ ያሉትን ንግዶች (አገልግሎቶች) የራስ የማድረግ ህልም ቢኖረን ይበዛብናል? አይመስለኝም ከአንድ ድሃ የአፍሪካ ሀገር የሄደ ስደተኛ ልጅን መሪዋ አድርጋ ለመሾም የፈቀደች ሀገር እኛ ከተጋን ትምህቱንም ሆነ ሀብቱን አትከለከንም። ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆኑ ወገኖቻችን በዙሪያችን ሞልተዉናል።
ነገር ግን መጀመሪያ መማር ማወቅ ለመለወጥ መዘጋጀት ይቀድማል። አሁን ምንሰበስበው ስምንትና ዘጠኝ ዶላር ለነገው ህልማችን ግብዐት እንጂ ራሳችንን ማታለያ የሀገር ቤት ወገናችንን ማደናበሪያ መሳሪያ መሆን የለበትም።
በነገራችን ላይ ይህ ጽሑፍ በትምህቱም ሆነ በንግዱ ለራሳቸው ስኬታማ ለወገን ኩራት የሆኑትን አይመለከትም። እነሱ በተቃራኒው ለነኩቺ ወንድም ወገኔ ምሳሌዎች ናቸው። በል እንግዲህ ወገኔ ወደ Amarika ስትመለስ መዝገበ ቃላት ስንቅህ ይሁን ከዛ ለሚጥለው ደረጃ ስትበቃ እንማከራለን:: ደህና ሰንብቱ።
-
EBS Mogachoch9 years ago
[New] EBS Drama Series – Mogachoch : ሞጋቾች | Episode 7
-
Articles9 years ago
Ethiopia’s renewable energy revolution shouldn’t fail to empower its poor
-
News2 years ago
መንግሥት ከሕወሓት ይልቅ ለአገሪቱ ሥጋት የሆኑ ሌሎች ችግሮች አሉብኝ አለ
-
Opinions2 years ago
On the TPLF’s Love Affair With ‘Genocide’
-
Music4 years ago
2019 ESFNA Atlanta: Ethiopian Day – Ethiopia Hagerachin : ኢትዮጵያ ሀገራችን
-
Music4 years ago
2019 #ESFNA Atlanta: Ethiopian Day | Neway Debebe – Hageren Alresam : ሀገሬን አልረሳም
-
Articles8 years ago
ሰበር ዜና፦ ተዋናይት ሰብለ ተፈራ (ትርፌ) በመኪና አደጋ ህይወቷ አለፈ
-
Bahilawi Zefenoch10 years ago
Bahilawi Zefenoch – ባህላዊ ዘፈኖች
Genet
October 12, 2014 at 4:58 pm
Betam yemeyasdeset derset yemsmesel nger new nger gen yahya nger yeewnet yemhone new ena sewoch banchkakein teru new ena antein gen kahuin ahuin metawe beya segahu eko anteletolo mfethewen wedehuwala akoyeto yemtsffe ewketo alehena berretan endzhe kewenett gar yalu Derammawochin metsafe Albhe beyaa emakerhulhu. Lejetowanem teberkey elalehu leweyalawem andandya entezazen enjie malet deferet ayedelemena hulum sew leba ayedlemna merarat albhe elalhu.bye
hagos
September 26, 2014 at 3:43 am
ያለ ነውና ኣንተም ተማርበት ልጅትዋን እግዚኣብሄር ይባርካት
yadeta berhanu
September 25, 2014 at 1:50 pm
Enen betam yegeremegn Ye leju Tsihuf chilota ye ewunet betam des yilal . Keziya beterefe , Tininish santimochen iyelekakemu yemiyaskerut ye taksi redatochachenen tazebkuachew
habtamu mohammed
September 25, 2014 at 1:46 pm
በጣም የሚገርም አጋጣሚ ነው ለማንኛውም ብሮችህን ስታስቀምጥ ለወደፍቱ ባሉህ ኪሶች ከፋፍለህ የማስቀመጥ ልምድ ይኑርህ.
Anonymous
September 25, 2014 at 12:56 pm
በጣም ይገርማል ልጅቷ እግዛብሄር ይባርካት ሌሎችም የተቸገረን መርዳት በእግዛብሄር ዘንድ ዋጋ አለውና ቸል አትበሉ
Anonymous
September 25, 2014 at 9:21 am
enderasu
Anonymous
September 25, 2014 at 9:21 am
endihm ayente yesew chenqet yemigebawe sew ale…..melekam sewche yebezulen…
melesekassaw
September 25, 2014 at 8:21 am
BECHGRH GIZYE YEDERESELHN ATRSA.
frehiwot Gidey tedla BERHAYE
September 25, 2014 at 6:22 am
DEAR READERS,WHOEVER CAN HELP ME TO GET BACK TO MY OWN CITY IN FRANCE, i’LL BE GREATFUL,AND BLESS YOU ALL.BECAUSE ANYPERSON CONTACT ME WITH AWRONG REASON i ALREADY GAVE MY FULL DOCMENT TO THE gOVERMENATALLY LAW MAKERS WHICH BY THE WAY LATE ME TO STAY FOR AT LEAST 3YEARS THAT i GOT THIS MESSAGE FROM WESTSIDE OF eTHIOPIA,WHEN i VISIT MY GREATGRANNIES LAND wELEGA aRJO pROVIDENCE SO,i TRIED TO COMMUNICATE WHY i SHOULD STAY LIFE CAN’T BE REPEATED BAD MEMORY TO ME AND OTHERS WHO REALLY WANTS TO CHANGE IN THE NAME OF gOD aLMIGHTY PAS,RELIGIOUS WAR ONLY i NEED TO FREE LIKE HE FREES ME,THERE,BUT REMEMBER BOYS CAN NOT UNDERSTAND GIRLS PERSONALL PROBLEM.
Anonymous
September 25, 2014 at 6:09 am
read “ታክሲ አዲ’ሳባ ሰማያዊው ግመል”
Anonymous
September 25, 2014 at 6:08 am
Sewoche ebakachu andu wendmachu endi sisakeke zeme belachu mayetu agebabe ayedelem pls Ethiopianweyane enredada agatamiwe Hulachenenem bezure selemidersen. (betame azgnalew) teru temrete newe
Anonymous
September 24, 2014 at 7:21 pm
በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር እነዚ የሰዉ ንብረት የሚዘርፉ ሌቦች ጉዳይ ነዉ የሚገርመዉ ነገር ደግሞ ማንም ይሄን ጉዳይ አይቶ እዳላየ የማለፉ ነገር አንዳንዴ ሰዉ በሀገሩ እንደ ልቡ መሆን የማይችልበት ስልክ አዉጥተን እንኳን ማናገር የማይቻልበት ሀገር ታክሲ ተራወች በተለይ ሰወች በብዛት የሚገበያዩበት ቦታዎች ችግሩ የከፋ ነዉ ሁሉም የየበኩሉን ካልተወጣ ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የማይቀር ነዉ
Anonymous
September 24, 2014 at 2:26 pm
Betam new yesakut really! Yihen neger yetsafkew sewuye derasi bithone yawatahal!
kefyalewtadele
September 24, 2014 at 1:56 pm
yigermal
ለማ ዓለሙ
September 24, 2014 at 1:36 pm
ሹፌሪና የችን እህታችን ልታመሰግንህ ትገበለህ
Anonymous
September 24, 2014 at 1:07 pm
for next time ask your neighbor before you argue with this rude co-drivers, i paid many times for such incidents even though i never faced such case, most of the “weyalas” are very fast to start a fight, i dont know what is wrong with them
http
September 24, 2014 at 12:53 pm
heyyy…tirekah temechitognal.