Connect with us

Health

ከመጠን በላይ በሆነ ላብ ተቸግረዋል? እንግዲያውስ መፍትሄዎቹ እነሆ

Published

on

sweet

sweet

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

ላብ በጣም ጥሩ ነገር ነው ምክንያቱም ሰውነትዎን ስለሚያቀዘቅዝልዎ ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ሲሆን የሚያሳቅቅ እና የሚያስፈራ ችግር ነው፡፡ ላብ የቆሸሽን ከማስመሰሉ በተጨማሪም ባክቴሪያዎች ከመጠን በላይ እንዲራቡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ይህም ሁኔታ መጥፎ የሰውነት ጠረን እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ሁልጊዜ የሚለብሱት ቲ-ሸርት መርጠብ ያስጨንቅዎት ይሆናል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሚያልበን ላብ ለመቀነስ ይረዳሉ ይጠቀሙባቸው፦

የቡና እና ሻይ አወሳሰድዎን ይቀንሱ፡፡
ካፌይን(Caffeine) ለብዙዎቻችን የምንጊዜም ተመራጭ ትኩስ መጠጣችን ሲሆን የነርቭ ስርዓታችንን ያነቃቃል፡፡ ይህ እንዲሆን ባንፈልግም የላብ አመንጪ እጢዎቻችን በእጥፍ እንዲሰሩ(ላብ እንዲያመነጩ) ያደርጋቸዋል ስለዚህ ትኩስ ነገሮችን መጠቀም ማቆም የሚደገፍ ሃሳብ ነው፡፡

በብዛት ውሃ መጠጣት፡፡
አብዛኛው ላብ የሚሰራው ከውሃ ስለሆነ የላብ መጠንን ለመቀነስ የውሃ አጠቃቀማችንን መቀነስ አለብን ማለት አይደለም፤ በቀን ከ8-12 ብርጭቆ ውሃ በአማካይ መጠጣት ተገቢ ነው ይህን ማድረጋችን ሰውነታችን እንዲቀዘቅዝ ያደርገዋል ስለዚህ ሰውነታችን ራሱን ለማቀዝቀዝ ላብ አያመነጭም፡፡

ሲጋራ ማጨስ እና ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጥ መጠጣት ያቁሙ፡፡
እነዚህ ሁለት ልምዶች በቶኖች የሚገመቱ መርዛማ ነገሮች ወደ ሰውነታችን እንዲገባ ያደርጋሉ እነዚህ መርዛማ ነገሮችን በጥቂቱ ከሰውነታችን ለማስወገድ ከመጠን በላይ ያልበናል በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስና ከመጠን ያለፈ የአልኮል መጠጦች መጠቀም ለጤንነታችን ጎጂ ስለሆኑ አይመከርም፡፡

በፀረ-ኦክሲዳንት የበለጸጉ ምግቦችን ይመገቡ፡፡
ፍራፍሬ እና አትክልቶች ፀረ-ኦክሲዳንት በውስጣቸው ይዘዋል ይህም በሰውነት ውስጥ ያሉ መርዛማ ነገሮችን ለማክሸፍ ይረዳል፡፡እነዚህ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች መርዛማ ነገሮችን ስለሚያከሽፉቸው እነዚህን መርዞች ከሰውነታችን ውጭ ለማስወገድ ላብ ማላብ አያስፈልግም፡፡ አንዳንድ ጥሩ የፀረ-ኦክሲደንት ምንጮች /መገኛዎች/፦ ወይን፣ ቀያይ ፍሬዎች፣ ለውዝ፣ ብርቱካናማ ቀለም ያላቸው ፍራፍሬዎች ናቸው፡፡

ከሚያቃጥሉ ምግቦች እራስዎን ያርቁ፡-
የሚያቃጥሉ ምግቦች ለጤንነታችን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን በብዛት እንዲያልበን ስለሚያደርጉ አይመከርም፡፡ ምንም ለእኛ ለኢትዮጲኖች ከባድ ቢሆንም የሚያቃጥሉ ምግቦች የሰውነትን ሙቀትን በመጨመር ከመጠን በላይ እንዲያልበን ያደርጋሉ ፡፡ የላብ አመንጪ እጢዎቻችን ወደ ስራ በመግባት ሰውነትን ያቀዘቅዛሉ፡፡

ጭንቀትና ፍርሃትን ያስወግዱ፡-
ፍረሃት እና ጭንቀት የላብ አመጪ እጢዎች ከመጠን በላይ በስራ እንዲጠመዱ ያደርጋቸዋል ይህም ውጥረት፣ ስጋትና ሃሳብን ለመቀነስ የሚወስዱት እርምጃ ነው፡፡ የተለያዩ ዘና የሚያደርጉ ስፖርታዊ እንስቃሴዎችን በመስራት ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች በመቀነስ የሚያልበንን የላብ መጠን መቀነስ ይቻላል፡፡

ከቤት ከመውጣትዎ በፊት ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ፡-
ቀዝቃዛ ሻወር በማንኛውም ምክንያት ያላበንን ላብ ለማስወገድ እና የሰውነታችንን ሙቀትን ለማመጣጠን ይርዳናል፡፡ ቀዝቃዛ ሻወር በሚወሰድበት ጊዜ ፀረ-ባክቴሪያ ሳሙናዎችን በመጠቀም የሰውነትን ጠረን/ማዕዛ ማስተካከል ይቻላል፡፡ በሙቅ ውኃ ሻወር መውሰድ ያለበዎትን ከመጠን ያለፈ የላብ ችግር ያባብሳል፡፡

የብብዎትን ፀጉር ያስወግዱ፡-
ላብ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያልቡን የሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ አንዱ ብብት ነው፡፡የላብ ማድረቂያ ምርቶችን ከመጠቀም ባሻገር የብብት አካባቢ እንዲቀዘቅዝ ፀጉርን ማስወገድ ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ በተጨማሪም የብብት ፀጉርን መላጨት ሽታ አምጭ ባክቴሪያዎችን እንዳይራቡ ያደርጋቸዋል፡፡

ትክክለኛ የሆኑ ልብሶችን መጠቀም(መልበስ)፡-
ከተፈጥሮ ነገር ውጭ የተመረቱ ልብሶችን እንደ ኮተን፣ ላይለን እና ውል የሰውነት ቆዳዎችን እንዲተነፍስ ያደርጋል፡፡ ሰው ሰራሻ (ሲንቴቲክ) ፋይበሮች ሙቀትን በማመቅ ብዙ ላብ እንዲያልበን ያደርጋል፡፡ ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ በቂ የሆነ አየር በልብስ እና በቆዳ መካከል እንዲዘዋወር ያደርጋሉ፡፡ ደብዛዛና ቀለል ያሉ ልብሶችን መልበስ ይመከራል ፡፡ በተለይም ጥቁር ቀለም ያላቸው ልብሶች ሙቀትን ይሰበስባሉ፡፡

ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረትን ያስወግዱ፡-
ከመጠን ያለፈ ወይም በጣም ወፍራም ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ያልባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት ስላላቸው ነው፡፡ በእውነት ከዚህ የላብ ችግር መውጣት የሚፈልጉ ከሆነ እና ከትክክለኛው/መጠነኛ የሰውነት ክብደት በላይ ከሆኑ ሸንቀጥ ለማለት ይሞክሩ፡፡

መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena
እንዲሁም የኢትዮጤና ድህረ ገጽን ይጎብኙ www.ethiotena.net/wordpress

Continue Reading
19 Comments

19 Comments

 1. Seni

  June 16, 2017 at 4:02 am

  በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው

 2. yalelet

  August 4, 2016 at 6:03 pm

  በጣም አስተማሪ እና እውቀት አሰጨባጭ ነው
  በትክክል የተባለውን አድርጌ የሚያልበኝ ሀሉ ቀንሶልኛል አናመሰግናለን

 3. Anonymous

  December 29, 2015 at 12:41 pm

  አመሰግናለሁ

 4. Anonymous

  October 11, 2015 at 5:59 am

  tnx

 5. buta

  October 11, 2015 at 5:41 am

  eweeeeeeeeee

 6. Nega guleshu

  October 11, 2015 at 4:15 am

  Gbetam arif tmhrt new etegebrewalehu

 7. yichalal

  October 11, 2015 at 1:52 am

  Mekrachi hu aylyne

 8. ተመሥገን አበራ

  October 10, 2015 at 8:34 pm

  አረፍ ነው

 9. Anonymous

  October 10, 2015 at 3:31 pm

  woow! likely advice specialy 2 me!! 10ks!

 10. Anonymous

  October 10, 2015 at 1:31 pm

  በጠም ጠቃም ምክር ነዉ;እናመሰግናለን።

 11. Anonymous

  October 10, 2015 at 12:40 pm

  በጣም ጥሩ ትምህርት ነው ያገኘሁት በዚው ቀጥሉ

 12. eshetutefera

  October 10, 2015 at 11:51 am

  Good

 13. Atalay

  October 10, 2015 at 7:49 am

  It is an interesting issue should be known by …. but now adays how many of us read usable texts? Frim reading we can be dr. for ourselves in every moment..I like it responssibly…

 14. Anonymous

  October 10, 2015 at 5:14 am

 15. Bayera Nega

  October 10, 2015 at 5:10 am

  ለዚ እኮ ነው የምወዳችሁ…..በርቱ ብዙዎችን እየጠቀማችሁ ነው።

 16. Anonymous

  October 10, 2015 at 5:03 am

  txs!!!

 17. guye

  October 10, 2015 at 4:35 am

  betam amesginalew

 18. Anonymous

  October 10, 2015 at 3:45 am

  nice to advise me

 19. Adane Dawit

  October 10, 2015 at 2:06 am

  10Q batam tamchitognal

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

Construction of Africa CDC headquarters in Ethiopia to begin ahead of schedule

Published

on

By

Africa CDC

The proposed construction of the new Africa Centre for Disease Control and Prevention (Africa CDC) headquarters in Addis Ababa, Ethiopia is supposedly expected to begin this year ahead of schedule.

This was proposed by Xi Jinping, the president of the People’s Republic of China during the recent China-Africa summit. He said that the decision was reached with an aim to help the African continent compact the COVID-19 pandemic.

“The new Africa CDC will play a major role in the fight against the coronavirus pandemic across Africa and China will continue to do whatever it can to support Africa’s response to the virus,” affirmed President Jinping.

The Government of China was given the mandate to undertake the construction of the US $80bn new Africa CDC headquarters building in June last year through an Agreement signed with the African Union Commission.

Project overview

The new Africa CDC headquarters building will be built in a Village, south of Addis Ababa, on a site that covers an area of approximately 90,000m2 with a total construction area of nearly 40,000m2.

Upon completion, the structure will comprise of fully furnished emergency operation center, a data center, a laboratory, a resource center, briefing rooms, a training center, a conference center, offices, and expatriate apartments

Xi Jinping said that his country will tirelessly work hand in hand with Africa to fully deliver the health care initiative which was adopted at the FOCAC Beijing Summit, and speed up the construction of China-Africa Friendship Hospitals and the cooperation between paired-up Chinese and African hospitals.

“Together, we will build a China-Africa community of health for all,” he concluded.

Source: ConstructionReviewOnline.com

Continue Reading

Articles

“አጋጣሚ ነው ግን….?”

Published

on

By

Psychology of Coincidence

Psychology of Coincidence

“አጋጣሚ ነው ግን….?”

(ሳም አለሙ)

አንዳንድ ጊዜ “እንዴት ሊሆን ቻለ?” በሚል ጥያቄና ግርምት እንድንዋጥ የሚያስገድዱን አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ…ለምሳሌ አሞኛል ብለን(የእውነት አሞን) ከአለቃችን ፍቃድ ወስደን ከስራ ቦታ ወደ ቤታችን እያመራን ነው እንበል..እንዳጋጣሚ ሆኖ ታዲያ ለረጅም ጊዜ ተለይቶን የቆየ ወዳጅ ጋር ተገጣጠምን…ይሄው ወዳጃችን ሳንገባበዝ አንፋታም በማለት “ግግም” ይላል…”ጥቂት አመም አርጎኝ ነው…” ብንለውም ወይ ፍንክች!!..ከቆይታ በኋላ ከካፌ ወይም ከሬስቶራንት ስንወጣ ታዲያ ከመሥሪያ ቤታችን አለቃ ጋር መላተም! ልብ በሉ ሰውየው ከዚህ ቀደም እዚያ አካባቢ በዚያ ሰዓት ላይ ተከስቶ አያውቅም!… አለቃችን ወዲያው ምንድነው ሚያስበው? እንደዋሸነውና ከዚህ በኋላ የሆነ ምክንያት አቅርበን ፍቃድ ብንጠይቀው ሊሰጠን እንደማይገባ ይወስናል…እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ጥያቄዬ…ነገሩ እንዴት ሊሆን ቻለ? ከዚህ ቀደም በዚያ ሰዓት ከስራ ቦታው የማይወጣው አለቃችን እንዴት ትዝብት ላይ በሚጥለን አጋጣሚ ሊከሰት ቻለ? እንዲህ አይነቱን “አጋጣሚ” የፈጣሪ ወይም የሰይጣን እጅ ከበስተጀርባው እንዳለበት አርገው ሚያስቡ አጋጥመውኛል…አባባላቸው ውሀ ባያነሳም ጉዳዩ አወዛጋቢ ነው።ሌላ ምሳሌም ልጥቀስ..ስለሆነ ሰው እያሰባችሁ መንገድ ላይ ዎክ እያደረጋችሁ ሳለ በድንገት ከዚያ ሰው ጋር ተገናኝታችሁ አታቁም? በርግጥ እንዲህ አይነቱን ክስተት ነጮች Telepath በማለት ባጭሩ ሊገልጹት ይሞክራሉ….የሆነ ሆኖ በበኩሌ እንዲህ አይነቱን “አጋጣሚ” እንዳጋጣሚ ብቻ ልወስደው አልቻልኩም…ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያሻው ጉዳይ ይሆን?!

Continue Reading

Articles

የዚካ ቫይረስ በሽታ

Published

on

ulvety68t0mw0a33zh6z

ulvety68t0mw0a33zh6z

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

ዚካ ቫይረስ የፍላቪቫይረስ ዝርያ ሲሆን ከደንጉ፣ ቢጫ ወባና ከምዕራብ ናይል ቫይረስ በሽታዎች ጋር የሚመሳሰል ባህሪ አለው፡፡ ይህ ቫይረስ ዚካ ፌቨር ወይም የዚካ በሽታ ለተባለ በወባ ትንኝ ለሚተላለፍ በሽታ መነሻ ነው፡፡ የዚካ ቫይረስ በአሁኑ ጊዜ የአለምን ትኩረት እየሳበ የመጣ በሽታ ሊሆን ችሏል የዚህም ምክንያት ጥናት አድራጊዎች በሽታው አዲስ ከተወለደ ህፃን የጤና ችግርና ከአእምሮ ችግሮች ጋር የተያያዘ ሆነው ስላገኙት ነው፡፡

የዚካ ቫይረስ ስርጭት

ዚካ ቫይረስ በመጀመሪ የተገኝው በ1947 ዓ.ም በኢንቴቤ ኡጋንዳ ውስጥ በሚገኝ በዚካ ጫካ ረኸሰስ በሚባል የዝንጀሮ ዝርያ ደም ውስጥ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰውና በወባ ትንኝ ውስጥ በኡጋንዳ፣ ሴኔጋል፣ ናይጀሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ማሌዢያ ተገኝቷል፡፡

በ2007 በጣም ከፍተኛ የሆነ የዚካ ቫይረስ ኢንፌክሽን ያፕ በተባለ ደሴት የተከሰተ ሲሆን 75% የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል በወረርሽኙ ተጠቅቶ ነበር፡፡

የዚካ ቫይረስ እስከ ሜይ 2015 ድረስ በምዕራብ ንፍቀ ክበብ ስርጭቱ አልተከሰተም ነበር የብራዚል ህብረተሰብ ጤና ባለስልጣን ወረርሽኙ በሰሜን ምስራቅ ብራዚል መከሰቱን እስካረጋገጠበት ድረስ፡፡

በአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት በብራዚል የመጀመሪያው የበሽታው ስርጭት የታየ ሲሆን ዚካ ቫይረስ በ21 ሀገሮች እና በአሜሪካ ግዛቶች ተሰራጭቷል፡፡

የዚካ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች

የዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በወባ ትንኝ ንክሻ ይተላለፋል፡፡ ቫይረሱ ኤደስ() በምትባል የወባ ትንኝ ዝርያ ውስት ይገኛል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዚካ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በደም ልገሳ፣ ከእናት ወደ ልጅ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ይተላለፋል ነገር ግን ይህ መተላለፊያ መንገድ የመከሰት ዕድሉ በጣም ጥቂት ነው፡፡ በአንድ አጋጣሚ ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ተገኝቷል፡፡

በቫይረሱ ተይዘን ምልክት እስከምናሳይበት ያለው የጊዜ ቆይታ በውል የመታወቅ ባይሆንም ከ 3-12 ቀናት እንደሆነ ይገመታል፡፡

የበሽታው ምልክቶች

ከ 20-25% በዚካ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብቻ የበሽታውን ምልክት ያሳያሉ፡፡ በብዙ በሽተኞች ላይ የሚታዩ የዚካ በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

• ትኩሳት

• ሽፍታ

• የመገጣጠሚያ ህመም

• የአይን መቅላት

• የጡንቻ ህመም ናቸው፡፡

የዚካ ኢንፌክሽንን የከፋ የሚያደርገው ሁለት ከአእምሮ ጋር የሚያያይዙት ጉዳዩች ስላሉ ነው፡፡

• በህክምና ቋንቋ ማይክሮሴፋሊ ይባላል የዚህ ቃል ትርጉም የሆነ ችግር ኖሮበት የሚወለድ ህፃን ለማለት ሲሆን የሚወለደው ህፃን ጭንቅላት እጅግ በጣም ያነሰ እና አእምሮ ዕድገቱን ሳይጨርስ ይወለዳል፡፡ ይህ ችግረ የሚያጋጥመው የህፃኑ እናት በመጀመሪያው ትራይሚኒስቴር ወቅት በዚካ በሽታ የተያዘች እንደሆነ ነው፡፡

• ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ጉሊያን ባሪ ሲንድረም ()ይባላል፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ሲሆን የራሳችን የበሽታ መከላከያ ስርዓት የራሳችንን ነርቭ ሴሎች በማጥፋት/በመግደል የጡንቻ መልፈስፈስ ሲያስከትል አልፎ አልፎ ደግሞ ልምሻ ወይም ፓራሊሲስ ያስከትላል፡፡

የዚካ በሽታ ምርመራ

ለዚካ ኢንፌክሽን የሚያገለግል በብዛት በአለማችን ላይ የምንጠቀምበት ምርመራ የለም በአብዛኛው ሰዎች ላይ ምርመራው መሠረት ያደረገው ምልክቶችን በማየትና የስርጭት ቦታውን በማወቅ ነው፡፡ በላቦራቶሪ ውስጥ ከሚደረጉ ምርመራዎች መካከል ፒ.ሲ.አር()፣ ሴሮሎጂካል ምርመራዎች()፣ ኒኩሊክ አሲድ አምፕሊፊኬሽን ምርመራዎች() ይጠቀሳሉ፡፡

 

የዚካ ቫይረስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገድ

• የወባ ትንኝን መቆጣጠር እና ማጥፋት

በግቢ ውስጥና በአካባቢያችን የተከማቸ ውሃ ዌም ኩሬ ካለ ማስወገድ

• በወባ ትንኝ እንዳንነከስ ራሳችንን መከላከል

የበሽታው ስርጭት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ ከሆነ በወባ እንዳይነከሱ የግል ጥንቃቄን ማድረግ አጎበር መጠቀም፣ በሽታው ወደተከሰተበት ቦታዎች አለመሄድ፡፡

• ስለ ዚካ ቫይረስና ወባ ለማህበረሰቡ ማሳወቅ

ህብረተሰቡ ስለ ዚካ ቫይረስ እና መከላከያ መንገዶቹ ማሰወቅና እራሳቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ ማድረግ፡፡

መልካም ጤንነት!!

ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

 

 

 

 

Continue Reading

Trending