Connect with us

Articles

ከሁሉም በላይ የሀገርንና የህዝብን ደህንነትና አንድነት ይቅደም!! – በዲያስፓራ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች የተሰጠ የጋራ አቋም መግለጫ

Published

on

Arena-logo1

Arena-logo1

ከሁሉም በላይ የሀገርንና የህዝብን ደህንነትና አንድነት ይቅደም!!
በዲያስፓራ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች የተሰጠ የጋራ አቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞና ብሶት በማስመልከት በውጭ ዓለም የሚኖሩ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች ከተለያዩ ቦታዎች ሰሞኑን ባደረጉት አስቸኳይ የቴሌ ኮንፈረስ ውይይት የሚከተለውን ባለስምንት ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ ለመላ ኢትዮጵያውያን አስተላልፏል።

ዓይናቸውን በፍቅረ ንዋይና በስልጣን ጥምነት የተሰወሩ አምባ ገነኖች የትም ይብቀሉ የትም ተመሳሳይ ባህርይ አላቸው። ዙሪያቸውን በወታደራዊ ሐይል ተከቦ ሲያዩት ዓለምን በመዳፋቸው ውስጥ ያስገቡት ይመስላቸውና ልባቸውን በትዕቢትና በትምክህት ስለሚሞላ ነፃነትና ፍትሕ ከሌለ ነገ ፈራሽ መሆኑን ከታሪክ አይማሩም። ሰብኣዊ ርህራሄና የይቅርታ መንፈስ የላቸውም። የህልውናቸውን መሰረት ሕብረተሰቡን በዘር፣ በጥቅምና በሀይማኖት ለያይተህ ግዛ የሚል ስለሆነ የህዝቡን ነፃ እንቅስቃሴ፣ አንድነትና መደራጀት ከጦር በላይ ይፈሩታል። ራሳቸውን ልዩ ፍጡራንና ጀግኖች አድርገው በመመልከት ከሀገርና ከሕግ በላይ በመሆን የህዝቡን ጭኾትና ህይወት የዶሮን ያህል ግምት አይሰጡትም። የዓይን ብሌየናቸው ገንዘብና ስልጣን ስለሆነ የሀገርንና የወገንን ፍቅር የላቸውም። በርስትነት በያዙት የብዙሃኑ መገናኛ አማካኝነት ነጋ ጠባ የሚያስተጋቡት መዝሙርና የጉራ ነጋሪት በለው፣ ፍለጠው፣ ርግጠው፣ ቁረጠው፣ ግደለው ከሚል ቀረርቶ በስተቀር የህዝቡን ብሶት የማዳመጥና አርቆ የማየት ዓቅም፣ ሞራል፣ ብቃትና ተፈጥሮ የላቸውም። ይህ በመሆኑም የህዝቡን ዓመፅ ቤተ መንግስታቸው አፋፍ ላይ ደርሶ እንደ እሳተ ጎመራ እስከሚለበልባቸው ድረስ ተቻችሎና ተከባብሮ አብሮ ከመኖር ይልቅ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በማለት እስከመጨረሻ ህልፈታቸው ድረስ መሟሟትንና መተላለቅን ይመርጣሉ። ሀገርንና ህዝብን አጥፍቶ መጥፋት ማለት ትርጉሙ ይኸው ነው።

የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስትም ከአምባ ገነናዊ ተፈጥረው በመነሳት 90 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ህዝብ በማግለልና የበይ ተመልካች በማድረግ ሀገሪትዋን ጠቅልሎ በሞኖፓል እየገዛ ይገኛል። ተቃውሞ ያነሳ ዜጋ ሁሉ በአግባቡ ከማስተናገድና ዴሞክራሲያዊ መፍትሔ ከመሻት ይልቅ ልክ ትናንት ደርጋውያን በመውደቂያቸው ዋዜማ ያሳይዋቸው የነበረ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዎችና ፉኮራዎች ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ የመብት ጥያቄ ያነሱትን ዜጎች ሁሉ የተለያዩ የቂጥያ ሰሞችን በመለጠፍ የሻዕቢያ ተላላኪ፣ ሽብርተኞች፣ የደርግ ስርዓት ናፋቂዎች፣ ትምክህተኞች፣ የጎዳና ነውጠኞች፣ ቦዘኔዎች፣ ነፍጠኞች፣ ወዘተ በማለት ፍትሓዊ ጥያቂያቸውን በማናናቅና በማፈን ወታደራዊ የሐይል እርምጃው ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሲተገብር ቆይቷል።

የተከበርከው የትግራይ ህዝብና መላው ወገናችን ይህ የሐይል እርምጃና የመብት ረገጣ ዛሬ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ብቻ የተጀመረ ሳይሆን በተለይም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነኝ የሚለው ህወሓት በአስር ሽዎች ሰማእታት የወደቁበትን የትግል አላማ ከህዝቡ እጅ ነጥቆ በመውሰድ ጥቂት በቤተሰብ: በጋብቻና በትውልድ ሐረግ የተሳሰሩትን ዘመድ አዝማድ መሪዎች ጥቅም ማስጠበቂያ በማድረግ የህዝቡንና የሰማእታቱን አደራ የበላ ድርጅት ነው። ዛሬ በትግራይ ምድር “እኔ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ” ወይም ትግራዋይ ነኝ ብለህ በነፃነት ኰርተህ ለመረማመድ ቀርቶ እንደ ሰብኣዊ ፍጡር በህይወት ለመኖርም አስቸጋሪ የሆነበት ጊዜ ነው። እንደ መሪዎቹና ካድሬዎቻቸው አመለካከት ከሆነ በትግራይ የህወሓት ደጋፊ ያልሆነ የክልሉ ተወላጅ እንደ ትግራዋይ ተደርጎ ስለማይታይ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ብቻ ሳይሆን ስብእናውን፣ ዜግነቱንና ማንነቱንም ጭምር የተነጠቀ ነው። ይህንን የህወሓት የሰብኣዊ መብት ረገጣን በመቃወም በተለያየ ጊዜ በክልሉ በተንቤን ዓቢይ ዓዲ፣ በነበለት፣ በእምባስነተይ፣ በሁለት አውላዕሎ፣ በእግሪ ሐሪባ፣ በዓዲ ረመፅ፣ በብዘትና በሌሎች ወረዳዎች ላይ የተደረጉትን የህዝቡን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በወታደራዊ ሐይል ከመበተንና ከማጥቃት አልፎ ሰልፉን አስተባብሯል የተባሉትን ግማሾቹ አምልጠው ወደ ስደት ሄዷል ሌሎቹ ደግሞ የት እንደገቡ የማይታወቅ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርቷል። ቤተሰቦቻቸውንም እንደውሻ ከያሉበት እየታደኑ ታስሯል: ተሰዷል: አሊያም ደብዛቸው ጠፍቷል። ሌላ ቀርቶ ምርጫ መጣ በተባለ ቁጥርናበዋዜማው በመላ ትግራይ እስከ አፍንጫውን የታጠቀ መደበኛ ሰራዊትን በማዝመትና አካባቢውን በጥይት ጭኾት ነጎድጓድ በማደንቆር ሻዕቢያ ባንተ ላይ ሊዘምት ተንቀሳቅሷል እያሉ ህዝቡን በማሸበርና በማስደንገጥ የምርጫ ጎሮጀውን ከህዝቡ እጅ በአፈ ሙዝ ነጥቀው በመውሰድ መቶ በመቶ አሸንፈናል ይላሉ።

ከዚህም በላይ የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄን በማንሳት በሕግ ተመዝግበው: የህዝቡን ልዕልና አክብረው: ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል አምነው: ሕገ መንግስቱ የፈቀደላቸውን መብት መሰረት አድርገው በመታገል ላይ በሚገኙት የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ፓረቲ አባላት ላይ እየደረሰ ያለው በደል ስንመለከትም ህወሓት ምን ያህል የሰብኣዊ ፍጡር ደመኛና ባላንጣ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። በትግራይ የተለየ አመለካከት መያዝ ወይም የዓረና ትግራይ ደጋፊ መሆን ማለት እንደ ነውር ወይም እንደወንጀለኛ ስለሚያስቆጥር ከማሰር፣ ከመግደልና ከማፈን አልፈው “የዓረና አባል ለሆነ ትግራዋይ ሁሉ እሳት እንዳታስጨሩ፣ ሲሞት እንዳትቀብሩ፣ ልቅሶ እንዳትደርሱ፣ በሃዘንም ሆነ በደስታ ከነርሱ ጋር በአካል እንዳትገናኙና እንዳትቆሙ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አግልሏቸው” የሚል ማሕበራዊና ሀይማኖታዊ ውግዘት እንዲደርስባቸው ያደርጋሉ። በመላ አባላቱ ላይ የከፈቱትን የስነ ልቦናዊ ጦርነት አልበቃ ብሏቸው በሆዳቸውና በህልውናቸው ለመቅጣት ሲባልም የስራ ዕድል እንዳያገኙ: ሀብት እንዳያፈሩ: ሌላ ቀርቶ ከለጋሽ ሀገሮች የሚመጣውን የስንዴ እርዳታም ሳይቀር እንዳይሰጣቸው ይከለከላሉ። ገበሬ ከሆነ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እንዳያገኝ፣ የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ ከስራው እንዲባረር፣ ተማሪ ከሆነ ተምሮ የስራ ዕድል እንዳያገኝና ከተለያዩ የትምህርት ዕድሎች እንዲታገድ፣ ነጋዴ ከሆነ ደግሞ ንግድ ቤቱን እንዲዘጋ አሊያም ከመጠን በላይ ግብር እንዲጫንበት እየተደረገ ይገኛል። በቤተሰብ ደረጃም ዘልቀው በመግባት ልጆቻቸው የዓረና አባል ሆነው የተገኙትን ወላጆች ይቀጣሉ። ሚስት ወይ ባል የዓረና አባል ሆኖ ከተገኘ ሚስቱ ባልዋን እንድትፈታ በማድረግ ቤተሰብ ያፈርሳሉ ይበትናሉ። ህዝቡን ሳይወድ በግድ አንድ ለአምስት በማደራጀት እርስ በርሱ እየተናከሰ እንዲኖር በማድረግ በተለይም የዓረና አባላትን የማጥቂያ መሳሪያ አድርገው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። በዚሁ አስከፊ የአፈና እርምጃ ምክንያት በተለይም ወጣቶቹ ያላቸው ምርጫ ሳይወዱ በግድ ባርነትን አሜን ብሎ ተቀብሎ መኖር ወይም ዓይኑን ጨፍኖ ወደ ስደት መፍለስ ነው። ከዚህ በላይ ጭካኔ! አረሜንነትና በደል ምን ሊባል ይችላል። እውነት ህወሓት የትግራይ ህዝብ ጠበቃና ነፃ አውጪ? ህሊናችሁን ይፍረደው።

ዛሬ በኦሮሞያ: በአማራና በሌሎች ቦታዎች የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነትና የፍትሕ ጥያቄ በትግራይ ምድር እየተፈፀመ ካለው የመብት ረገጣና ኢፍትሓዊ እርምጃ የተለየ አይደለም። የኢሕአዴግ መሪዎች በተለይም ህወሓት የሁሉንም ቅራኔዎች: ጭቆናዎችና ዓፈናዎች መንሲኤ እነርሱ ራሳቸው ሆኖ ሳለ ዛሬም እንደለመዱት የማደናገሪያና የማጨበርበሪያ ተንኰላቸውን በመቀጠል የህዝቡን ጠበቃ በመምሰል በሌሎች ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በትግራይ ላይ ያነጣጠረ የእልቂት ጦርነት በማስመሰል የሽብር ፕሮፓጋንዳ መርዛቸውን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለው ተግባር ግን ሐቁ ሌላ ነው። ህወሓት ከተፈጠረባት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ስንመለከተው በዘረጋው የዓፈናና የለያይተህ ግዛ ፓሊሲ መሰረት ትግራዋይን እየገደለ ያለው ራሱ ህወሓትና አጋሮቹ ናቸው እንጂ ሌላ ባዕድ አይደለም። ትግራዋይን ሆን ብሎ ከኤርትራ ህዝብም ሆነ ከሌሎች አጎራባች ወንድሞቹ ጋር እሳት እየጫረ በጠላትነትና በጥርጣሬ ዓይን እንዲታይ ሌት ተቀን ጥረት እያደረገ ወገኖቻችንን ለግድያና ለቃጠሎ እንዲዳረጉ ምክንያት እየሆነ ያለው ራሱ ህወሓት እንጂ ሌላ አይደለም። ትግራዋይን ከቤት ንብረቱንና ከየመንደሩ እየተፈናቀለ ወደ ባህር ማዶና በየቦታው እየተጣለና እየተሰደደ ያለው የህወሓትን አድልዎና አፈና የፈጠረው ጠንቅ እንጂ ሀገሩንና ህዝቡን ጠልቶ አይደለም። ትግራዋይን በሻዕቢያ አለንጋ እየተገረፈ ከየቤቱ እየታደነና እየታፈነ መረብ ተሻግሮ ደብዛው እንዲጠፋ ምክንያት እየሆነ ያለው ራሱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪና ጠበቃ ነኝ እያለ የሚመፃደቀው ህወሓት እንጂ ሌላ አይደለም። እንደነ ታደሰ አብርሃንና አረጋዊ ገብረዮሐንስን የመሳሰሉት ወጣት የዓረና መሪዎች የገደለና እነ አብርሃ ደስታን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የድርጅቱን አባላትና ደጋፊዎች የተለየ አመለካከት ስለያዙ ብቻ እስር ቤት አጉሮ እያሰቃየና እያሳደደ ያለው ራሱ ህወሓት እንጂ ሌላ አይደለም። ህወሓት ራሱ ባመጣው ጣጣ ሻዕቢያ የትግራይ ህዝብን በወረረ ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ በመሆን ከእልቂት ያዳነው ራሱ የትግራይ ህዝብን ጨምሮ ጠቅላላ ኢትዮጵያዊ እንጂ ህወሓት ብቻውን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠረው ትግራዋይ በመላ ኢትዮጵያ ሀብትንና ንብረትን መስርቶ እየኖረ ያለው ህወሓት የቸረው መብት ሳይሆን ለዘመናት አብሮ ተፋቅሮ የቆየና የገዛ ሀገሩ መሆኑን ስለሚያቅ ነው። ትግራይም የትግርኛ ተናጋሪ ብቻ ሳትሆን የሌላውን ወገን አጥንት የተቀበረባት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሬት ናት። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ጠበቃና መድህን 90 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ በምንም መልኩ ጠላቱ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ በአጠቃላይ ለትግራዋይ ከህወሓት በላይ ጨቋኝና አፋኝ ስርዓት የለውም ቢባል ማጋነን አይሆንም።

የተከበራችሁ ውድ ኢትጵዮያውያን በሙሉ ከላይ የተጠቀሱትን ሐቆች እንደተጠበቀ ሆኖ በቅርቡ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች አካባቢዎች የተደረጉትን ህዝባዊ ሰልፎች በአመዛኙ በመላ ሀገሪቱ ላይ ያሉት ችግሮች ተመሳሳይ ስለሆኑ ትግላቸው የሚደገደገፍ ነው ብለን እናምናለን። ይሁን እንጂ እኛም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ቁስል ያላቸውን ጭቁን ወገኖች የትግሉን አጋር በመሆን በሙሉ ልባችንና ዓቅማችን እንዳንሳተፍ የሚያደርጉ አግላይ: ከኢትዮያዊነት ስነ ምግባርና ሃላፊነት ውጭ የሆኑትን አስጊ አዝማሚያዎችና ተግባራት ሲፈፀሙ ስናይ እጅጉን አሳዝኖናል። የሚያሳዝነውም ድርብ ድርብርብ ጉዳት ስላለው ነው። አንደኛ ድርጊቱ የጭቁኖች ኢትዮጵያውያንን የትግል አንድነት የሚያላላና የሚያዳክም ነው። ሁለተኛ በየአካባቢ የተነሳውን የህዝቡን እምቢተኝና እየተከፈለ ያለውን አኩሪ መስዋእትነት መንገዱንና አቅጣጫውን በማሳሳት እንደተለመደው ተዳፍኖና ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ነው። ሶስተኛ እነዚህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረጉ ስህተቶች ዞሮ ዞሮ ተጠቃሚ የሚሆነው ፍትሕ የጠማውን ህዝብ ሳይሆን እኛን በዘርና በሀይማኖት ከፋፍለው እርስ በራሳችን አናቁረውና በታትነው በጭቁኖች ደም እነርሱ ዘላለማዊ ስልጣናቸውን አደላድለው ለመኖር የሚፈልጉ አምባ ገነን መሪዎችንና ተከታዮቻቸውን የሚያጎለብት ነው። አራተኛ እየተፈፀመ ያለው የተዛባ ተግባርና እንቅስቃሴ በቂም በቀልና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ በዘር ማጥፋት ወንጀለኝነትንም ጭምር የሚያስጠይቅ ጥቁር የታሪክ ጠባሳ ነው። አምስተኛ ሀገርን የሚበታትን ከመሆኑም በላይ የእርስ በርስ እልቂትን የሚጋብዝ ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታና እንዲገታ ለማድረግም የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ሲቢክ ማሕበረ ሰቦች፣ ምሁራን፣ ወጣቱ ትውልድና ጠቅላላ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም የሚኖሩት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም ትብብራቸውን እንዲያሳዩ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። እዚህ ላይ መሰመር ያለበት ዓቢይ ጉዳይ ይህ የተዛባና መንገዱን የሳተ: በጥቂት ቡድኖች አነሳሽነት እየተፈፀመ ያለው ፀረ ህዝብና ፀረ አንድነት ተግባር ጨዋውና የዋሁን የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ተግባር ነው ብለን ፍፁም አናምንም። ትናንትም: ዛሬም ሆነ ነገ በምንወደው በአማራውና በኦሮሞው ህዝባችን ላይ ያለንን ልባዊ ፍቅር: ፅኑ እምነትና አክብሮት ፍፁም አይለውጠውም። ተራራን የሚያህል የጋራ ጠላት ፊት ለፊታችን ተጎልቶ እያለ ነገር ግን የጀመርነውን ትግል በዋናው ዓቢይ ጉዳይ በጋራ ጨቋኞቻችን ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን መንገዳችንን በማሳሳት እነሱ በሚሰጡን አጀንደ ላይ ተጠምደን ነገ ሁላችንም በእኩል የሚያስተናግድና ድምፃችንን የሚሰማ ስርዓት ሲረጋገጥ እግረ መንገዳቸውን ሊፈቱ በሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ በማትኮር ራሳችን በራሳችን ትግላችንን የሚጎዳ ተግባር መፈፀም ማለት ለጠላቶቻችን ዱላ ማቀበል ማለት ነው የሚሆነው።

ይህን ዓይነቱ ስሜት የወለደው ስህተት ደግሞ እውነተኛ የወገንና የሀገርን ፍቅር ካላቸውና ነገ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች በእኩል የሚስተናገዱባት: ነፃነትዋንና የግዛት አንድነትዋን የተጠበቀች: አንዲት የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድትረጋገጥ ከሚመኙና ከሚታገሉ ሐይሎች ይመነጫል ብለን ፍፁም አናምንም። ምክንያቱም በሀገራችን የነበረውና አሁን ያለው ታሪካዊና ነባራዊ እውነታ የሚያረጋግጥልን አንድና አንድ ብቻ ነው። እሱም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እውን እንድትሆንና ነፃነትዋንና ክብርዋንም ጠብቃ እስከ ዛሬ ድረስ እንድትኖር ያደረጉዋትና የመስዋእትነትን ዋጋ የከፈሉላት አንገፋና አናሳ ሳይባባሉ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ናቸው። ስለዚህ አንዱን ዘር በማግለል ወይም በመጥላት ነገ ሁላችንም የምንመኘው ፍትሕ: ነፃነት: ዴሞክራሲና ሰላም በፍፁም ሊረጋገጥ አይችልም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርንም መኖር አትችልም። በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ላይ የተመሰረተ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ውጤት ሊኖረውና የሀገርንና የህዝብን ሉዓላዊ ክብርና አንድነት ሊያስጠብቅ እንደማይችል ሩቅ ሳንሄድ በጎሮቤቶቻችንና በሌሎች ሀገሮች እየተካሄዱ ያሉትን አውዳሚ ክስተቶች ጉልህ አብነቶች ናቸው። በኛ እምነት ሀገር ማለት ህዝቡን ነው። ኢትዮጵያም የህዝቡን የትግል ቃል ኪዳን ውጤት ናት። በመሆኑም ህዝብዋን እየጠሉ ሀገር ወዳድ መሆንና ሀገር አለኝ ማለት አይቻልም። የሀገራችንን የአንድነት ሞሶሶ ተጠብቆ እንዲቆይ ያደረገው ዋናው ሚስጢሩም በመተማመን: በመከባበር: በመቻቻል: በመፈቃቀድ: በመረዳዳትና በመፈቃቃር ላይ የተመሰረተ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የአንድነት ቃል ኪዳን ነው። ከዚህ ውጭ አሁን ከደረስንበት 21ኛው የሰለጠነ ዘመንና የዓለም ህዝቦች ከጠባብ መንደራቸውን አልፈው በሁሉም መስክ በጋራ ጥቅምና በሰጥቶ መቀበል መርሕ ላይ የተመሰረተ አብሮ መኖር በጀመሩበት መዋእል ላይ እየኖርን ነገር ግን ይህን ሐቅ ማየት የተሳናቸው እንደገና እኛን ወደሗላ ወደ 16ኛው የመሳፍንት ዘመን መልሰው በዘርና በህዝብ ቆጠራ ላይ የተመሰረተ ስርዓት በመትከል ትልቁን ዓሣ ትንሹን ዓሣ እየበላና እየረገጠ የሚኖርባት ኢትዮጵያ እንድትሆን የሚመኙት ሐይሎች ፍፁም የማይሆንላቸው መሆኑን አውቀው በአስቸኳይ ከስህተታቸውንና ከሗላቀር ድርጊታቸውን እንዲታቀቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የተከበራችሁ ታጋይ ሐይሎችና ሲቪክ ማሕበረሰቦች አሁን በሀገራችን ያለው ሁኔታ ለሕግ ተገዝ የሆነ መንግስትና በሕግ የሚዳኝ ሕብረተሰብ በሌለበት፣ ሓላፊነት የሚሰማው መንግስትና የአመራር ብቃት ያላቸው የፓለቲካ መሪዎች በሌሉበት፣ ህዝብና መንግስት እሳትና ጭድ ሆነው በተፋጠጥ በቆሙበት፣ በአጠቃላይ ሀገራዊ የትግል አንድነት ባልተፈጠረበትና መልክ ባልያዘበት ሁኔታ ላይ እያለን ይህ ዓይነቱ የፓለቲካ ቀውስ መከሰቱ እጅግ የሚያሳስብና ፈታኝ ጊዜ ነው። ሰው እየሞተ ነው። በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ከማንም ጊዜ በላይ እየታፈሱ እስር ቤት እየተወረወሩ ናቸው። ሰዎች በማያውቁት ጉዳይ ላይ ጥቃት እየደረሰባቸውና ቤት ንብረታቸውን እየተው እየተፈናቀሉ ናቸው። ይህን ሁሉ ተደምሮ ሲታይ የሀገርንና የህዝብን ጥያቄ መልስ የሚሰጥና መስመር የሚያስይዝ ባሌቤት በማጣት ትልቅ የአመራር ክፍተት ተፈጥሯል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ሀገሪቱን ወደ ባሰ የፓለቲካ ቀውስና ብጥብጥ ልታመራ እንደምትችል የሚያጠያይቅ አይደለም። ስለሆነም ይህንን አስፈሪ ሁኔታና የእልቂት ድባብ ለመለወጥ ህዝብ: መንግስትና ሌሎች ታጋይ ሐይሎች ሚና ምን መሆን አለበት? ለሚለው ጥያቄ ትእግስት: ጥበብ: በሳል: ብቃት: የነቃና የተዋሃሃደ ጥረት የሚጠይቅ ታሪካዊ ሓላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በሀገሪትዋ ያለውን ሁኔታ ራሱ ተናጋሪ ነው።

የኢሕአዴግ መንግስት አሁን ያለበት ሁኔታ ስናይ የህዝቡን ድምፅ ሰምቶ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ዓቅምና ተፈጥሮ እንደሌለው ራሱም ጭምር እያመነ ነው። ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት የስርዓቱን መሪዎች ብቃትና ራእይ ማነስ ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው የግል ጥቅማቸውን በማሳደድ ላይ የተጠመዱ ስለሆኑ ስለሀገርና የህዝብ ችግር ለማሰብ ጉዳያቸውም አይደለም። በአሁኑ ጊዜ ሓላፊነት የሚሰማው የመንግስት አካል ማን ነው ብለህ ለማወቅ አስቸጋሪ የሆነበት ጊዜ ነው ያለው። የመንግስት አካላትን ስንመለከት ሁሉም የየራሱ ቡድናዊና ቤተሰባዊ መንግስት በመመስረት የየግሉን አጀንዳ ይዞ የሚሯሯጥ ነው። ህዝቡም በመንግስቱ ላይ አሜኔታ በማጣቱ በራሱ መንገድ መሄድ ጀምሯል። ሰሞኑን የኢሕአዴግ ፓሊት ቢሮ ያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባም ገና ከጅምሩ ውጤት አልባ እንደሆነ ያወጣውን መግለጫና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ራሳቸውም ለጋዜጠኞች የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያመላክታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነገሩን መርዶ ኢሕአዴግ አሁንም በራሱ ጎጆ አጥር ግቢ ውስጥ እየተሽከረከረ እንደሚቀጥል ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገላለፅ መተካካት (ትራንስፎርመሽን) የሚሉትም ትርጉሙ አረጌውን ስርዓት ፓሊሱና ርእዮተ ዓለም እንዳለ ሆኖ ነባር የኢሕአዴግ አባልን በአዲስ የኢሕአዴግ አባል መተካት ማለት ነው። ስለዚህ የመልክ መቀያየር እንጂ የባህርይና ያስተሳሰብ ለውጥ አልተደረገም ሁለቱም ያው ናቸው። ይህ ዓይነቱ ንግግርና መግለጫ ደግሞ ላለፉት ሃያ ዓመታት የህዝቡን ጆሮ ያደነቆረና የሰለቸ አነጋገር ነው።

ኢሕአደግ እውነት ለለውጥ ቆርጦ የተነሳ ቢሆን ኖሮ የመርፌን ቀዳዳ ያህል የጠበበውን የፓለቲካ ምሕዳር በሩን በመክፈት በሀገራችን ጉዳይ ላይ እኛም ያገባናል የሚሉትን ተቃዋሚ የፓለቲካ ሐይሎችን ለማስተናገድና ለመሳተፍ የሚችሉበትን የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት ተግባራዊ ባደረገ ነበር። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የነገሩን ነገር ካለ አሁንም የህዝቡን ድምፅ ለማፈን ወታደራዊ ጡንቻቸው እንዲሚያጠናኩሩ ነው። ሌላው በፓሊት ቢሮው የወጣውን መግለጫ ያነበብነው የኢሕአዴግ መንግስትን የግለ መሪዎችን ጥቅም ማካበቻ አድርጎ መጠቀም የሰርዓቱን ዋነኛ አደጋ እንደሆነ ይጠቁማል። ይሁን እንጂ ሁሉም ባለስልጣን በየደረጃው በኪራይ ሰብሳቢነት ስኳር የተለከፈ ስለሆነ ማን በማን ላይ ደፍሮይዘምታል የሚል ጥያቄ ምልክት ነው። መንግስት እወስዳለሁ ያለውን እርምጃም ምናልባት ግምገማ በሚል ሰበብ ህዝቡን እርስ በርሱ ለማናከስና ትግሉን ለማቀዝቀዝ ወይም አንዳንድ ባለስልጣናትን ለመምታት ይጠቀሙበት ይሆናል እንጂ የተነሳውን አንገብጋቢና ስር የሰደደውን የህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ የሚመልስ አይሆንም። ሁሉንም በአንድ ድርጅት የበላይነት ሞኖፓላዊ አስተሳሰብ በተጠመቁ ግለ መሪዎች መካከል ሹም ሽር በማድረግና ወንበርን በመቀያየር የሚፈታ ችግር አይኖርም። የችግሩን መንሲኤ የግለ ሰቦችን ጉዳይ ሳይሆን የስርዓቱን መበስበስና አፋኝ ፓለሲያቸውን የወለደው ችግር ነው። ስለዚህ የችግሩን ምንጭ የሆነውን የስርዓቱን ፓሊሲ ለውጥ ሳይደረግ አንድ አምባ ገነን መሪን በማባረር በሌላ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያለውን አምባ ገነን መሪ ቢተካ ነገ ተመልሶ ወደ ሌብነት መግባቱ አይቀሬ ነው። ምክንያቱም ህዝቡን የስልጣን ባለቤትነቱን ሙሉ በመሉ ሳይረጋገጥ ማለት ነፃና ገለልተኛ የሆኑትን የፍትሕ: የዳኝነት: የዴሞክራሲና የምርጫ ተቋማት እስከሌሉ ድረስ ኪራይ ሰብሳቢነትንና የስርዓቱን መበላሸት መዋጋትና መቆጣጠር አይቻልም። የኢሕአዴግ ስርዓት ባህርይም ካለፈው ልምዱን ስንመለከት ስር ነቀል የሆነ የተሃደድሶና የፓለሲ ለውጥ(reform) ማድረግ ማለት ራስህን በራስህ የመግደል (suicidal) እርምጃ አድርጎ ስለሚያየው ከእባብ እንቁላል እርግብ ይወለዳል ብለን አንጠብቅም።

ውድ ኢትዮጵያውያን እኛ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች ይህንን የአቋም መግለጫ እንድናወጣ የተገደድንበት ዋናው ምክንያት በሀገራችን ውስጥ የተከሰተውን የፓለቲካ ቀውስና በወገኖቻችን ላይ እያስከተለ ያለውን የህይወትና የንብረት መጥፋት አደገኛ አዝማሚያን በሚመለከት ያለንን ስጋት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም ለሚኖረው መላ ወገናችን መልእክታችንን ለማስተላለፍ ነው።

   1. ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብታችን ይከበር!! ድምፃችን ይሰማ!! በማለት ሕገ መንግስቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው በሰላም አደባባይ ወጥተው አቤት ስላሉ ብቻ ወታደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸው በየጎዳናው የወደቁትን ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልፃለን። የከፈላችሁትን አኩሪ መስዋእትነት ለፍትሕ፣ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ የተከፈለ ዋጋ ነውና ታሪካችሁን ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል። በዚሁ አጋጣሚም ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ለመላ ህዝባችን መፅናናትን እንመኛለን።

 

   2. ህዝቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ፍርሓትን ሰብሮ አደባባይ በመውጣት ለመብቱ እያደረገ ያለው የሞት ሽረት ትግል መበረታታ አለበት ብለን ስለምናምን ድጋፋችንና የትግል አጋርነታችንን እንገልፃለን። ለወደፊትም ከዘር ጥላቻ፣ ከቂም በቀልና ከጠባብ አስተሳሰብ በፀዳ መልኩ፣ ሀገርንና የ90 ሚሊዮን ህዝብን ጉዳይ ማእከል ያደረገ፣ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊነትንና እውነተኛ ህዝባዊ አላማን መሰረት አድርጎ በሚካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ከህዝባችንና ከታጋይ ወገኖቻችንን ጎን በመሰለፍ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁነታችንን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

 

   3. በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መንግስት ለተፈጠረው ችግር መንሲኤና ተጠያቂ ራሱ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥተው የፍትሕ ጥያቄ ያቀረቡትን ዜጎች ድምፃቸውን በማፈን እየወሰደ ያለው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፣ የማሰርና የመመንጠር እርምጃ አጥብቀን እናወገዛለን። ድርጊቱንም በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚሁ ሳቢያ እስር ቤት የታጎሩትን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ እንጠይቃለን። ለተፈጠረው ችግርና ለተፈፀመው ግድያም በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በደለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

 

   4. መንግስት ለሀገርና ለህዝብ ድህንነት ሲባልና ለራሱ ህልውናም ሲል የሰላም እጁን በመዘርጋት የህዝቡን ድምፅ የሚስተናገድበት ነፃና ገለልተኛ የፍትሕና የዴሞክራሲ ተቋማትን በመዘርጋት፣ ህዝቡ በሕገ መንግስቱ የሰፈሩትን ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመጠቀም መፃኢ ዕድሉን የሚወስንበት ነፃ የምርጫ ስርዓትን በማቋቋም: የፓለቲካ ምሕዳሩን ከላይ እስከ ታች በማስፋት: በአጠቃላይ ኢሕአዴግንም ጨምሮ የለውጡን አጋር የሚሆንበትን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለማደረግ የሚያስችል የተመቻቸ የፓለቲካ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈጥር አጥበቀን እንጠይቃለን።

 

   5. መከላኪያ ሰራዊት የገባኸው ቃል ኪዳን ከሁሉም ገለልተኛና ነፃ ሆነህ ለሕገ መንግስቱ፣ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝብ ልዕልና ታማኝና ዘብ በመሆን የዜጎችን ድህንነት በእኩል ለመጠበቅ ነው። የሚከፈልህን ደመወዝም ሆነ የታጠቅከውን መሳሪያ ከጥቂት መሪዎች ኪስ የምታገኘው ጉርሻና ስጦታ ሳይሆን የጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ነው። ስለሆነም አንተ ከህዝብ አብራክ የወጣኸው የኢትዮጵያ ወታደር እየከሰመ በመሄድ ላይ የሚገኘውን አምባ ገነን ስርዓትና በተለይም በፍቅረ ንዋይ ታውረው ሐቁን ማየት የሳናቸውና መንገዱን ጠፍቶባቸው በመደነባበር ላይ የሚገኙትን መሪዎች ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል አፈ ሙዙን በጭቁኑ ህዝብ ላይ ከማነጣጠር ይልቅ ከህዝቡ ጋር ወግነህ የለውጡን አጋር እንድትሆን ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

 

   6. ተቃዋሚ የፓለቲካ ሐይሎች፣ ሲቢክ ማሕበረ ሰቦች፣ ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶችና የሚዲያ ባለሙያዎች በሙሉ!! በመካከላችን በብዙ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ መለስተኛ ልዩነት መኖር ባህሪያዊ ነው። ነገር ግን በእናት ሀገርና በህዝብ ህልውናና ደህንነት ላይ ግን ልዩነት ሊኖረን ፍፁም አይገባም። ስለሆነም ጥቃቅን ልዩነቶቻችንና ቅራኔዎችን ወደጎን በመተው ከሁሉም በላይ ”የሀገርንና የህዝብን ደህንነትና አንድነት ይቅደም “ በሚል የሀገር አድን የጋራ መፈክር ዙሪያ ተሰባስበን የአባቶቻችንን ወኔና ጀግንነት ዳግም በማደስ ለእናት ሀገራችን ትንሳኤ አብረን ዘብ እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

   7. መንግስትንና ህዝብን በውል ለይቶ ማየት ያቃታቸውን ቡድኖችና ግለ መሪዎች በጉዳዩ ላይ ምንም በሌለበትና ለራሱ በህወሓትና በሻዕቢያ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ በባርነት ስር እየማቀቀ የሚገኘውን የትግራይ ህዝብ ከወንለኛ መሪዎች ጋር ደምረው በጀምላ በመጥላት የህዝቡን ስሜትንና ክብርን የሚነካ ተግባር ሲፈፅሙ ይገኛሉ። በመሆኑም ለረጅም ዘመናት አብሮ ተፋቅሮና ተዋልዶ በኖረው ወንድማማች ህዝብ መካከል ሆን ተብሎ በዘር ጥላቻ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በመገፋፋት አላስፈላጊ ግጭትና የእርስ በርስ መናቆር ለመፍጠር የሚደረገውን ማንኛውም ሕገ ወጥ ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን። አንዳንድ የመንግስት አካላትም ሆኑ ሌሎች ግለ ሰቦችና ቡድኖች ወጣቱን ትውልድ የሀገርንንና የወገንን ፍቅር ተላብሶ በመቻቻል አብሮ መኖርን ከማስተማር ይልቅ ጥላቻን በመስበክ በገዛ ወገኑ ላይ እንዲዘምት ከማድረግ እንዲታቀቡ አበክረን እንጠይቃለን።

 

   8. የኢትዮጵያ ህዝብ! ባንተ ላይ ነጋ ጠባ ሲካሄዱት የቆዩትን አደናጋሪና ከፋፋይ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በምንም ሳትበገር፣ መንግስታትና መሪዎች አላፊ ሀገርና ህዝብ ግን ነባሪ መሆናቸውን በፅናት በማመን ላሳየኸው ትዕግስትን: ጨዋነትንና ሃላፊነትን የተሞላበት አኩሪ ተግባርና ባህል ምስጋናችንንና አንድናቆታችንን ስንገልፅ ታላቅ ኩራት ይሰማናል። ስለሆነም ዛሬም እንደትላንቱ ዓለም ያደነቀውን የአትንኩኝ ባይነትህን: እንግዳ ተቀባይ ተምሳሌነትህንና የአንድነት ቃል ኪዳንህን ጠብቀህ ከስርዓቱ ጭቆናና አፈና ለመላቀቅ በምታደርገው ህዝባዊ ተጋድሎ ላይ እኛም እስከመጨረሻ ከጎንህ የምንቆም መሆናችንን በልበ ሙሉነት ለመግለፅ እንወዳለን።

እግዚአብሄር የሀገራችንን ሰላምና አንድነት ይጠብቅ

ምንጭ: Email

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending