Connect with us

Articles

እውነተኛ ገጠመኝ – ስርዓት አልባ የሆኑ ስርዓት አስከባሪዎቻችንን ማን ስርዓት ያስይዝልን??

Published

on

Artist Azeb Worku

Artist Azeb Worku

ቦታው ኤየርፖርት ፓርኪንግ (የሐገር ውስጥ በረራ)
ጊዜው ጠዋት 4 ሰዓት አካባቢ
እኔ እና ወንድሜ በጠዋት እንግዳ ለመቀበል ኤየርፖርት ተገኝተናል ከብዙ ሠዓታት ጥበቃ በኋላ እንግዳችን መጣችና ተቀብለናት ከፓርኪንግ ስንወጣ
አንድ መሳሪያ የታጠቀ ፌደራል ፖሊስ – ( በሐይለኛ ቁጣ እየደነፋ) አቁሙ
መኪናችንን አቆምን
ፌደራሉ – (በማመነጨቅ ) መንጃ ፈቃድህን አምጣ
ወንድሜ – ምን አጠፋሁ?
ፌደራሉ – ደርበህ ነው የቆምከው
ወንድሜ እረ እኔ በጭራሽ ከፓርኪንግ ነው የምወጣው
ፌደራሉ – አትለፍልፍ መንጃ ፈቃድህን አምጣ
ወንድሜ ሰጠው
ፌደራሉ – በል ሂድ ከዚህ
ወንድሜ – መንጃ ፍቃዴስ?
ፌደራሉ -( ደሜን አታፍላው በሚል ስሜቴ ) አንተ ሰውዬ አታነግረኝ ሂድ ብዬሃለሁ ሂድ መንገድ አትዝጋ
እኔ – (መስኮት ከፍቼ )መንጃ ፍቃዱስ?
ፌደራሉ – ምን አባሽ አገባሽ አንቺ? አንቺ ደግሞ ምን ቤት ነሽ? …………. ( ይሄ በነጥብ በነጥብ ያለፍኩት አጸያፊ ስድቡን ነው)
እኔ,- ( በንዴት )ለምን ትሰድበኛለህ ?
ፌደራሉ – ምን ታመጫለሽ ሂጅ ጥፊ ከዚህ
ፌደራሉ – መንጃ ፍቃዱን ይዞት ሄደ
አጠገቡ የነበረ አንድ ሰው ሊያግባባን ሞከረ፡፡ ስድባችንን ውጠን ትንሽ አስጨብጠን መንጃ ፍቃዳችንን ተቀብለን እንድንሄድ መከረን፡፡ አናደርገውም ትራፊክ ይዘን እንመጣለን አልን ቦሌ አደባባዩ ጋር ላገኘነው ትራፊክ ፖሊስ ሰላምታ ሰጥተን ጉዳያችንን አስረዳን ትራፊኩን ጭነን ወደ ኤየርፖርት ተመለስን ፡፡
ትራፊኩ ፌዴራሉ ን ጠየቀ
ፌደራሉ – በሚኒባስ የተከለከለ ቦታ አቁሞ ሰው ጭኖ ሲወጣ ነበር ብሎ ለትራፊክ ፖሊሱ ተናገረ
ወንድሜ – ይሄ ታክሲ አይደለም የድርጅት መኪና ነው ይቹ እህቴ ናት አለ
እኔም – ተሳፋሪ አለመሆናችንን ለማረጋገጥ ከሆነ የኔን መታወቂያ እና የሱን መታወቂያ አመሳክር አልን
ፌደራሉ – ትራፊክ ይዘሽ የመጣሽው ትራፊክ የምፈራ መሰለሽ
ሰዎቹ – በሰላም መፍታት ስትችሉ አከረራችሁት
ፌደራሉ – (እየደነፋ እና ትራፊክ ፖሊሱ ላይ እያፈጠጠ) ቅጣው
ትራፊክ ፖሊስ – በምን ልቅጣው
ትንሽ በዕድሜ ጠና ያለ ፌደራል ከወጣቱ ፌደራል አጠገብ ቆሞ – ደርቦ በመቆም ብለህ ቅጣው (ይሄን ያለው ጠና ያለው ፌደራል በሰዓቱ በቦታውም አልነበረም)
እኔ -እኔን ያለ አግባብ ሰድበኸኛል ይቅርታ እንድትጠይቀኝ እፈልጋለሁ
ፌደራል – (በተደፈርኩ ስሜት እየደነፋ) ምን ?
እኔ – አንተ ስርዓቱን ልታስከብር ቆመህ ስርዓት በሌለው መንገድ አጸያፊ ስድብ ሰድበኸኛል
ፌደራል- (በትዕቢት) እና ምን ታመጫለሽ ?
እኔ – እሺ ስምህን ነገረኝ
ፌደራል – አልነግርም
እኔ- ስምህን መጠየቅ መብቴ ነው አንተም መንገር ግዴታህ ነው
ፌደራል – ( በማመናጨቅ )ስሙን አልነግርም አለኝ ብለሽ ክሰሺ
ሌላ ፌደራል ፍለጋ ሄድኩ ኤየርፖርት መግቢያ በር ላይ መገናኛ ሬድዮ የያዘ ፌደራል አገኘሁ፡፡
ፌደራሉ – ( ጉዳዩን አዳምጦ ) ሊሰድብሽ መብት የለውም፡፡ ስሙን መንገርም ግዴታው ነው ተመልሰሽ እራሱኑ ጠይቂው እኔን እዚህ ነገር ውስጥ አትክተቺኝ…..
ተመለስኩ ወደ ፌደራሉ
ፌደራሉ በታላቅ ትዕቢት ከሌላ ፌደራል ጋር ቆሞ ይመለከተኛል
እኔ – ቀረብ አልኩትና የኔ ወንድም የስራ ባልደረባህን አነጋግሬው ነበር ስምህን መንገር ግዴታህ እንደሆነ ነግሮኛል፡፡
አጠገቡ የቆመው በዕድሜ ጠና ያለው ፌደራል- ስሙን ቢነግርሽ ምን ልታደርጊ ነው ?
እኔ – ሰላማዊ ሰውን ያለአግባብ ስለሚሰድብ እና ስለሚያወርድ ልከሰው
ጠና ያለው ፌደራል – በቃ አልናገርም አለሽ እኮ (በመሳለቅ) ከፈለግሽ የኔን ስም ያዢ ኢንስፔክተር መልካሙ ጥሎኝ ሄደ …
እደነዚህ ዓይነት ስርዓቱን ሊጠብቁ እና ስርዓት እና ሕግ ሊያስከብሩ የሚቆሙ ለሕግ የማይገዙ ስርዓት አልባ ፖሊሶች ሕብረተሰቡን ሲሰድቡ ሲያዋርዱ እና ሲሰድቡ ሊያስጠብቁት የቆሙለትን ሰርዓት ማሰደባቸውን እና ማስወቀሳቸውን ልብ ይሉታል? መንግስትስ አታሰድቡኝ ግዴታችሁን ተወጡ የሰዉን መብት አክብሩ ማለት የለበትም? ሲያሰድቡት በዝምታ ይመለከታል?

Source: Azeb Worku

 

Continue Reading
61 Comments

61 Comments

 1. Anonymous

  August 6, 2015 at 9:26 am

  ቦታው ኤየርፖርት ፓርኪንግ (የሐገር ውስጥ በረራ)
  ጊዜው ጠዋት 4 ሰዓት አካባቢ
  እኔ እና ወንድሜ በጠዋት እንግዳ ለመቀበል ኤየርፖርት ተገኝተናል ከብዙ ሠዓታት ጥበቃ በኋላ እንግዳችን መጣችና ተቀብለናት ከፓርኪንግ ስንወጣ
  አንድ መሳሪያ የታጠቀ ፌደራል ፖሊስ – ( በሐይለኛ ቁጣ እየደነፋ) አቁሙ
  መኪናችንን አቆምን
  ፌደራሉ – (በማመነጨቅ ) መንጃ ፈቃድህን አምጣ
  ወንድሜ – ምን አጠፋሁ?
  ፌደራሉ – ደርበህ ነው የቆምከው
  ወንድሜ እረ እኔ በጭራሽ ከፓርኪንግ ነው የምወጣው
  ፌደራሉ – አትለፍልፍ መንጃ ፈቃድህን አምጣ
  ወንድሜ ሰጠው
  ፌደራሉ – በል ሂድ ከዚህ
  ወንድሜ – መንጃ ፍቃዴስ?
  ፌደራሉ -( ደሜን አታፍላው በሚል ስሜቴ ) አንተ ሰውዬ አታነግረኝ ሂድ ብዬሃለሁ ሂድ መንገድ አትዝጋ
  እኔ – (መስኮት ከፍቼ )መንጃ ፍቃዱስ?
  ፌደራሉ – ምን አባሽ አገባሽ አንቺ? አንቺ ደግሞ ምን ቤት ነሽ? …………. ( ይሄ በነጥብ በነጥብ ያለፍኩት አጸያፊ ስድቡን ነው)
  እኔ,- ( በንዴት )ለምን ትሰድበኛለህ ?
  ፌደራሉ – ምን ታመጫለሽ ሂጅ ጥፊ ከዚህ
  ፌደራሉ – መንጃ ፍቃዱን ይዞት ሄደ
  አጠገቡ የነበረ አንድ ሰው ሊያግባባን ሞከረ፡፡ ስድባችንን ውጠን ትንሽ አስጨብጠን መንጃ ፍቃዳችንን ተቀብለን እንድንሄድ መከረን፡፡ አናደርገውም ትራፊክ ይዘን እንመጣለን አልን ቦሌ አደባባዩ ጋር ላገኘነው ትራፊክ ፖሊስ ሰላምታ ሰጥተን ጉዳያችንን አስረዳን ትራፊኩን ጭነን ወደ ኤየርፖርት ተመለስን ፡፡
  ትራፊኩ ፌዴራሉ ን ጠየቀ
  ፌደራሉ – በሚኒባስ የተከለከለ ቦታ አቁሞ ሰው ጭኖ ሲወጣ ነበር ብሎ ለትራፊክ ፖሊሱ ተናገረ
  ወንድሜ – ይሄ ታክሲ አይደለም የድርጅት መኪና ነው ይቹ እህቴ ናት አለ
  እኔም – ተሳፋሪ አለመሆናችንን ለማረጋገጥ ከሆነ የኔን መታወቂያ እና የሱን መታወቂያ አመሳክር አልን
  ፌደራሉ – ትራፊክ ይዘሽ የመጣሽው ትራፊክ የምፈራ መሰለሽ
  ሰዎቹ – በሰላም መፍታት ስትችሉ አከረራችሁት
  ፌደራሉ – (እየደነፋ እና ትራፊክ ፖሊሱ ላይ እያፈጠጠ) ቅጣው
  ትራፊክ ፖሊስ – በምን ልቅጣው
  ትንሽ በዕድሜ ጠና ያለ ፌደራል ከወጣቱ ፌደራል አጠገብ ቆሞ – ደርቦ በመቆም ብለህ ቅጣው (ይሄን ያለው ጠና ያለው ፌደራል በሰዓቱ በቦታውም አልነበረም)
  እኔ -እኔን ያለ አግባብ ሰድበኸኛል ይቅርታ እንድትጠይቀኝ እፈልጋለሁ
  ፌደራል – (በተደፈርኩ ስሜት እየደነፋ) ምን ?
  እኔ – አንተ ስርዓቱን ልታስከብር ቆመህ ስርዓት በሌለው መንገድ አጸያፊ ስድብ ሰድበኸኛል
  ፌደራል- (በትዕቢት) እና ምን ታመጫለሽ ?
  እኔ – እሺ ስምህን ነገረኝ
  ፌደራል – አልነግርም
  እኔ- ስምህን መጠየቅ መብቴ ነው አንተም መንገር ግዴታህ ነው
  ፌደራል – ( በማመናጨቅ )ስሙን አልነግርም አለኝ ብለሽ ክሰሺ
  ሌላ ፌደራል ፍለጋ ሄድኩ ኤየርፖርት መግቢያ በር ላይ መገናኛ ሬድዮ የያዘ ፌደራል አገኘሁ፡፡
  ፌደራሉ – ( ጉዳዩን አዳምጦ ) ሊሰድብሽ መብት የለውም፡፡ ስሙን መንገርም ግዴታው ነው ተመልሰሽ እራሱኑ ጠይቂው እኔን እዚህ ነገር ውስጥ አትክተቺኝ…..
  ተመለስኩ ወደ ፌደራሉ
  ፌደራሉ በታላቅ ትዕቢት ከሌላ ፌደራል ጋር ቆሞ ይመለከተኛል
  እኔ – ቀረብ አልኩትና የኔ ወንድም የስራ ባልደረባህን አነጋግሬው ነበር ስምህን መንገር ግዴታህ እንደሆነ ነግሮኛል፡፡
  አጠገቡ የቆመው በዕድሜ ጠና ያለው ፌደራል- ስሙን ቢነግርሽ ምን ልታደርጊ ነው ?
  እኔ – ሰላማዊ ሰውን ያለአግባብ ስለሚሰድብ እና ስለሚያወርድ ልከሰው
  ጠና ያለው ፌደራል – በቃ አልናገርም አለሽ እኮ (በመሳለቅ) ከፈለግሽ የኔን ስም ያዢ ኢንስፔክተር መልካሙ ጥሎኝ ሄደ …
  እደነዚህ ዓይነት ስርዓቱን ሊጠብቁ እና ስርዓት እና ሕግ ሊያስከብሩ የሚቆሙ ለሕግ የማይገዙ ስርዓት አልባ ፖሊሶች ሕብረተሰቡን ሲሰድቡ ሲያዋርዱ እና ሲሰድቡ ሊያስጠብቁት የቆሙለትን ሰርዓት ማሰደባቸውን እና ማስወቀሳቸውን ልብ ይሉታል? መንግስትስ አታሰድቡኝ ግዴታችሁን ተወጡ የሰዉን መብት አክብሩ ማለት የለበትም? ሲያሰድቡት በዝምታ ይመለከታል?

 2. Anonymous

  September 25, 2014 at 11:25 am

  ?

 3. helen geta

  September 19, 2014 at 7:31 am

  ጊዜ የሰጠው ቅል ዲንጋይ ይሰብራል።

 4. Anonymous

  September 16, 2014 at 1:33 pm

  u are lucky not be boxed

 5. Ye Ambo Lj

  September 16, 2014 at 1:00 pm

  Bergt beandu tifat hulunm mewenjel agbab ayidelem, honom gn yatefaw akal ke ewuket netsa bemehonu lnferdibet anichilm ina atfrejibet, yane ihit ayzosh yenetsanet ken eruq aydelem. tesfa atkurechi

 6. Anonymous

  September 16, 2014 at 9:31 am

  belelaw hager yeswen kebr yemineka police ayedelem priminister yekesesal ezihe lela dula

 7. Anonymous

  September 16, 2014 at 9:24 am

  በሀቅ በቅነነትና በታማኝነት ህገራቸውንና ህዘቡን ለሚያገለግሉ የፊደራል ፓሊስ አባላት kerstose yeserachewn yestachew

 8. tekuresew bacha

  September 16, 2014 at 9:18 am

  wochewe gude endezihe yale neger kezehe befite getemoshe ayawekeme?eEthiopia weste eyenorshe edelegna neshe eheta kzeheme belaye ale betekuse mene yebalale aye woyane!

 9. Anonymous

  September 15, 2014 at 8:21 pm

  Hulunem mewengel sayhon abezanawen arporte akababe Yalu hege asekebarewoch teru senemegbare yelachewem melkamen tehuto ALU yemesema noro ferana gelebwe beley melkame new mengsete yhzben astyayeten adamach yenur yewetaw kebrtesebu new yemeygeleglewem hzben new sedate yakber 10xxx

 10. merhawi

  September 15, 2014 at 6:14 pm

  beand sew yetensa le hulum and atargi le hulum geze alew metages betam arif nw

 11. biniyam

  September 15, 2014 at 2:31 pm

  esek 6 sele temaru newe
  ateferajebachewe

 12. Anonymous

  September 15, 2014 at 1:43 pm

  ውድ የኢትዮፐያ ለጆች
  አንድ ፖሊስ ሲያጠፋ ሁሉንም በጅምላ መወንጀል ነውር ነው
  አብዛኛው ፖሊስ ቀን ከሌት የህገሩንና የህዘቡን ሰላም ለማረጋገጥ መስዋት እየከፈለ ነው
  ሆኖም እናንተ እየሰጣችሁት ያለው ሚዛናዊነት የጎደለው አስተያየት ከሱ የማትሻሉ መሆናችሁን ይመሰክራል
  በስራ ላይ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ ስህተት ይፈዕማል
  ምናልባት ከአስተያየት አቅራቢዎች ውሰጥ አንዳንዶቻችሁ—-ስርአት አልባ ተማሪ/መምህር/ልጅ/ሚስት/ባል /የታክሲ ረዳት/የመንግስት/የግል ሰራተኛ/ጎረቤት/ነጋዴ/ጋዜጠኛ/ዘበኛ/ስፖርተኛ/የህክምና ባለሞያ/አርቲስት/ ወዘተ አጋጥማችሁይሆናል
  ቁምነገሩ ለማረምና ለማስተካከል መጣር መታገል እንጂ በስድብ የተለወጠ ሀገር የለም
  ክብርና ሞገስ ሀገራቸውን በሀቅ በቅነነትና በታማኝነት ህገራቸውንና ህዘቡን ለሚያገለግሉ የፊደራል ፓሊስ አባላት

 13. Anonymous

  September 15, 2014 at 1:25 pm

  ውድ የኢትዮፐያ ለጆች
  አንድ ፖሊስ ሲያጠፋ ሁሉንም በጅምላ መወንጀል ነውር ነው
  አብዛኛው ፖሊስ ቀን ከሌት የህገሩንና የህዘቡን ሰላም ለማረጋገጥ መስዋት እየከፈለ ነው
  ሆኖም እናንተ እየሰጣችሁት ያለው ሚዛናዊነት የጎደለው አስተያየት ከሱ የማትሻሉ መሆናችሁን ይመሰክራል
  በስራ ላይ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ ስህተት ይፈዕማል
  ምናልባት ከአስተያየት አቅራቢዎች ውሰጥ አንዳንዶቻችሁ—-ስርአት አልባ ተማሪ/መምህር/ልጅ/ሚስት/ባል /የታክሲ ረዳት/የመንግስት/የግል ሰራተኛ/ጎረቤት/ነጋዴ/ጋዜጠኛ/ዘበኛ/ስፖርተኛ/የህክምና ባለሞያ/አርቲስት/ ወዘተ አጋጥማችሁይሆናል
  ቁምነገሩ ለማረምና ለማስተካከል መጣር መታገል እንጂ በስድብ የተለወጠ ሀገር የለም
  ክብርና ሞገስ ሀገራቸውን በሀቅ በቅነነትና በታማኝነት ህገራቸውንና ህዘቡን ለሚያገለግሉ የፊደራል ፓሊስ አባላት

 14. Anonymous

  September 15, 2014 at 1:13 pm

  ውድ የኢትዮፐያ ልጆች
  የተባለው እውነት ከሆነ የተደረገው ስህተት በመሆኑ መታረም አለበት
  ሆኖም አንድ ፖሊስ ሲያጠፋ ሁሉንም በጅምላ መወንጀል ተገቢ አይደለም
  አብዛኛው ፖሊስ ቀን ከሌት የህገሩንና የህዘቡን ሰላም ለማረጋገጥ መስዋት እየከፈለ ነው
  ሆኖም እናንተ እየሰጣችሁት ያለው ሚዛናዊነት የጎደለው አስተያየት ግን ከሱ የማትሻሉ ለመሆናችሁ በቂ ምስክር ነው
  በስራ ላይ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ ስህተት ይፈዕማል
  ምናልባት ከአስተያየት አቅራቢዎች ውሰጥ አንዳንዶቻችሁ—-ስርአት አልባ ተማሪ/መምህር/ልጅ/ሚስት/ባል /የታክሲ ረዳት/የመንግስት/የግል ሰራተኛ/ጎረቤት/ነጋዴ/ጋዜጠኛ/ዘበኛ/ስፖርተኛ/የህክምና ባለሞያ/አርቲስት/ ወዘተ ትሆኑ ይሆናል ወይም አጋጥማችሁይሆናል
  ቁምነገሩ ለማረምና ለማስተካከል መጣር መታገል እንጂ በስድብ ለውጥ አይመጣም
  ክብርና ሞገስ በሀቅ በቅነነትና በታማኝነት ህገራቸውንና ህዘቡን በማገልገል ላይ ለሚገኙ የፊደራል ፓሊስ አባላት

 15. Anonymous

  September 15, 2014 at 1:01 pm

  ውድ የኢትዮፐያ ለጆች
  አንድ ፖሊስ ሲያጠፋ ሁሉንም በጅምላ መወንጀል ነውር ነው
  አብዛኛው ፖሊስ ቀን ከሌት የህገሩንና የህዘቡን ሰላም ለማረጋገጥ መስዋት እየከፈለ ነው
  ሆኖም እናንተ እየሰጣችሁት ያለው ሚዛናዊነት የጎደለው አስተያየት ከሱ የማትሻሉ መሆናችሁን ይመሰክራል
  በስራ ላይ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ ስህተት ይፈዕማል
  ምናልባት ከአስተያየት አቅራቢዎች ውሰጥ አንዳንዶቻችሁ—-ስርአት አልባ ተማሪ/መምህር/ልጅ/ሚስት/ባል /የታክሲ ረዳት/የመንግስት/የግል ሰራተኛ/ጎረቤት/ነጋዴ/ጋዜጠኛ/ዘበኛ/ስፖርተኛ/የህክምና ባለሞያ/አርቲስት/ ወዘተ አጋጥማችሁይሆናል
  ቁምነገሩ ለማረምና ለማስተካከል መጣር መታገል እንጂ በስድብ የተለወጠ ሀገር የለም
  ክብርና ሞገስ ሀገራቸውን በሀቅ በቅነነትና በታማኝነት ህገራቸውንና ህዘቡን ለሚያገለግሉ የፊደራል ፓሊስ አባላት

 16. Anonymous

  September 15, 2014 at 11:56 am

  እኔ አንደማስበው ከሆነ የአየር መንገድ ፖሊሶች በሰው የሚቀኑና በህየይወታቸው ተደስተው የማያውቁ ስለህግ ስለህዝብ ግዴሌሾች ከመሆናቸውም በላይ የሰራዊት ባህሪ የሌላቸው እራሳቸው አሸባሪዎች መሳሪያ ታጥቀው ሕዝብን የሚያስፈራሩ ከአነ አልሻባብ ጋር ተባባሪ የሆኑ በዘረፋና በድብደባ የህዝብን ንብረትና አካል የሚያጎድሉ የተደራጁ አሸባሪዎች ናቸው እነዚህ ሰዎች የህዝብን ምርጫና ፈላጎት እንዲሁም ህገ መንግስቱን በተግባር መተርጎም ሰይሆን ዋናው አላማቸው አየዘረፉና አየደበደቡ እንዲኖሩ በፓርላማ የተፈቀደላቸው እሰኪመስል ድረስ ደረስ እንደዚህ አይነት ተደጋጋሚ በደል በደል ሲፈፀፅሙ ይሀው 10 ረጅም አመት አስቆጥረናል ከመንግስት በላይ ከሆኑም እንወቀውና ለነሱ አንገዛ መንግስት አኔ አለሁ የሚል ከሆነም ይቆጣጠራቸውና ህግና ስርአት የዜጎች መብት የሚከበርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሃላፊነት አለበት ይህን በደል ከፈጣሪ በታች መንግስት ሊያስታግስ ቢችል መንግስትና ህዝብ በመልካም አሰስተደደር ችግር የሚነሱ ጥያቀዎችን በአግባቡ መመለስ ከመቻሉም በላይ ህዝቡ በህግና በመንግስት ላይ የሚኖረውን አመኔታ ከፍ እንዲል ያደርገዋል ህዝብም የሚፈልገው ይህንኑ ነው ሁሉም ዜጋ እኩል መሆንን ሰላምን ፍትህን ማግኘት ከሁሉም በላይ ይናፍቃልና የዚህን ችግር መፍትሔ የሚፈልግና ለመፍታት ጥረት የሚያደርጉ ዚጎችንና አከላትን ግን በቅድሚያ አመሰግናለሁ አረ በህግ አረ በህ !!! የህግ አስከባሪ አካላት ህግን ማክበር ይማሩ!!!!! ዜግነታችን በህግ ይከበርልን ህግ ከተከበረ ሁሉም ነገር ይከበራል ፡፡

 17. Anonymous

  September 15, 2014 at 11:30 am

  እረ በዚህም መገላገልሽ ጥሩ ነው እነሱ እኮ ከፈለጉ …………………… ለማንኛውም ሰሚ ባይኖርም መብትሽን ለማስገበር ያደረግሺውን ጥረት ሳላደንቅ አላልፍም

 18. ተመስገን

  September 15, 2014 at 10:55 am

  ተመስገን አልተኮሰም? አንቺም እንደው አበዛሺው አርፈሽ ስድብሽን ተከናንበሽ አትሄጂም?

 19. Anonymous

  September 15, 2014 at 9:35 am

  ewnat man hi yebalelen ?????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????

 20. Anonymous

  September 15, 2014 at 9:33 am

 21. TEKLE

  September 15, 2014 at 8:50 am

  IT IS SOO GOOD

 22. ye fitche liji

  September 15, 2014 at 7:21 am

  weyi gud! beteleyima gemed afochu ager yenesu bicha new yememesilschew . daru yemanew ?

 23. Anonymous

  September 15, 2014 at 6:49 am

  sirachew yih new higune meche yawukutal, manis asitemiruachew, endiyawum endiyawukut ayifekedim

 24. abduman

  September 15, 2014 at 6:48 am

  i appreciate your struggle for your right

 25. Dagne

  September 15, 2014 at 6:39 am

  Anchi Addis honesh new enji ene bebekule hule yemsedebewna yemwaredu bendezeh aynet leba yemengist sereat askebariwoch new. yemgermew neger esu aydelem setekesh tifategna yemtbayew enesu sayhonu anchi nesh. ya malet men malet new yehen sera yemiserut tederajtew mehonu chigrun yekefa yadergewal

 26. dejan

  September 15, 2014 at 6:34 am

  Aziti, zare new ende yenesu bilgina? Anchi zare silagatemesh yihonal. Inde abatachew yebesebesu nachew.

 27. mahlet

  September 15, 2014 at 6:07 am

  ስርዓት አልባ የሆኑ ስርዓት አስከባሪዎቻችንን ማን ስርዓት ያስይዝልን?
  Ande ken be temeherete bate menegede laye eyehadeku ande federal police enede melakefe belo anageregn alegn zoreme beye salayewu menegedane keteleku salanagerewu bemehada yetenadedewu police denegete mobile tedewolelegnena anesecha sanagere ejie laye wodeke ………. keza police mene beyaderege tiru newu,yewodeke mobile setanesa agegnehuwate belo kesesegn enedagatamie tele akababie selenebere seleke kuterane tenagera yena enedehone aseregageche hadekugne…beka be shenefete tereteche zem aleku ena zemenu yenesu newu men yederegale….

 28. elizabeth

  September 15, 2014 at 5:31 am

  ሁልጊዜ ውስጤ የሚያዝንበትን ነገር ስላነሳሽ ጌታ ይባርክሽ፡፡ በየመንገድ ላይ በያዙት ዱላ የሚደባደቡትን ፖሊሶች ሳይ ህገመንግሥቱን ያቁታልወይ እላለሁ፡፡ አንድ ቀን ልጆቼን ይዤ መንገድ ስሄድ አንድ ወጣት ልጅን ፖሊሶች ይዘው ምን እንዳደረገ ባላውቅም ይዘውት እየሄዱ ሳለ ምን አጥፍቼ ነው እያለ ሲጠይቅ በያዙት ዱላ ያለሀዘኔታ እየተፈራረቁ ሲመቱት አይተው ማሚ ለምን ይመቱታል ቆይ ለሲቪክስ አስተማሪ ነው የምነግረው ትክክል አይደሉም አኮ ሲሊ እኔም ተዋቸው እነሱ ሲቪክስ ስላልተማሩ ነው አልኩ፡፡ ስለትግልሽ እስከተወሰነ ርቀት መጓዝሽ አስደስቶኛል፡፡ ፖሊሶች ሲቀጠሩ መጀመሪያ ህገመንግሥቱን በትክክል እንዲረዱት ቢደረግ የሚሰሙን ከሆነ፡፡

 29. Anonymous

  September 14, 2014 at 9:30 pm

  yalderesew gilgel yawkal alu ! they have a big complex they don’t respct peope.
  you are not the only one victim it happend to many people !!!!!! stupid mind never learn how to respect people

 30. Anonymous

  September 14, 2014 at 7:05 pm

  ዋናው ጉዳይ የቦሌ የኤርፖርት ፖሊሰዎች ከቢጫ ታክሲዎች ጋር የጥቅም ግኑኝነት ስላላቸው በሚኒባስ እና በሰማያዊ ታክሲዎች ላይ ከፍተኛ በደል አያደረሱ ነው

 31. Anonymous

  September 14, 2014 at 5:45 pm

  ለብቻው በጫካ ውስጥ የኖረ በምን የሰው ክብር ያውቃል .

 32. tilahun

  September 14, 2014 at 4:35 pm

  Chanalachu temechtognal
  betlye sreat askebary teblo
  sreat yamtisuten lemn
  endamnkes …?

 33. Anonymous

  September 14, 2014 at 4:08 pm

  Fana pm anterasegh yesu buchla mehonigh alkerem dedeb

 34. Dereje Mengesha

  September 14, 2014 at 4:01 pm

  Federalochu serat aleba aydelum seratu rasu yefeqedelachiwun new yemiyadergut ke manegnawum hig belay nachewuna yanen mekad aychalem eskemegdel deres be netsanet mebet alachew ena yehe ye weyane hig alba wegentegna serat eskalteqeyere ders federalau endalesh yene ehet yetem betheji minim atamechim beqa this is the nacked truth on the Ethiopian soil .

 35. Yared

  September 14, 2014 at 1:59 pm

  U tell us only ur story.I do not belive u.

 36. yanit moges

  September 14, 2014 at 1:50 pm

  ene mlew seltan yaleagbab metekem endemiyasketa lengerew endae

 37. Anonymous

  September 14, 2014 at 1:29 pm

  ይሄ መሳደብ ትንሹ ስተታቸው ነው እኔ ባለውበት አካባቢ በየቀኑ ማለት ይቻላል በተለያየ ምክንያት ሰውን ሲደበድቡ ነው ሚውሉት ሰውም ስለለመደው መብታቸው አድርጎ ማሰብ ጀምሮአል ለምን ብትሉ የተትመም ብትሄዱ ሌላ ዱላ ስለሚሆን……………………………………………………………………………………………………..

  ሶሎ ከመርካቶ

 38. Anonymous

  September 14, 2014 at 12:35 pm

  Mibtcn.makbr.ymyak.mingstnw.yaln.

 39. Anonymous

  September 14, 2014 at 10:47 am

  yabsachal

 40. melaku

  September 14, 2014 at 9:57 am

  betam yasaznal endih aynetun hizbna mengist yemiarariku hig askebari bay wenjelognochin mengist bezmta malef yelebetm

 41. Anonymous

  September 14, 2014 at 9:34 am

  it resut from the political moral of the executive body!

 42. Anonymous

  September 14, 2014 at 9:24 am

  እሷም ስራዓቱን ለማስወገድ የበኩላን ትወጣ የሳ አንድ ቀን ሌሎች ሁለግዜ የሚበደሉ አሉ

 43. Anonymous

  September 14, 2014 at 9:23 am

  mengest sigemer maseb yemichelewen police meche endihe ayenet bota yemedebal yetemare federal yelemeeko

 44. Anonymous

  September 14, 2014 at 7:46 am

  aye KEBRARAW chinkilat ena hod tekeyayerebih ende? ayzoh tinish gize new bizuhanu yemikeberebet gize yemetal.. ayzosh

 45. yasmina

  September 14, 2014 at 7:45 am

  አገሬ ኢትዩጵያ የመሀይች መቀለጃ ሆና መቅረትዋ ቢያሳዝንም ምንም ማድረግ አለመቻላችን ይቆጨኛል እጆችዋ ሁሌም ወደፈጣሪ መዘርጋትዋ ግን አይቀርም ሠላም ፍቅር አንድነት ለዘላለም አሜን

 46. Anonymous

  September 14, 2014 at 7:12 am

  Mawoeke yegolehale wodaje!!!!!

 47. Anonymous

  September 14, 2014 at 7:01 am

  Bettam new yemgermut ጡንቻ ራሶች

 48. Genet

  September 14, 2014 at 6:44 am

  Getawan yetemamanech Beg Jeratowan Deji Tasaderalech yelale yageray sew Ena ehetya sewwyawe eko kemngesetoo telkobeshe new enjie endhe yeleb leb balbekwe Nberr.Mengesetin yemewekelu yetebaluit Dureya sewoch mehonachwein Gena Zaraya new Yawekeshewe meselegh enjie Alem yawekachwe nachwe..Sedeb yeseletenubet Wanawe serachwe new.kkkkkkkk

 49. Anonymous

  September 14, 2014 at 6:14 am

  Ena mefthew zim malet new? Fana pm weregna.

 50. Anonymous

  September 14, 2014 at 6:12 am

  Mesged neberebat? Maser mefthe new bileh endet tasbaleh? Doma.

 51. fana pm

  September 14, 2014 at 6:00 am

  Ere bakish weregna ena mengest yenageral enji beye betachew eyehede mesdeb alebet abezashew betam

 52. fana pm

  September 14, 2014 at 5:58 am

  Ere bakish weregna ena mengest yenageral enki beye betachew eyehede mesdeb alebet abezashew betam

 53. dani

  September 14, 2014 at 5:55 am

  yasazena, serat alebeghenet

 54. Kala

  September 14, 2014 at 4:45 am

  Eth. wyne Menengste edmelikachine
  Ysdfrnale Ayhoisse ehite afese aydlme?

 55. Anonymous

  September 14, 2014 at 4:34 am

  America lezegochwa respect alate ke police yebelete ezi hager gen manem lemanem respect yelewm so ShAmE.

 56. Kebraraw

  September 14, 2014 at 3:51 am

  Negeregna besratu atanagrutm kenante belay yetemare yale aymeslachihum asmesay film seri copy right eyeserash demo gurashn tnefialesh ende

 57. Anonymous

  September 14, 2014 at 3:08 am

  የነሱ አይነት ናቸው መሪዎችም የትም ብትሔጂ መፍትሄ አታገኚም

 58. milli n.zenebe

  September 14, 2014 at 2:06 am

  shame on weyane lenegeru shame yet yakalu

 59. Anonymous

  September 14, 2014 at 1:39 am

  Wow yemiyastela wutet

 60. kasa

  September 14, 2014 at 1:28 am

  if I were a police and i would be arrested you. cos you did not respect the officer.

 61. Gedle

  September 13, 2014 at 11:59 pm

  You should contact someone in the higher up. You should have also recorded the conversation. I wouldn’t even confront such an idiot. He could even be mentally ill. They no t only do give the government a bad image but it also shows inefficiency and administrative problems.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending