Connect with us

Articles

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ

Published

on

Hailemariam-and-Dr.Tedros

Hailemariam-and-Dr.Tedros

ከያሬድ ኃይለማርያም
ሰኔ 16፣ 2007 ዓ.ም.
ከብራስልስ

‘የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል’ አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም “ልማታዊ” በሚል ካባ የተከናነበውን የለየለት አንባገነናዊነት ሙሉ ድጋፋቸውን እየሰጡ ለመሆኑ የኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ እቅድ ጨምሮ በርካታ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡ ከምርጫው በፊትም ሆነ ከተጠናቀቀ በኋላ የአውሮፓ ኅብረትና የአሜሪካን መንግስት ያሳዩትም ድጋፍ የእዚሁ መገለጫ ነው፡፡ በአፋኝ አገዛዝ ውስጥ ላለ ሕዝብ ዲሞክራሲን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ ፍትሕን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ድጋፍ ልክ ለተራበ ሕዝብ ስንዴና ዘይትን እንደመርዳት ቀላል አይደለም፡፡ እህል ተርፏቸው ወደ ባሕር የሚጨምሩ አገሮች የተራበ ሲያገኙ የተረፋቸውን መወርወራቸው አንድም እርዳታ በመስጠትና ለጋሽ በመሆን የሚገኝውን የመንፈስ እርካታና በዋነኝነት ደግሞ የተጠኑ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትርፎችም ኢላማ ያደረገ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ላለፉት አስርት አመታት በርካታ የአፍሪቃ አገራት፤ የኛዋ አገር ደግሞ በግናባር ቀደምነትነት የዚህ የእህልና የገንዘብ ድጎማ ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች፡፡ በዚህ የቁስ እርዳታ ማን እንዳተረፈ በጥልቅ መመርመር የግድ ይላል፡፡ በእርግጠኝነት ግን መናገር የሚቻለው አገርንና ሕዝብን ለውርደት የዳረገና ክፉ የታሪክ ጠባሳንም የተወ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዘንድሮ ስንዴና ዘይት የሚላክለት ድሃ ሕዝብ ያለችውን ቅሪት እየሸጠ በርሃና ባሕር አቋርጦ በራሱ ጥረት “ምና አደከማችሁ እኔ እዛው እምጣለሁ” ብሎ ለጋሾቹ ደጃፍ ደርሷል፡፡ ለዚህም በየአመቱ ከኢትዮጰያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከሱማሌ የሚሰደደው ሕዝብ ቁጥር ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ የምዕራቡ አለም እርዳታውን በመርከብ ከማጓጓዝ ሳይድን አልቀረም፡፡ ስንዴ የሚጭኑ መርከቦች ሽብርን ለመዋጋት በሚል ሽፋን የጦር መሳሪያ በማጓጓዝ ስራ የተጠመዱ ይመስለኛል፡፡
ዛሬ ላይ የቻይና ቢዝነስ ተኮር ወረራ ያስደነበራቸው የምዕራቡ አለም አገራት የአፍሪቃን አንባገነኖች ከነ ወንጀሎቻቸውና ስንክሳራቸው ተቀበለው አብረው ለመዝለቅ የተገደዱበትና መለማመጥ የጀመሩበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ “ልማት” እና “ደህንነት” (security) ብቸኛዎቹ የምዕራቡና የአፍሪቃ አንባገነኖች የመወያያና የመደራደሪያ አጀንዳዎች ሆነዋል፡፡ ሰብአዊ መብቶች፣ ዲሞክራሲንና የሕግ የበላይነትን በዋነኝነት ያነሱ የነበሩት አውሮፓዊያን ሳይቀሩ እነዚህን አጀንዳዎች ወደጎን የገፉዋቸው መሆኑን በግልጽ እየታየ ነው፡፡ ለዚህም በኢትዮጵያ የ2007 ምርጫ ዙሪያ ያሳዩት የዳር ተመልካችነት ሚና እና ከምርጫውም በኋላ የሰጡዋቸው መግለጫዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ሁሉን ነገር ወደ ጎን ተትው “ሰላም” በሚለው አጀንዳ ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸውን ነው፡፡ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ከ”ልማታዊው” አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ያላቸውን ጥብቁ ቁርኝት አድሰው እንደሚቀጥሉም በግልጽ የሚያሳየውን የአጋርነት መግለጫቸውን አንብበናል፡፡
በአገዛዝ ሥርዓቱና በአለም አቀፉ ማኅበረሰብ መካከል፤ የአፍሪቃ ኅብረቱንም ጨምሮ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ቀደም ብሎ የተደረሰበት አንድ አይነት ስምምነት እንዳለ ከሚያሳዩት ፍንጮች መካከል አንዱ የምርጫ ቦርድና ገዢው ቡድን ጭምር መፈክራቸው “ምርጫዉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል” የሚል ነበር:: ይህ መሪ መፈክር ተደጋግሞ በሁሉም ሚዲያዎችም እነቪኦኤን ጨምሮ እስክንደነቁር ድረስ ሲነገርን ቆይቷል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ ቅድመ ሥራ የተሰራበት ነገር ስለመሆኑ ምንም አያጠራጥርም፡፡ አንደኛ ሰላም ባለበት አገር ልክ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ ዳመና እንዳንጃበበ ተደርጎ የተሰራው ሰፊ ቅስቀሳና ዘገባ ሕዝቡ ስጋት ውስጥ እንዲገባና እንዲሸበር አድርጎታል፡፡ ይህ ተንኮል ያልገባውና ቀላል ግምት የማይሰጠው ሕዝብም ሊመጣ ይችላል ከተባለው አደጋ እንኳን ወያኔ አንዳች ሰይጣናዊ ኃይል ቢያስጥለው አይጠላም፡፡ ይህም ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነገር ነው፡፡ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ ፈጥሮ ሕዝብን ማስጨነቅና ማስሸበር የተፈለገበት ዋነኛ አላማም የገዢውን ኃይል ብቸኛ የሰላም አስከባሪነት ሕዝብ አጉልቶ እንዲያየውና ወያኔ ከሌለ ያልቅልናል የሚል ስጋትም በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል:: ይህ ደግሞ ከአመታት በፊት ቀድሞ የተወሰነና የምዕራቡንም አለም ቅቡልነት ያገኘውን የገዢውን ቡድን በስልጣን የመቆየት እቅድና ሕዝብ ባይዋጥለትም ሳያገራግር እንዲቀበል ለማድረግ ያለው ቀላሉና ብቸኛው መንገድ ነበር፡፡ ስለሆነም “ነጻና ፍትሐዊነት” በምንም መልኩ የዚህ ምርጫ መሪ መፈክሮች አልነበሩም፡፡ ወያኔም ይህን ለማሟላት ዝግጁ አይደለም፡፡ ስለዚህ ምርጫውን ተከትሎ አንዳች የመተላለቅ አደጋ እንዳንጃበበ አድርጎ የማቅረቡ ፋይዳ ለወያኔም ሆነ ለምዕራቡ አለም ብቸኛው የማደናገሪያ ካርድና የመውጫ ቀዳዳ ነበር፡፡
ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት እንኳን በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ሲጉላሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩና አልፎም በአንዳንድ ቦታዎች ሲገደሉ የበርካታ ሚዲያዎች፣ የአፍሪቃ ሕብረት ታዛቢዎችና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ አንድ አይነት ነጠላ ዜማ ነበር የሚያዜሙት፤ “የምርጫው ሂደት ሰላማዊ ነው፡፡ … በሰላምም ተጠናቋል፣ ወዘተ…”፡፡ ይህ ከላይ እንዳልኩት አንድም የአገዛዝ ሥርአቱን ብቃትና ጥንካሬ ለማጉላት ያለው ብቸኛ መንገድ ስለሆነ በሌላ መልኩም ቀድሞ የተዶለተበትንና አለም አቀፍ ቅቡልነት ያገኘውን በምርጫ ስም የአንባገነን ሥርዓቱን የአገዛዝ ዘመን የማደስ ስልት ለመሸፈን የተደረገ የትብብር ዘመቻ ነው፡፡
ምርጫ የዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሚረጋገጡባቸው መንገዶቹ አንዱ ነው፡፡ ልማት ደግሞ የአንድ አገር ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መበቶች በተሟላ መልኩ እንዲረጋገጡ የሚያስችል ሌላው መንገድ ነው፡፡ ልማትና ዲሞክራሲ ተጣጥመው በሚሄዱበት ስፍራ ሁሉ ማህበራዊ ፍትሕም ይሰፍናል፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምም ይኖራል፡፡ ለዚህም ነው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ በሁለት ማዕቀፍ የተቀመጡት መብትና ነጻነቶች፤ የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የባሕላዊ መበቶች ሳይነጣጠሉ መተርጎምና መከብር እንዳለባቸው የተደነገገው:: ይሁንና ለድሃ አገራት ስንዴና ዘይት እየረዳ ስለ ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር ካንገት በላይም ቢሆን ይሟገት የነበረው የምዕራቡ አለም ‘ድሃ በል’ በሆነው የገበያ መርህና በግሎባላይዜሽን ስም የዝርፊያ ጋሪውን አስቀድሞ ዜማውን በመቀየር ከ”ልማታዊ” አንባገነኖች ጋር ተስማምቶ የእጃዙር ቅኝ ግዛት መረቡን አፍሪቃ ላይ ጥሏል፡፡ እኛንም ከገዢዎቻችሁ የተራረፈውን ቀምሳችሁ ማደር ከቻላችሁ ዲሞክራሲንና ሰብአዊ መብቶችን ቀስ ብላችሁ በመቶ አመት ሂደት ትቀዳጃላችሁና ተረጋጉ እያሉን ነው፡፡ ለጊዜው አለማችን እኛው በፈጠርናቸው ሽብርተኞች ተወጥራለችና እጃቸው ከመውደቋ በፊት እነሱን ለማጥፋት እንተባበር እያሉን ነው፡፡ እንግዲህ የሚበጀንን እንምረጥ::
በቸር እንሰንብት!
ያሬድ ኃይለማርያም

Continue Reading
9 Comments

9 Comments

 1. yidnekachew

  June 24, 2015 at 1:57 pm

  በግሌ ነጻነት በሌለበት ነጻነት ከሚመርጡ ዜጎች ጋር ልትመድበኝ ትችላለህ፡፡ለዚህም በፈቃዴ የሰጠሁህ ነጻነት ነውና በፈለግከው መልኩ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡ሃሳቡ በገባኝ ያህል ስመዝነው ግን ወደ ውስጥ መመልከት ነው ጠቃሚ የሚሆነው ከውጭ የሚመጣ ፍርፋሪውም አልጠቀመንም የሚለውን እይታዬን ለማካፈል እንጂ ለሰልፍ አይደለም፡፡
  ሁኔታዎች እየፈቀዱልን ባይሆንም ለምጄዋለሁና ኢትዮጵያውያን ነኝ ብዬ በድፍረት ልቀጥል፤ ባታሪካችን አንድም ለውጥ ህዝቡ እነደ ህዝብ ተንቀሳቅሶ ያስፈልገኛል ብሎ ጠይቆ ለውጥ ያመጣበት ጊዜ አላየሁም ምነአልባት የኔ አተያይ ሊሆን ይችላል ብዬ ራሴን ባልወቅስም እናንተ እንደመሰላችሁ፡፡ ካነበብኳቸው ታሪኮች ግን ሌላው ቀርቶ ታላላቅ የምንኮራባቸው የታሪክ አሻራዎች ሲፈጠሩ በወቅቱ የነበሩ ጥቂት ዓይኖቻችን ለማጥፋት ከጠላት ጋር ሲደራደር የነበረው ከሚያግዛቸውና ከሚታዘዛቸው በላይ ነበር፡፡በየትኛውም የታሪክ አንጓችን የምንኮራባቸው ጥቂት ብልሆች እነጂ ህዝብ አላገኘሁም ይልቁንም አጥፊውን የሚደግፍ ነበር ሚበዛው፡፡በተጨማሪም የችግቻችን መፍትሄ ከውጭ ለማፈላለግ ሃገሪቷን የሚቸበችብ የ60ዎቹ ትውልድ ተብሎ የሚወደሰው ጭምርና የእውነተኛ ለውጥ ፈላገው ሰው ቁጥርም እነደዛው ነበር የተጣሉ/የተጋጩ አስተሳሰቦች የበዙበት ሃገርና ህዝብ፡፡
  አንድ ደራሲ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲበላው የሚያክ፣ሲጎረብጠው የሚገላበጥ እንጂ ለምን ብሎ የሚመራመር አለመሆኑን ያሳያሉ ይህ ደግሞ የፈለገው ሃገር ወዳድ ብትሆኑ እውነተኛው የህዝቡ ችግ ነው፡፡ሌላው ሆዱ ከሞላ ምንም ማሰብ የማይችል ብሎም የማይፈልግ ህዝብ ነው የተሸከመችው፡፡ ቅናት ምቀኝነት ተንኮል እንጂ ምርምር ጥያቄ ተነሳሽነት የመያቋርጥ ለውጥ ፈላጊነት የዚህ ህዝብ እጣ ፈንታ አይደለም፡፡ እነደውም የተረቶቹ ምዓት ተስፋ ያስቆርጣል ከጎረሱት የዋጡት እያለ በኢህሰዴግ ለ 100 ዓመት ለመገዛት የወሰነና የፈቀደ ህዝብ ነው ያለን፡፡ለመማር ሳሆን በትእቢት የተወጠረ በግልብ እውቀትና በጥራዝ ነጠቅነት የሟሸሸ ህዝብ ነው ያለው፡፡
  ለማንኛውም ኢህዴግ በቻይና ፍቅር ወደቀ ህዝቡን ጣለ፤ደርግ በሩሲያ ፍቅር ወደቀ ህዝቡን ጣለ፤ንጉሱ በእነግሊዝ ፍቅር ወደቁ ህዝቡን ጣለ፤ አጼ ምኒሊክም ከፈረንሳይ ፍቅር ይዟቸው አሸለቡ፡፡ እናንተ ደግሞ አሜሪካን ምን እንድታደርግ እነደምትፈልጉ አላውቅም የ100 ዓመት የቤት ስራ ለዚች ሃገር እነሰጣለን ብለው ተነሱ ተሳካላቸው ታዲያ መጣ ሄደ ምን ያደርጋል ለምን ይመለካል ምንም አላቹ ምን በዓለም ላይ ሰላም እንዳይሰፍን የምትፈልግ ሃገር ለመሆኗ ማረጋገጫ ከፈለጋችሁ Read about The Georgian Guide stone, Evil Illuminati and others.

 2. ETHIOPIAN

  June 24, 2015 at 1:36 pm

  እንደዚህ ዓይነት ትችት ጠቃሚ የሚሆነው ኣንተም በሃገርህ ውስጥ እየሰራህ ለሃገርህ ትክክለኛ ፍቅር ሲኖርህ ለህዝብህ ስትወድና ስታፈቅር ብቻ ነው። ኣሁን የምትለው ግን 100% ጨለምተኝነት ነው። ጨለምተኝነት ደግሞ በኣሁን ግዜ በሃገራችን ውስጥ ቦታ የለውም ኣንተ ቅሬታና ኣብየቱታ ሲኖርህ ቅሬታህንና ኣብየቱታህን ለኣውሮፓውያን ነው የምታቀርበው ምክንያቱ በራስ መተማመንህ በጣም ስለ ወረደ ነው። በሃገር ውስጥ ሆነህ ግን ያየሀውን ስህተት እንደዚህ ቢስተካከል ብለህ ሓሳብ መስጠት ትችላለህ። ኣንተ የሆነውንና ያልሆነውን ቅሬታህ ደርድረህ ለኣውሮፓውያን ብትናገር ችግርህ ማን ነው የሚፈታልህ እዚህ ላይ እኮ እየተሸነፍክ ነው ፣ እየተዋረድክ ነው ፣ እጅህ ለባዕድ እየሰጠህ ነው የዚህ ምክንያት ደግሞ የታወቀ ነው ያ ጨለምተኛ ኣሰተሳሰብህ በየትም ይሁን በየት የሚሳካበትና ኣንተ ስልጣን የምትጨብጥበት ሁኔታ ብቻ ነው እየሰራህ ያለሀው። ስለዚህ ይህ ዓይነት ኣካሄድ ካሁን በፊትም ኣልጠቀመንም እና ኣደብ ግዛ ሃገርህ ውደድ የራስህ ችግር በራስህ ለመፍታት ሞክር….. ጨለምተኛ…..

 3. Anonymous

  June 24, 2015 at 10:51 am

  It’s difficult to think what EPRDF is doing, imagine we are in 21st century. it is killing generations

 4. aman

  June 24, 2015 at 7:12 am

  መፍትሄው ንጌረን ተብለህ ብትጠየቅ ንሮ? እናትህ እቅፍ ነበር እምትገባው……….ምክንያቱም ጥላቻ እንጂ እዉነታው ኣልገባህም ሞኝ…

 5. Anonymous

  June 24, 2015 at 5:51 am

  ለመሆኑ:የትኛው:ዲሞክራሲ: ነው:ጉራ:የሚነዛበት:የአሜሪካን:ነው?ይሄ:በአሁን:ዘመን: በጠራራ:ፀሐይ: ጥቁር:ሰለሆነበጥይት የየሚገደልበት? ለመሆኑ:በእዚህ:ዓመት: ከጥቁር:በስተቀር:በተዳጋጋሚ:የተገደለ:በአሜሪካ:አለን?እንፈር:ኢህአዴግን:ስለጥጠላኸው:ብቻ:እታጋንነው:እንደማንኛውም:ሀገር: እያደር:ለውጥ:ይመጣል።ከጀመርነው:ልማት:አንዲት:ሳንቲሙትር:ፎቀቅ:ማለት:አንችልም።እንዲያውም:መንግሥት:ህዝቡን: ማሞላቀቁን:ናና:ተመልከ ት።

 6. Anonymous

  June 24, 2015 at 12:55 am

  ፈጣሪ ይሁነን እንጅ ነገ ምን ልንሆን እንደምንችል የምናውቀው ነገር የለንም :: መንግስት አሁንም ይበልጥ ጡንቻው ፈርጥሞ ፤ ጉልበቱን ጨምሮ ምርጫ በመጣ ቁጥር የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በመግደል ፣ በማሰርና ከሀገር በማስወጣት እንዲሁም ምርጫ በደረሰ ወቅትም ህዝቡ በፍራቻ ማቅ ውስጥ ሆኖ ይሰነብታል ፡፡ ይህንንም እርባና የሌለው ምርጫ አደረግኩ ይለናል ፡፡ የሃገሪቱ ንብረትም በውስን ዘረኛ የሆኑ ግለሰቦች ቁጥጥር ስር ሆኖ ሀገሪቷን እንዳሻቸው ሲያደርጓት በአንፃሩ በልቶ ማደር የማይችል ህዝብ የትየለሌ መሆኑን ባይናችን እያየን ነው ፡፡

 7. serawit

  June 23, 2015 at 8:18 pm

  nice

 8. Anonymous

  June 23, 2015 at 7:29 pm

  welllllll dats
  goood……

 9. Anonymous

  June 23, 2015 at 6:15 pm

  SLERASEH BEDENB MEGEGEM -MAWEK YEMATCHIL SEW SILE YE AMERICA MERI ENA AWROBAWIAN HAGERAT LEMETEBTEN MORALUM AKMUM AYFEKDLHIM MISKIN

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending