Connect with us

Articles

“ትናንት መኖር የምፈልገውን ዓይነት ህይወት ነው ዛሬ የምኖረው”

Published

on

cb73a32357004dab0c007fc139a29398_XL

 

May 03, 2014 | Written by  ኤልሳቤት ዕቁባይ

ባለፈው የትንሳኤ በዓል የ “ጆሲ ኢን ዘ ሀውስ” ፕሮግራም በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል በጎ ተግባር ያቀረበ ሲሆን ብዙዎችም አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ የሟቿ አርቲስት ማንአልሞሽ ዲቦ ቤተሰቦችን የመኖርያ ቤትና ሌሎች ችግሮች ለመፍታት የተደረገውን እልህ አስጨራሽ ጥረትና የተገኘውን አስገራሚ ውጤት ያስቃኛል -ፕሮግራሙ፡፡ አንድ ሰው ብቻውን እንኳን  በቁርጠኝነት ከተነሳ የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ትምህርት የሚሰጥና የሚያነቃቃ ሥራ ነው፡፡ “እውቅናን ተጠቅሞ ወገንን መደገፍ በአገራችን  አልተለመደም” ከሚለው አርቲስት ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ) ጋር የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት እቁባይ ተከታዩን ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡

የአርቲስት ማንአልሞሽ ዲቦ ቤተሰቦች የነበረባቸውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት ያደረግኸውን ጥረትና የተገኘውን ውጤት በኢቢኤስ የቴሌቪዥን ጣቢያ “ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ” ፕሮግራምህ ላይ አሳይተሃል፡፡   ከተመልካች ምን ዓይነት ምላሽ አገኘህ?
ሁሌም ጥሩ ነገር ስትሰሪ ይመጣል ብለሽ የምትገምቺው ምላሽ ይኖራል፡፡ እኔ ያገኘሁት ግን ፍፁም ያልጠበቅሁት ነው፡፡ በቃላት እንዲህ ነው ብሎ መግለፅ ያዳግታል ፤በጣም የሚገርም ምላሽ ነው ያገኘሁት፡፡
ከብዙ ድካምና ጥረት በኋላም ቢሆን ያሰብከው በመሳካቱ ምን ስሜት ፈጠረብህ ?
እኔ ትናንት መኖር የምፈልገውን ዓይነት ህይወት ነው ዛሬ የምኖረው፡፡ በአብዛኛው እኛ አገር እውቅናን ተጠቅሞ ወገንን መደገፍ  አልተለመደም፡፡ ያ ሁልጊዜ ያናድደኝ ነበር፡፡ አርአያህ (ሮል ሞዴልህ) ማነው ስባል እንኳን አንጀሊና ጆሊንና ብራድ ፒትን ነው የምጠራው፡፡ እነሱ ለኛ ሩቅ ናቸው፤ሆኖም  ግን እውቅናቸውን ተጠቅመው የተቸገረ ይረዳሉ፡፡ የኔ እውቅናም እዚያ ደረጃ ላይ መድረስ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ እንጂ “አየኸው አየሽው” የሚል መጠቋቆሚያ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የእነዚህ ልጆች የቤት ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ የጀመርኩት ሥራ አድካሚ የነበረ ቢሆንም ሁሉም ነገር እንዳየሽው ተሳክቷል፡፡ እኔ ያሰብኩት እንደውም  ከዚህም በላይ ነበር፤ ነገር ግን ነገሮች እንዳሰብኩት አልሄዱም፡፡ ስራው የፈጠረብኝን ስሜት በተመለከተ—-እኔ  ስራውን ለቀረፃ ብዬ አይደለም የሰራሁት፡፡ አሁንም ሳስበው ራሱ ውስጤ ይረበሻል፤ እንባ እየተናነቀሽ ቴሌቪዥን ላይ መስራት በጣም ከባድ ነው፡፡ ቤተሰብ አንድ ላይ ተቀምጦ የሚያየው ፕሮግራም ነው፡፡ ኃላፊነቱ ከባድ ነው ግን  መሸከም መቻል አለብሽ፡፡ ማህበረሰቡንና ትውልዱን የሚቀርፁ፣ ክፍተቶችን የሚደፍኑ ስራዎች መስራት አለብኝ ብዬ ስለማምንም ነው የሰራሁት፡፡
ያሰብከው ከዚህም በላይ እንደነበር ጠቅሰሃል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ነበር ያሰብከው?
ለምሳሌ ልጆቹ ቋሚ የታክሲ ገንዘብ እንዲያገኙ ፈልጌ ነበር፡፡ አክስታቸው ትእግስት ቀን ቀን እየሰራች ትምህርቷን ማታ እንድትማርና አረብ አገር ያለችውን እህቷን እንድታግዝ ነበር ሃሳቤ፡፡ እስቲ አስቢው— አረብ አገር ያለችው እህቷ ባለፈው ኢትዮጵያውያን ሲባረሩ መጥታ ቢሆን ኖሮ ምን ይሆኑ ነበር? ለትእግስት የተገኘላት ስራ ክፍያው አነስተኛ በመሆኑ ልፋት ይሆንባታል ብዬ ተውኩት፡፡ እሷን ስራ የማስያዙን ነገር ግን አሁንም አልተውኩትም፤እየሞከርኩ ነው፡፡
የማንአልሞሽን ልጆች ለማገዝ ያነሳሳህ ምንድነው? በምን ሁኔታ ላይ ነበር ያገኘሃቸው?
ለቤተሰቡ ቤት ለማግኘት ሰባት ወር ነው የፈጀብኝ፡፡ እንዳልኩሽ ስሰራው ለፕሮግራም ብዬ አልነበረም፡፡ የአርቲስት ማንአልሞሽ ልጆች የት ደርሰው ይሆን ብዬ ሳጠያይቅ— ለቡ እንደሚኖሩ ሰማሁ፡፡ ሳገኛቸው በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ነበሩ፡፡ ለቡ የገቡት ከተማ የቤት ኪራይ በጣም ተወዶባቸው ነው፡፡ እናታቸው በአንድ ወቅት በጣም ታዋቂ አርቲስት ስለነበረች ልጆቿ ብዙ ጥሩ ነገርና ምቾት ለምደዋል፡፡ እኔ ሳገኛቸው ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ቤታቸው የሄድኩ ብቸኛ እንግዳ እንደሆንኩ ነገሩኝ፡፡ ቤተሰቡ ከባድ የስነልቦና ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ልጆቹ ተገልለዋል፡፡ እሷ ሳለች የለመዱትን ጥሩ ነገር ሁሉ አጥተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ኑሮን ለመቋቋም የወሰኑት ውሳኔ በጣም ከባድ ነው፡፡ አንድ አክስታቸው ትምህርቷን አቋርጣ፣ ልጆቹን እያሳደገች ነው፡፡ ሌላ አክስታቸው አረብ አገር ሄዳ እየሰራች  መተዳደሪያ የሚሆናቸው ገንዘብ ትልካለች፡፡ አሁን ደውላልኝ ነበር፡፡ ያለችበትን ሁኔታ ነግራኛለች፡፡ “እዚህ ያለሁት ተመችቶኝ ሳይሆን ልጆቹ ፆም እንዳያድሩና እንዳይቸገሩ ብዬ ነው” ብላኛለች፡፡
የልጆቹን ስሜት ለመጠበቅ ስትል ብዙ መጨነቅህ በፕሮግራምህ ላይ በግልፅ  ይታይ ነበር—
አዎ— የልጆቹን ስሜት ላለመንካት በጣም ተጠንቅቄያለሁ፡፡ እናታቸውን አጥተዋል፡፡ በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎች ዛሬ የሉም፣ ለአራት አመት ማንም አግኝቷቸው አያውቅም፡፡ ዙሪያቸውን ከከበባቸው ችግሮች ውስጥ እኔ ያተኮርኩት በመኖሪያ ቤት ፣ በትምህርት እና በጤና ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በመጀመሪያ እነሱ ጋ ልሄድ ነው ስል፣ ጥያቄ ያነሱ  ሰዎችም አልጠፉም፡፡ እኔ ጥያቄው ላይ ሳይሆን መልሱን መስጠት ላይ ነበር ያተኮርኩት፡፡ “ቴሌቪዥን ላይ የምናውቀው ሰው እንዲህ ፍቅር ከሰጠን ሌሎቹም ተሳስተው መሆን አለባቸው–” የሚል ስሜት በውስጣቸው እንዲፈጠር ለማድረግ ነው የሞከርኩት፡፡ በደረሰባቸው ችግር የተፈጠረባቸው ስሜት መለወጥ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡ እናታቸውን ቢያጡም የሚያስብላቸውና የሚቆረቆርላቸው ወገን እንዳላቸው ሲረዱ ነው ስሜታቸውና አመለካከታቸው የሚለወጠው፡፡
ለማንአልሞሽ ልጆች ያሰብከውን ለማሳካት ምን ፈተናዎችን ተጋፈጥክ ?
የሄድኩበት መንገድ በጣም ከባድ ነበር፡፡ የብዙ ሰው ፊት አይቻለሁ፡፡ አንዳንዶች “የምትሰራው ስራ በጣም አሪፍ ነው ፤እንረዳዳለን” ብለው ቃል ከገቡልኝ በኋላ፣ ጉዳዩን ዳር ለማድረስ ስደውልላቸው ጭራሽ ስልኬን አያነሱም፡፡ ስለዚህ ባለችኝ ገንዘብ ስራውን መጀመር ነበረብኝ፡፡ በሌላ በኩል ታይታውን የማይፈልጉ፣ስማችን እንዳይነሳ የሚሉ ሰዎች ያልጠበቅሁትን ድጋፍ አድርገውልኛል፡፡ በተለያዩ ቦታዎች  የተለያዩ ችግሮችና ውጣውረዶች ገጥመውኛል፡፡ ያሰብኩት ሲሳካ ግን  ሁሉንም እረሳኋቸው፡፡ ምን ሆነ መሰለሽ —- በቅርቡ የሚወጣ አልበም አለኝ፡፡ ከሱ ጋር በተያያዘ ለአንድ ኩባንያ የስፖንሰርሺፕ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየተጠባበቅሁ ነበር፡፡ ልጆቹን ሰርፕራይዝ ለማድረግ ከደብረዘይት ወደ አዲስ አበባ እየመጣን ገላን ላይ ስልክ ተደወለልኝና፣ “የአልበምህን የስፖንሰርነት ጉዳይ ጨርሰናል” አሉኝ፡፡ ያ ለኔ ትልቅ ዜና ነበር፣ ምክንያቱም ገንዘቡ በሚሊዮኖች የሚገመት ነው፡፡ ብታምኚም ባታምኚም ምንም አልመሰለኝም፤ በልጆቹ ደስታ ውስጥ ተውጬ ነበር፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ልጆቹን ከጎረቤት ጋር አስተዋውቀህ ነው የተለየሃቸው፡፡ ይሄ ለኔ ትልቅ ትርጉም ያለው ስራ ነው —-
ልጆቹን እዛ ላሉት እናቶች እና አባቶች ነው የሰጠኋቸው፡፡ ይህ ደግሞ ለሁለቱም ትልቅ እድል ነው፡፡ በረዳናቸው ለሚሉት እንደ አባት እና እናት ተንከባክበው የማሳደግ እድል ሰጥቷቸዋል፡፡ ልጆቹም ተንከባካቢ አግኝተዋል፡፡ ግቢው ጎረምሳ ይበዛበትና አይመቻቸው ይሆን — ብዬ አስቤ ነበር፡፡ እኔ አሁን እንደ አባት ነው እያሰብኩ ያለሁት፡፡ ልጆቹን ደህና ቦታ ለማስያዝ ነው ሃሳቤ፡፡ ደውዬ ሳናግራቸውም እንደ አባት ነው የማናግራቸው፡፡ በትውውቁ ላይ አዋቂ ሰዎች ሲመጡ መንፈሴን ከፍ አደረገው፡፡ በነገርሽ ላይ የሆኑ ሰዎች ከዱባይ ደውለው እያለቀሱ “ከዚህ በፊት በውሳኔ ፊልም ነበር ያለቀስነው፤ አሁን ደግሞ ትክክለኛ ህይወት በቴሌቪዥን አይተን አለቀስን” አሉኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ልጆቹ ከቤተሰብ ጋር ነው የሚኖሩት፡፡ በኢትዮጵያ ባህል መሰረት ጉልበት  ስመው ነው ከአዲሱ ቤተሰባቸው ጋር የተዋወቁት፡፡
አንዳንዶች ዝነኝነት ሲመጣ ኣያያዙን  ባለማወቅ ግራ ሲጋቡና ለችግር ሲጋለጡ ይታያል፡፡ ታዋቂነት ላንተ እንዴት ይገለፃል?
ዝናና ክብር ሲመጣ መንገድ የሚስት ይኖራል ፤ ፈፅሞ ከመስመሩ ውልፊት የማይልና መንገዱን የማይስትም አለ፡፡ ቤቱ ለልጆቹ ሲፈቀድላቸው በጣም ተደስቼ ስለነበር ጓደኞቼን “እራት እንብላ” አልኳቸው፡፡ እራት እየበላን ቤቱ እንደተፈቀደ ስነግራቸው፣ የተወሰኑት “ለዚህ ነው የጠራኸን? እኛ ደግሞ ለአልበምህ ስፖንሰር ዘግተህ መስሎን ነበር–” አሉኝ፡፡  ለነገሩ በእነሱም አልፈርድም፡፡ እኛ አገር የተለመው እንዲህ ነው፡፡ አንድ ሰው በአብዛኛው ደስ ብሎት የሚፈነድቀው የራሱ ጉዳይ ሲሞላለት ብቻ ነው፡፡ የሌላው ችግር ብዙም አያሳስበንም፡፡ ሁሉንም ሰው በጅምላ ማለቴ ግን አይደለም፡፡ ጥቂት ቢሆኑም ከራሳቸው አልፈው ለሌላው የሚያስቡና ለውጥ ለማምጣት የሚተጉ አሉ፡፡
አዲሱ አልበምህ መቼ ይወጣል?
በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ይወጣል፡፡ በጣም አሪፍ ስራ ይዤ መጥቻለሁ ጠብቁ፡፡ አሁን የ “ጆኒ ኢን ዘ ሃውስ” ፕሮግራም ሲዝን ሶስት ስለሚጀምርም በጣም ስራ በዝቷል፡፡
በሲዝን ሶስት ምን አዲስ ነገር እንጠብቅ?
ሲዝን አንድን ጨርሼ ሲዘን ሁለት ልጀምር ስል ከተመልካቾች በተቀበልኩት አስተያየት “ምንም ለውጥ አታድርግ” ያሉኝ ብዙ ነበሩ፡፡ በሚቀጥለው ሲዝን ለተመልካች የሚጠቅም፣ ማዝናናቱን ያልለቀቀ፣ ቁም ነገር የሚያስጨብጥ ፕሮግራም ይዤ እመጣለሁ፡፡ ተመልካቹ  ቀጥል ብሎ ፊሽካውን ነፍቶልኛል፡፡ “እንኳን አሁንና ሙሉ ትጥቅ እያለን በጦር በጎራዴ ታንክ እንማርካለን” አይደል የሚባለው፡፡ አሁን የህዝብ ይሁንታንና ፍቅርን አግኝቻለሁ፡፡ ስለዚህ በእርግጠኝነት ከእስካሁኑ የላቀ ጥሩ ነገር እሰራለሁ፡፡ በነገርሽ ላይ ከህፃናት ጀምሮ መንገድ ላይ ያየኝ ሁሉ ነው የሚመርቀኝ፡፡ አንዳንዴ ከራሳችን አልፈን  ለሌላው አስበን ስንሰራ ሽልማቱ ብዙ ነው፡፡ ከሁሉም ግን የህሊና እርካታው ይበልጣል፡፡ አየሽ  እርስ በርስ ካልተሳሰብንና ካልተደጋገፍን በቀር ሌላ ማንም አይደርስልንም፡፡ በእኔ እምነት “ጠላት” የሚባሉ ሰዎች እንኳን ከምር ጠላት አይደሉም፤ የሚፈልጉት መድሀኒት ነው፡፡
የባህሬን ስራህ እንዴት ነበር?
በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ስራዬን ከጨረስኩ በኋላ አንድ ኢትዮጵያዊት ምሳ ጋበዘችኝና እቤቷ ሄድኩ፡፡ ምሳውን ተጋብዘን ከጨረስን በኋላ፣እዛ ቤት የምትሰራ ኢትዮጵያዊት አለች፡፡ የማንአልሞሽ ልጆች ላይ በተሰራው ፕሮግራም ስሜቷ በጣም መነካቱን ነግራኝ፣ ልሄድ ስል አሰሪዋን “ከደሞዜ ላይ የሚቆረጥ የታክሲ ብር ስጭልኝ” አለቻት፡፡ ልቤ በጣም ተነካና፤ገንዘብ ተከፍሎኝ ልሰራ እንደመጣሁና የሚመልሰኝ መኪና እንዳለ ነግሬያት፣ “አገር ቤት ለቤተሰብ የምትልኪው ገንዘብ ካለሽ ልውሰድልሽ” ስላት “ለነሱ አሁን አልክም፣ ትንሽ አጠራቅሜ ነው” አለችኝ፡፡ ከሌላት ገንዘብ ላይ ልትሰጠኝ በማሰቧ ልቤን በጣም ነካችው፡፡
ከመጣህ በኋላ የማንአልሞሽን ልጆች ጠየቅሃቸው?
አዎ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለሆነው ልጅ ከባህሬን ተጨማሪ ላብቶፕ ስለተላከለት እሱን ላደርስ እሄዳለሁ፡፡ አሁን ቤታቸው በቴሌቪዥን ካየሽው በላይ ሆኗል፡፡ ማድቤቱን የሚሰሩ ሰዎች አግኝተናል፡፡ ዋሪቶችም ኪችን ካቢኔት እንሰራላቸዋለን ብለውናል፡፡ ልጆቹ አዲስ ህይወት ላይ ናቸው፡፡ ስለነሱ ሳስብ ውስጤ በጣም ይረበሻል፡፡ ከለቡ ወደዚህ ቤት ሲመጡ እቃቸው ብዙ ስለነበር የመኪና ዋጋ ተወደደ፣ ሁሉም ከስምንት መቶ ብር በታች አንጭንም ብለው ሙጭጭ አሉ፡፡ ሊያግዛቸው የሄደ ከእኔ ጋር የሚሰራ ልጅ ዋጋ እንዲቀንሱለት ብሎ፣ለሾፌሩ ጉዳዩን ነገራቸው፡፡
እንደዚያ ሲከራከሩ የነበሩት ሰውዬ ምንም ሳያቅማሙ “ነዳጁን ቅዳና በነፃ እወስዳለሁ” አሉት፡፡ በመንገዳቸው ላይ ትንሿ ልጅ “ለካ እስከዛሬ ሌላ አገር ነው የምንኖረው፣ እንደዚህ ርቀን ነበር እንዴ?” ስትል ሾፌሩ ሰምተው እንባቸውን መቆጣጠር አቃታቸው፡፡ እንዳልኩሽ — ሲዝን ሶስትን ለመጀመርና አልበሜን ለማውጣት ሩጫ ላይ ነኝ፤ ያለችኝን ጊዜ አመቻችቼ  እጠይቃቸዋለሁ፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

Continue Reading
37 Comments

37 Comments

 1. serkalem mulugeta

  May 12, 2014 at 1:39 pm

  እግዚአብሔር በህይወትክ ሁሉ ጣልቃ ይግባልክ እመብርሃን ሃሳብክን ትሙላው ፕሮግራሙን ባየነው ግዜ በጣም እያለቀስን ነበር አግዚአብሔር ከአይን ያውጣህ፡፡

 2. tsadkan

  May 9, 2014 at 2:07 pm

  Jossy Betam konjo sra sertehal hule E/r kante ga yhun.Betam enwedhalen enakebrhalen.Bego sra yehlina ereft new !!!!!!!!!!!!!

 3. mahder

  May 9, 2014 at 7:53 am

  egziabher edmena tena yistih hasbihin yimulaw

 4. mitmita

  May 8, 2014 at 9:37 pm

  “tibeb ayinetgna negr natina tibebin agign.kehabtim hulu mastewalin atrif tebikat esuam kef kef tadergihalech…akbirat ersuam takfihalech.lerasih yedesta aklilem tisetihalech bedsta aklilm tibetkihalech” M.Msal 4 #7-9….jossy yanten program simelket bewnet 2tgnaw alebe show(alebachew teka)behillinaye yimlalsal………..berta GOD BLESS YOU!!!

 5. Anonymous

  May 8, 2014 at 7:24 pm

  wow!!! jossy fruit of ethiopia, i appreciated you with loss of words by heart because all things you have accomplished are very intersting which expresses your humanity gifted from God.
  i hope you may do a lot.

 6. Anonymous

  May 8, 2014 at 4:14 pm

  Jossy e/r yasebkewn bemulu yasakalh tebark. AkEBRHAlEW!!!!

 7. Anonymous

  May 8, 2014 at 2:58 pm

  10Q Jossy.Let God give more than what you want!!!!!!!!!!!!!!

 8. Tahay zlike

  May 8, 2014 at 2:43 pm

  Gose yeserawet gata Egzabeher
  lezelalem yebarekhe !!

 9. Anonymous

  May 8, 2014 at 2:20 pm

  በጣም ነበር ልብ የሚነካው እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ፡፡

 10. Anonymous

  May 8, 2014 at 2:19 pm

  nurit 41 mins ago

  ጆሲ ምን እንደምልህ አላውቅም እመብርሀን ሕይወትህን በብርሀን ትሙላው ሁሌም ያሳብከው እንዲሳካ እመኛለሁ
  ለብልህ አይነግሩም በርታ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን

 11. meskerem

  May 8, 2014 at 1:54 pm

  በጣም ነበር ልብ የሚነካው እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ፡፡

 12. Anonymous

  May 8, 2014 at 1:37 pm

  E/R yebarkeh jossy enwedhalen!

 13. nurit

  May 8, 2014 at 1:36 pm

  ጆሲ ምን እንደምልህ አላውቅም እመብርሀን ሕይወትህን በብርሀን ትሙላው ሁሌም ያሳብከው እንዲሳካ እመኛለሁ
  ለብልህ አይነግሩም በርታ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን

 14. Zerihun

  May 8, 2014 at 12:47 pm

  እግዚአብሔር ይባርክህ ፡፡ ያሰብው ሁሉ እንዲሳካልህ መልካም ምኞቴ ነው፡፡

 15. Zinash Tezera

  May 8, 2014 at 12:05 pm

  ጆሲ በእውነት በጣም ደስ የሚል እና ልብ የሚነካ ነገር ነው የሰራኸው ጌታ ያሰብከውን ሁሉ ያሟላልህ ሌሎችን ለማስደሰት እንደሞከርክ በዘመንክ ሁሉ የሚያሰደስት ነገር ያጋጥምክ ተባረክ……….

 16. sofi weldeyesus

  May 8, 2014 at 11:36 am

  tilik bereket new yagegnehew josy Egiziabihar yibarkih chemiro yibarikih

 17. Hailu kassaye

  May 8, 2014 at 11:24 am

  You are really an honorable Ethiopian! please keep on doing this for the rest of your life!!

 18. Anonymous

  May 8, 2014 at 11:12 am

  Jossy, eyalekesku new yayehut. God bless u.

 19. ABI KONJO

  May 8, 2014 at 11:02 am

  wow josy smart sewu e/r yirdak eniwedikalen

 20. Anonymous

  May 8, 2014 at 10:59 am

  Bless u Jossy

 21. Anonymous

  May 8, 2014 at 10:34 am

  E/r ybarkeh jossi smart

 22. Anonymous

  May 8, 2014 at 10:32 am

  ጆሲ አንተ በጣም ትልቅና እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነህ፡፡ እግዚአብሔር ዘመንህን፣ ሥራህን ሁሉ ይባርክልህ!!!! ሌላ ምንም ቃል የለኝም፡፡

 23. Anonymous

  May 8, 2014 at 10:10 am

  jossy gegna yehe leleloch tawaki sewoch timehert yemisete new sint ewekena noruachew minem asetewaso yalabereketu sewoche alu kezih memar albachew

 24. melese abebe

  May 8, 2014 at 9:52 am

  bewenate betame des belogale bazhe katlbate e/g yerdahe “enda hilena natante yamemahe terase yalme”

 25. Khalid gemechu

  May 8, 2014 at 9:42 am

  Jossye kelb turu sew neh yemtserachw bego negeroch betam yasdestugnal kedestayem bzat yasleksegnal anten fetari wedezih tru menged slemerah hulem fetarihn amesgn hulem fetari kante gar yhun idmena tena ystk amen iwedhalew

 26. Anonymous

  May 8, 2014 at 9:14 am

  በጣም ነበር ልብ የሚነካው ሁለት ጊዜ ፕሮግራሙን ሳይ ነው ያለቀስኩት እግዚአብሔር ውለታህን ይክፈልህ፡፡

 27. Anonymous

  May 8, 2014 at 9:13 am

  GBU José

 28. Anonymous

  May 8, 2014 at 9:00 am

  ጆሲ እግዚሐብሄር አምላክ አብዝቶ ይባርክ፡፡ ለእኛ ለወጣቶች አርእያ የምትሆን ልጅ ነህ፡፡ አይደለም አንድ ግለሰብ ይቅር እና የገዛ ዘመድህ እንኩዋን እንዲህ የሚያደርግ እሪንጃአ ሚያደርግ ያለ አይመስለኝም፡፡

 29. TIGIST Abera

  May 8, 2014 at 8:45 am

  Josy really it’s very teaching hearth I wish
  We are ethiopian people helping each other
  My God bless you more !!

 30. Abebe Lega

  May 8, 2014 at 8:27 am

  Jossy Fetari kante gar yehun. Please dig more, merdat leminfeleg yetemechache huneta ale wey? “እንኳን አሁንና ሙሉ ትጥቅ እያለን በጦር በጎራዴ ታንክ እንማርካለን” አይደል የሚባለው፡፡

 31. seble mekonen demsie

  May 8, 2014 at 7:44 am

  jossy ewnat betam tilk sew nah E/r bangru hulu yekatlk edmna tena yestk

 32. khalid

  May 8, 2014 at 7:36 am

  A wonderful story.

 33. Anonymous

  May 8, 2014 at 7:22 am

  i like u , peoples like u have to learn such humanity from you ! ! !

 34. semegn

  May 8, 2014 at 7:16 am

  betam des yemil sera new eyadrke yalehew e/bher yeme

  wdwen sera new

 35. Anonymous

  May 8, 2014 at 6:51 am

  Jossy ye ewnet tilk sew neh,..abo tidar yistih tru mist tru lij aging

 36. Anonymous

  May 8, 2014 at 6:45 am

  ………………….0

 37. Aklil Tsega

  May 8, 2014 at 6:35 am

  betam dese yemil bego sera sertehal kortenebehal E/R yebarkehe berta adenakeh nege Aklil from sebeta/Addis Abeba

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending