Connect with us

Articles

በ42ኛ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኬንያውያን በግል ኢትዮጵያውያን በቡድን ውጤቶች ጎልተው ታይተዋል

Published

on

36

ኬንያ የበላይ ሆና ባጠናቀቀችበት የካምፓላው ፉክክር ለአሸኛፊዎች ከተዘጋጁት 27 ሜዳልያዎች 25ቱ በምስራቅ አፍሪካ አገራት ተወዳዳሪዎች ተወስደዋል

በኡጋንዳ አስተናጋጅነት ካምፓላ ላይ በተከናወነው 42ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የተተበቀው የኢትዮጵያ እና ኬንያውያን ፉክክር የታየ ሲሆን ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች ፉክክርን በአንደኛነት ያጠናቀቀው የአዘጋጇ አገር ተወዳዳሪ ጃኮብ ኪፕሊሞም በ2007 ዓ.ም. ሞምባሳ ላይ ከተከናወነው ውድድር ወዲህ ከኢትዮጵያ እና ኬንያ ውጪ የሆነ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል፡፡

ከፍተኛ ብዛት በነበራቸው የኡጋንዳ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ደጋፊዎች ፊት በተከናወነው በዚህ ውድድር ላይ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ ጭምር ታዳሚ የነበሩ ሲሆን ውድድሩም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ግዜ በተከናወነው የሁለቱም ፆታዎች ድብልቅ ሪሌ ፉክክር ተከፍቷል፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ በተከናወነው የ8 ኪ.ሜ. ድብልቅ ሪሌ ኬንያውያን በኦሊምፒክ እና በሶስት ግዜ የዓለም 1500ሜ. ሻምፒዮኑ አስቤል ኪፕሮፕ፣ ዊንፍሬድ ንዚሳ፣ በርናርድ ኪፕኮሪር እና ቢያትሪስ ቼፕኮኤች አማካኝነት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሲሆኑ ወልዴ ቱፋ፣ ቦኔ ጩሉቄ፣ የዓለም ወጣቶች የ5000ሜ. ሻምፒዮኑ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና የ1500ሜ. የዓለም ሻምፒዮንና የሪኮርዱ ባለቤት ገንዘቤ ዲባባ በቅደም ተከተላቸው መሰረት ሮጠው የብር ሜዳልያ አስገኝተዋል፡፡ ዜግነታቸውን በቀየሩ አራት ትውልደ ኬንያውያን የተወከለችው ቱርክ ሶስተኛ በመሆን የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡ እያንዳንዳቸው ሁለት ኪሎ ሜትር በሮጡበት በዚህ ፉክክር ላይ ኬንያውያን በጠንካራ አትሌታቸው ኪፕሮፕ በመጀመር ፉክክሩን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻው በመሪነት መጨረስ ያስቻላቸውን አካሄድ ሲተገብሩ ኢትዮጵያውያ ሁለቱ ምርጥ አትሌቶቿ ዮሚፍ እና ገንዘቤን ሶስተኛ እና አራተኛ ተቀባይ ማድረጓ ወርቁን ለማግኘት አዋጭ መንገድ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን በሁለተኛነት የጨረሰበት ሰዓት ከአሸናፊው የኬንያ ቡድን በስምንት ሰከንድ ያነሰ ነው፡፡

 ለተሰንበት ግደይ በካምፓላ ውድድሩን በድል ስታጠናቅቅ (Photo - Roger Sedres) © Copyright

ለተሰንበት ግደይ በካምፓላ ውድድሩን በድል ስታጠናቅቅ (Photo – Roger Sedres) © Copyright

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ብዙም ሳትቸገር ከሁለት ዓመት በፊት በቻይና ጉያንግ ያስመዘገበችውን የአሸናፊነት ክብር ባስጠበቀችበት ከ20 ዓመት በታች ሴቶች 6 ኪ.ሜ. ፉክክር በ18 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ አንደኛ ስትወጣ የሀገሯ ልጅ ሀዊ ፈይሳ በ18 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆናለች፡፡ የሶስተኝነቱን ስፍራ ሴልፊኔ ቼፕቴኬ (19:02) ከኬንያ አግኝታለች፡፡ ፎቴን ተስፋዬ እና ዘይነባ ይመር በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና አስረኛ ሆነው መጨረሳቸውም ኢትዮጵያ በነጥብ ድምር ኬንያን በአንድ ነጥብ በልጣ የቡድን ወርቅ ሜዳልያው አሸናፊ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያ ቡድን ተሰላፊዎች ብሪ አበራ (20:00) እና ውዴ ከፍአለ (20:04) በውደም ተከተላቸው መሰረት 12ኛ እና 13ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ ይህን ፉክክር ከጅምሩ አንስቶ ኬንያውያን አትሌቶች በበላይነት ሲመሩት ቢቆዩም እና በኋላ ላይም ሁለቱ ወደፊት ተነጥለው ለመውጣት ቢሞክሩም በመጨረሻው ዙር ላይ በኢትዮጵያውያኑ ከመቀደም ሊያመልጡ አልቻሉም፡፡ በካምፓላ ያስመዘገበችው ድል ገንዘቤ ዲባባ በ2008 እና 2009፣ ኬንያውያኑ ቪዮላ ኪቢዎት በ2001 እና 2002 ፌይዝ ኪፒዬጎን በ2011 እና 2013 ያሳኩትን የአሸናፊነት ክብርን የማስጠበቅ ገድል እንድትፈፅም የረዳት ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ በስፍራው ለነበረችው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ ዘጋቢ በሰጠችው አስተያየት ‹‹የመወዳደሪያ ስፍራው በተወሰነ መልኩ ሳሩ ያደገበት ቦታ እና ብዙ መሰናክሎችም የነበረው በመሆኑ ትንሽ ፈትኖኛል፡፡ ሆኖም ባስመዘገብኩት ድል ደስተኛ ነኝ፡፡ የፊታችን ነሐሴ ወር ለንደን ውስጥ በሚካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ላለኝ ሕልምም ይህ ውጤት ጥሩ መነቃቃትን ይፈጥርልኛል›› ብላለች፡፡

ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

ባለፉት ሁለት ውድድሮች ኢትዮጵያ በሀጎስ ገ/ሕይወት እና ያሲን ሀጂ ድሎች አማካይነት የበላይ ሆና በታየችበት ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፉክክር ካምፓላ ላይ በደጋፊው ፊት የሮጠው ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ ለሀገሩ የመጀመሪያው የሆነውን የዓለም አገር አቋራጭ ወርቅ ሜዳልያ ድል አስመዝግቧል፡፡ ከውድድሩ በፊት የአሸናፊነቱ ግምት በስፋት የተሰጠው ለኬንያ እና ኢትዮጵያ አትሌቶች የነበረ ቢሆንም ኪፕሊሞ ከሀገሩ ሕዝብ ባገኘው ከፍተኛ ድጋፍ ተበረታቶ ከ2007 ዓ.ም. ወዲህ ያልታየውን ከኢትዮጵያ እና ኬንያ ውጪ የሆነ አገር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊነት እውን እንዲሆን አድርጓል፡፡ የኤርትራ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ አትሌቶች ከፊት መሪዎቹ ተርታ በመሰለፍ ሲፎካከሩበት በቆየው በዚህ ውድድር ላይ ኬንያውያን አሸናፊውን አትሌት አስለቅቀው ለመሄድ ያደረጉት ሙከራ ስኬታማ ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡፡ ኪፕሊሞ በደጋፊዎቹ ከፍተኛ ጩኸት ታጅቦ ሁለቱን ኬንያውያን እና ኢትዮጵያዊው ሶሎሞን በሪሁን አስለቅቆ ወደፊት በመገስገስም ውድድሩን 22 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በሆነ ግዜ በቀዳሚነት ማጠናቅቅ ችሏል፡፡ መጨረሻ ላይ ከፊቱ የነበሩትን ሁሉ በከፍተኛ ፍጥነት እያለፈ የመጣው ኢትዮጵያዊው አምደወርቅ ዋለልኝ አስቀድሞ ልዩነቱን አስፍቶ በነበረው ኪፕሊሞ በ3 ሰከንድ ልዩነት ተቀድሞ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሪቻርድ ያቶር (22፡52) ከኬንያ ሶስተኛ ወጥቷል፡፡ በተስፋ ጌታሁን፣ ሰለሞን ባረጋ እና ተፈራ ሞሲሳ ከ4ኛ – 6ኛ ባሉት ደረጃዎች በቅደም ተከተል ተከታትለው በመግባት ኢትዮጵያ የቡድን የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት እንድትሆን አስችለዋታል፡፡ ባየልኝ ተሻገር እና ሶሎሞን በሪሁን ፉክክሩን 12ኛ እና 13ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

ከ20 ዓመት በታች የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

ከ20 ዓመት በታች ወንዶች የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

አሸናፊው ኪፕሊሞ ከድሉ በኋላ ለአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ ድረ ገፅ ዘጋቢ በሰጠው አስተያየት ‹‹ፉክክሩ በጣም ጥሩ ነበር፡፡እኔም ማሸነፍ እንደምችል አስብ ነበር፡፡ በመጨረሻው ዙር ላይ አስለቅቄ ለመሄድ ስወስን ውድድሩን በአሸናፊነት እንደማጠናቅቅ ታውቆኛል›› ያለ ሲሆን የብር ሜዳልያ አሸናፊው አምደወርቅ በበኩሉ ‹‹ባገኘሁት የብር ሜዳልያ ደስተኛ ነኝ ነገር ግን ሁለተኛ በመውጣቴ ሙሉ በሙሉ አላረካኝም፡፡ ባቀድኩት መልኩ እንዳልሮጥ ደጋፊዎቹ ነገሮችን አክብደውብኛል›› በማለት ተናግሯል፡፡

ጥሩነሽ ዲባባ በ2008 ዓ.ም. ለመጨረሻ ግዜ ካሸነፈች በኋላ በኬንያውያን ቁጥጥር ስር የዋለው የአዋቂ ሴቶች የወርቅ ሜዳልያ ዘንድሮም ከ1ኛ – 6ኛ ኬንያውያን ተከታትለው ከገቡበት ሌላ አስገራሚ የ10 ኪ.ሜ. ገድል ጋር ወደናይሮቢ አቅንቷል፡፡ ኬንያውያን ለመጀመሪያ ግዜ ሶስቱንም ሜዳልያዎች ጠራርገው በወሰዱበት በዚህ ፉክክር ተከታዮቹንም ሶስት ደረጃዎች ባለማስቀመስ አዲስ ታሪክ አፅፈዋል፡፡ ኢረኔ ቼፔት (31:57)፣ አሊስ አፕሮት (32:01) እና ሊሊያን ካሳዪት (32:11) ለኬንያ ሜዳልያዎቹን ያስመዘገቡት ሶስት አትሌቶች ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ በላይነሽ ኦልጂራ (32:53) 8ኛ፣ ሰንበሬ ተፈሪ (33:12) 10ኛ፣ ገበያነሽ አየለ (33:30) 13ኛ እና ስንታየሁ ለውጠኝ (33:33) 14ኛ በመውጣት የቡድን የብር ሜዳልያን አስገኝተዋል፡፡ ዘርፌ ልመንህ ዘርፌ ልመንህ (34:59) 26ኛ ሆና ስታጠናቅቅ በጃን ሜዳው አግር አቋራጭ ውድድር ላይ አሸናፊ የነበረችው ዴራ ዲዳ ሳትጨርስ ቀርታለች፡፡

የአዋቂ ወንዶች 10 ኪ.ሜ. የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

የአዋቂ ወንዶች 10 ኪ.ሜ. የቡድን የሜዳልያ አሸናፊ ቡድኖች ሽልማት

የእለቱ የመዝጊያ ውድድር የሆነው የአዋቂ ወንዶች 10 ኪ.ሜ. ፉክክር ኡጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጊ ብስለት በጎደለው አስገራሚ አካሄድ የአዘጋጇን ሀገር ደጋፊዎች ተስፋ እጅግ ከፍ ካደረገ በኋላ ውድድሩን ሊጨርስ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው በኬንያዊው ያለፈው ሻምፒዮና ባለክብር ጆኦፍሬይ ካምዎሮር የተመቀደመበት እና ቀሪውን ርቀትም በአሰቃቂ አሯሯጥ በመፈፀም መልሶ ያቀዘቀዘበት ነበር፡፡ የ2017 የኡጋንዳ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና አሸናፊ የሆነው ቼፕቴጊ ከውድድሩ አጋማሽ ጀምሮ ፍጥነቱን ጨምሮ ሲወጣ ኬንያዊው ካምዎሮር በቅርብ ርቀት የተከተለው ቢሆንም በደጋፊዎቹ ከፍተኛ ጩኸት ተነሳስቶም ውድድሩ ሶስት ኪሎ ሜትር ያህል እየቀረው አቅሙን ባላማከለ መልኩ ይበልጥ በመፍጠን ከካምዎሮር ጋር የነበረውን ልዩነትም ማስፋት ችሎ ነበር፡፡ ኡጋንዳ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ድል ልታስመዘግብ በጣም እንደቀረበች በታመነበት ቅፅበት ግን የቼፕቴጊ አቅም በፍጥነት ወርዶ በካምዎሮር ከመታለፉም በተጨማሪ በመሮጥ እና መራመድ መካከል የሆነ አሯሯጥ ውስጥ ለመግባት ተገዶ ታይቷል፡፡ በመሪነቱ ስፍራ ላይ የተከሰተው ለውጥ ከፍተኛ የድጋፍ ጩኸት ላይ የነበሩትን ኡጋንዳውያን ደጋፊዎችን ፀጥ ያስደረገ ሲሆን ከውድድሩ በፊት የአሸናፊነቱን የቅድሚያ ግምት አግኝቶ የነበረው ካምዎሮርም ከሁለት ዓመት በፊት ቻይና ጉያንግ ላይ ያስመዘገበውን የአሸናፊነት ክብር ያስጠበቀበትን ድል ተጎናፅፏል፡፡ ጆኦፍሬይ ካምዎሮር ውድድሩን በአንደኛነት ለማጠናቀቅ 28 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ የፈጀበት ሲሆን እርሱን በመከተል የሀገሩ ልጅ ሊኦናርድ ባርሶቶን (28:36) እና ኢትዮጵያዊው አባዲ ሀዲስ (28:43) ቀሪዎቹን የሜዳልያ ደረጃዎች ወስደዋል፡፡ ጀማል ይመር 4ኛ፣ ሙክታር እድሪስ 6ኛ እና ኢብራሂም ጄይላን 8ኛ ሆነው በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ኬንያን በአንድ ነጥብ በልጣ የቡድን የወርቅ ሜዳልያውን የአሸናፊነት ደረጃ እንድታገኝ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው በዚህ ፉክክር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ቦንሳ ዲዳ 10ኛ ጌታነህ ሞላ 18ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከሁለት ዓመት በፊት በኬንያ ላይ የበላይነቷን አሳይታ የነበረችው ኢትዮጵያ በ4 የወርቅ 4 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳልያ በኬንያ የአንድ የብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳልያ ብልጫ ተወስዶባት በሜዳልያ ደረጃ ሰንጠረዡ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ የአትሌቶቻችንን ጥረት እና ያስመዘገቧቸውን የሜዳልያ ድሎች በየትኛውም ግዜ ቢሆን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ በሜዳልያ ቁጥር ተበላልጦ ቀዳሚ እና ተቀዳሚ መባሉም እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ በኩል በተለይም በአዋቂዎች ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም የተለመዱት የተናጠል የወርቅ ሜዳልያዎች ስኬት መራቅ በደንብ ታስቦበት መፍትሔ ሊበጅለት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ሳንጠቁም ማለፍ አንፈልግም፡፡ ከዕድሜ ትክክለኛነት ጋር በተያያዘ በአፍሪካውያን አትሌቶች ላይ የሚነሳው ጥያቄ እኛንም የሚመለከት ከመሆኑ አኳያ፣ በሀገር ውስጥ (በተለይም በታዳጊ እና የወጣቶች) ውድድሮች ላይም ችግሩ በተጨባጭ የሚታይ ከመሆኑ አንፃር እንዲሁም በወጣቶች ደረጃ ውጤታማ እየሆንን በታዳጊና ወጣቶች ውድድር ላይ ውጤት የሚያስመዘግቡት አትሌቶቻችን ወደአዋቂዎች ምድብ ተሸጋግረው ስኬታማ ሲሆኑ የምንመለከትባቸው አጋጣሚዎች እጅግ በጣም አናሳ እየሆኑ ከመምጣታቸው አንፃር አዲሱ የፌዴሬሽን አመራር ሊሰራቸው የሚገቡት ብዙ የቤት ስራዎች እንዳሉ አመላካች ነው፡፡ ስለሆነም በቅርብ ግዜ ለሚካሄዱት ውድድሮች ባለን ከመዘጋጀታችን ጎን ለጎን በረጅም ግዜ ዕቅድ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና ወደስኬቱ ጎዳና ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል፡፡

በካምፓላው ውድድር ላይ ከተመለከትናቸው ሁኔታዎች አንፃርም ሀገራችን ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የማስተናገድ ፍላጎቷን የዓለም አገር አቋራጭ ውድድርን ለማዘጋጀት በመጠየቅ እውን ልታደርግ እንደምትችል መጠቆም እንወዳለን፡፡ ለዚህም አስፈላጊዎቹ ማስተካከያዎች ተደርገውለት በአሁኑ ሰዓት ቦታው በተለያዩ ምከንያቶች እየተሸራረፈ የሚገኘው የጃን ሜዳ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ አያንስም፡፡ በፌዴሬሽኑ የአመራር ኃላፊነት ላይ የተቀመጡትና በስፖርቱ ውስጥ የገዘፈ ስምና ዝና ያላቸው እንደ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ እና አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማሪያም አይነቶቹ ግለሰቦችም ጥያቄው በዓለም አቀፉ አካል ተቀባይነት እንዲያገኝ የበኩላቸውን ከፍተኛ የማሳመን ስራ መስራት ይችላሉ፡፡

51 አገሮች የተሳተፉበት የካምፓላው የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር ሲጠናቀቅ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻሉት ስድስት አገሮች ብቻ ሲሆኑ በውድድሩ ላይ ለአሸኛፊዎች ከተዘጋጁት 27 ሜዳልያዎች መካከል ቱርክ እና ባሕሬይን ካገኟቸው የቡድን የነሐስ ሜዳልያዎች ውጪ 25ቱ በምስራቅ አፍሪካዎቹ አገራት (ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ እና ኤርትራ) ተወዳዳሪዎች ተወስደዋል፡፡ በአዋቂዎቹ የተናጠል ውድድር ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ያጠናቁቀት አትሌቶች በቅደም ተከተላቸው መሰረት 30000፣ 15000፣ 10000፣ 7000፣ 5000 እና 3000 ዶላር የሚያገኙ ሲሆን የአዋቂዎቹ ምድብ የቡድን አሸናፊዎችም በተቀመጠው የሽልማት ዝርዝር መሰረት 20000፣ 16000፣ 12000፣ 10000፣ 8000 እና 4000 ዶላር ያገኛሉ፡፡ በድብልቅ ሪሌ ውድድር ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ያጠናቀቁትም 12,000፣ 8000፣ 6000 እና 4000 ዶላር ይሸለማሉ፡፡

በ42ኛው የአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የተመዘገቡ የሜዳልያ ደረጃዎች

ድብልቅ ሪሌ 8 ኪ.ሜ.
1ኛ. ኬንያ 22:22
2ኛ. ኢትዮጵያ 22:30
3ኛ. ቱርክ 22:37

ከ20 ዓመት በታች ሴቶች 6 ኪ.ሜ.
1ኛ. ለተሰንበት ግደይ (ኢትዮጵያ) 18:34
2ኛ. ሀዊ ፈይሳ (ኢትዮጵያ) 18:57
3ኛ. ሴልፊኔ ቼፕቴኬ (ኬንያ) 19:02
4ኛ. ሼዪላ ቼላንጋት (ኬንያ) 19:12
5ኛ. ሴልፊኔ ቼፕቴኬ (ኬንያ) 19:16
6ኛ. ፎቴይን ተስፋዬ (ኢትዮጵያ) 19:24

የቡድን ውጤት
1ኛ. ኢትዮጵያ በ19 ነጥብ
2ኛ. ኬንያ በ20 ነጥብ
3ኛ. ኡጋንዳ በ63 ነጥብ

ከ20 ዓመት በታች ወንዶች 8 ኪ.ሜ.
1ኛ. ጃኮብ ኪፕሊሞ (ኡጋንዳ) 22:40
2ኛ. አምደወርቅ ዋለልኝ (ኢትዮጵያ) 22:43
3ኛ. ሪቻርድ ያቶር ኪሙንያን (ኬንያ) 22:52
4ኛ. በተስፋ ጌታሁን (ኢትዮጵያ) 22:58
5ኛ. ሰለሞን ባረጋ (ኢትዮጵያ) 23:03
6ኛ. ተፈራ ሞሲሳ (ኢትዮጵያ) 23:04

የቡድን ውጤት
1ኛ. ኢትዮጵያ በ17 ነጥብ
2ኛ. ኬንያ በ28 ነጥብ
3ኛ. ኤርትራ በ55 ነጥብ

አዋቂ ሴቶች 10 ኪ.ሜ.
1ኛ. ኢረኔ ቼፔት (ኬንያ) 31:57
2ኛ. አሊስ አፕሮት (ኬንያ) 32:01
3ኛ. ሊሊያን ካሳዪት (ኬንያ) 32:11
4ኛ. ሄይቪን ኪገን (ኬንያ) 32:32
5ኛ. አንገስ ጄቤት ቲሮፕ (ኬንያ) 32:32
6ኛ. ፌይዝ ኪፕዬጎን (ኬንያ) 32:49

የቡድን ውጤት
1ኛ. ኬንያ በ10 ነጥብ
2ኛ. ኢትዮጵያ በ45 ነጥብ
3ኛ. ባሕሬይን በ59 ነጥብ

አዋቂ ወንዶች 10 ..
1ኛ. ጆኦፍሬይ ካምዎሮር (ኬንያ) 28:24
2ኛ. ሊኦናርድ ባርሶቶን (ኬንያ) 28:36
3ኛ. አባዲ ሀዲስ (ኢትዮጵያ) 28:43
4ኛ. ጀማል ይመር (ኢትዮጵያ) 28:46
5ኛ. አሮን ክፍሌ (ኤርትራ) 28:49
6ኛ. ሙክታር እድሪስ (ኢትዮጵያ) 28:56

የቡድን ውጤት
1ኛ. ኢትዮጵያ በ21 ነጥብ
2ኛ. ኬንያ በ22 ነጥብ
3ኛ. ኡጋንዳ በ72 ነጥብ

የሜዳልያ ሰንጠረዥ

ደረጃ አገር ወርቅ ብር ነሐስ አጠቃላይ
1 ኬንያ 4 5 3 12
2 ኢትዮጵያ 4 4 1 9
3 ኡጋንዳ 1 0 2 3
4 ቱርክ 0 0 1 1
4 ባሕሬይን 0 0 1 1
4 ኤርትራ 0 0 1 1

 

Continue Reading
Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የ5000ሜ ፉክክር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በአሸናፊነት አጠናቀዋል

Published

on

Dawit-Seyaum-1
ትላንት ምሽት በኖርዌይ ኦስሎ በተከናወነው የዳይመንድ ሊግ 5000 ሜ. ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉትን ደረጃዎች በመቆጣጠር አሸንፈዋል፡፡ 

በዝናባማ የአየር ሁኔታ ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፉክክር ዳዊት ስዩም በመጨረሻዎቹ መቶ ሜትሮች ውስጥ ፍጥነቷን በመጨመር ጉዳፍ እና ለተሰንበትን ቀድማ አንደኛ ወጥታለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሪገን 2022 የአለም ሻምፒዮና ከመረጣቸው ዕጩ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተችው ዳዊት በኦስሎ ያሸነፈችበት 14፡25.84 የሆነ ሰአት የራሷ ምርጥ ሲሆን እጅጋየሁ ታዬ (14.12.98) እና ለተሰንበት (14፡24.59) ባለፈው ወር በዩጂን ካስመዘገቧቸው በመቀጠልም የዘንድሮ የአለም ሶስተኛው ፈጣን ነው፡፡ በውድድሩ ላይ ከነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን መካከል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርቀቱ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ያደረገችው አልማዝ አያና በ14:32.17 ስድስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ ሀዊ ፈይሳ በ14:33.66፣ ፅጌ ገብረሰላማ በ14:43.90፣ እና አበራሽ ምንሴዎ በ14:47.98 በቅደም ተከተል ሰባተኛ፣ አስረኛ እና አስራ አንደኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ ሶስቱም ያስመዘገቡት ሰዓት የራሳቸውን ምርጥ ያሻሻሉበት ሆኗል፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ እ.ኤ.አ. በጁን 2008 ዓ.ም. ያስመዘገበችውና 14:11.15 የሆነው የኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 5000 ሜትር የውድድር ስፍራ ሪከርድ ይሰበራል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡  
ዳዊት ስዩም ውድድሩን በድል ካጠናቀቀች በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠችው አስተያየት ‹‹ዛሬ ለእኔ ደስታን ስላመጣልኝ በውድድሩ ሰዓት የነበረውን ዝናብ ወድጄዋለሁ ማለት እችላለሁ፡፡ ጠንካራ ተፎካካሪዎች የነበሩበት ከባድ ውድድር ነበር እናም ሁሉንም ለማሸነፍ በቅቻለሁ። በርቀቱ የራሴን ምርጥ ሰዓት ማሻሻል መቻሌም አስፈላጊ ነበር፡፡ በስታድየሙ ውስጥ በከፍተኛ ስሜት ድጋፍ ይሰጡን የነበሩ ወገኖቻችን ነበሩ። ለሰጡን ድጋፍ እናመሰግናለን።›› ብላለች፡፡
 
በኦስሎ የወንዶች 5000 ሜትር የመጨረሻ ፉክክሩ በኢትዮጵያውያኑ ጥላሁን ሀይሌ እና ሳሙኤል ተፈራ መካከል የነበረ ሲሆን ጥላሁን የ1500 ሜትር ስፔሻሊስቱ ሳሙኤልን በአጨራረስ ፍጥነት ቀድሞ በ13:03.51 በአንደኛነት አጠናቋል፡፡ ሳሙኤል ተፈራ የራሱ ምርጥ በሆነ 13:04.35 ሁለተኛ ሲወጣ ጌትነት ዋለ የግሉ የዓመቱ ምርጥ በሆነ 13:04.48 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። በውድድሩ ላይ የነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሚልኬሳ መንገሻ በ13:05.94 አምስተኛ እንዲሁም አሊ አብዱልመናን የራሱ ምርጥ በሆነ 13:16.97 አስረኛ ወጥተዋል፡፡
ጥላሁን ሀይሌ ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠው አስተያየት ‹‹ሶስት ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘን መጨረስ መቻላችን ጥሩ አፈጻጸም ነበር። እየጠነከርኩ እንደሆነ የተሰማኝ ሲሆን በውድድሩ እና ባስመዘገብኩት ሰዓትም ተደስቻለሁ። ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ ስለነበኩ ወደ አሸናፊነቱ መመለስ መቻሌ በጣም ጥሩ ነው።›› ብሏል፡፡

በኦስሎ የሴቶች 800ሜ. ውድድር ላይ ተፎካካሪ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ድሪቤ ወልቴጂ በ1፡58.69 አምስተኛ ሆና አጠናቃለች።
Continue Reading

Articles

የዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ሻምፒዮና በእኔ እይታ

Published

on

IMG_0110
ከመጋቢት19-24/2014 ዓ.ም በሐዋሳ አለም አቀፍ ስቴድዮም የተደረገው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሞላ ጎደል ስኬታማ በሚባል ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ከአምስት አመት በኋላ በድጋሚ በአካል በመገኘት ስለተከታተልኩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና የግል ምልከታዬን እንደሚከተለው አጠናቅሬዋለሁ፡፡

የበለጠ ትኩረትን በሳቡት ውድድሮች ዙሪያ የተመዘገቡ ውጤቶችን በወፍ በረር በመዳሰስ ስጀምር ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የመጨረሻ ቀን የወንዶች 5000ሜ. የአለም ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና የ3000ሜ የብር ሜዳልያ አሸናፊው አሊ አብዱልመና 13፡45.0 በሆነ ሰዓት ከጥላሁን ሀይሌ፣ ጌትነት ዋለ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ቀድሞ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የፉክክሩ አካል የነበረው እና የርቀቱ የወቅቱ የአለም ሻምፒዮን ሙክታር እድሪስ ስድስተኛ ወጥቷል። 

ከ20 ዓመት በታች የ3000ሜ የአለም ሻምፒዮኑ ታደሰ ወርቁ በ28፡12.0 የወንዶች 10,000ሜ. ሻምፒዮን ሲሆን በ1996 ዓ.ም. በአትሌት ስለሺ ስህን ተመዝግቦ የነበረውን 28፡16.23 የሆነ የሻምፒዮናው ሪኮርድ ለማሻሻልም በቅቷል፡፡ በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፉክክር ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በቀዳሚነት የጨረሰችበት 31፡21.5 የሆነ ሰዓት አዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በርቀቱ የከዚህ ቀደሙ ሪኮርድ ለተሰንበት ግደይ ከሶስት ዓመት በፊት ያስመዘገበችው 32፡10.13 የሆነ ሰዓት ነበር፡፡

ሳሙኤል ፍሬው በዘንድሮ የወንዶች 3000ሜ. መሰናክል አፈፃፀም ከአለም ሁለተኛው ፈጣን በሆነ 8፡22.5 ሰዓት አሸናፊ ሲሆን ጌትነት ዋለ ከአራት ዓመት በፊት አስመዝግቦት የነበረውን 8፡28.98 የነበረ የሻምፒዮናው ሪኮርድም አሻሽሏል፡፡ በሴቶች 3000ሜ. መሰናክል ከ800ሜ ወደ ረጅም ርቀት የተሸጋገረችው ወርቅውሃ ጌታቸው በ9፡41.8 ሰዓት መቅደስ አበበን (9:43.8) በማስከትል በአሸናፊነት አጠናቃለች። 

አድሃና ካህሳይ (3:51.0) የወንዶች 1500ሜ ፉክክሩን በበላይት ሲያጠናቅቅ በሴቶች 1500 ሜ አያል ዳኛቸው (4:10.0) ተጠባቂዋ ዳዊት ስዩምን (4:11.1) በመቅደም በአንደኛነት አጠናቃለች። በ800ሜ. ወንዶች ቶሌሳ ቦደና (1:47.1) በሴቶች ወርቅነሽ መሰለ (2:02.1) አሸናፊ ሆነዋል።
ዮብሰን ብሩ በ400ሜ/400ሜ መሰናክል (45.9/50.5) ድርብ ድል ሲቀዳጅ፣ በወንዶች ጦር ውርወራ ኡታጌ ኡባንግ ብሔራዊ ሪኮርድ በሆነ 73.28ሜ. አሸንፏል፡፡ የኋልዬ በለጠው እና ዮሃንስ አልጋው በእርምጃ ሩጫ የሻምፒዮንነት ክብርን ተቀዳጅተዋል።

ጥቂት አስተያየቶች፡-
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪ እንደሆነ እና ለዕድገቱ እንደሚቆረቆር ሰው በብሔራዊ ሻምፒዮናው ላይ ስለተመለከትኳቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ጥቂት አስተያየቶቼን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡-

አዎንታዊ ጎኖች
• ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉትን ተግዳሮቶች በሙሉ በመቋቋም ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ከአዲስ አበባ ውጭ አካሂዶ በሰላም ማጠናቀቅ መቻሉ አንደኛው ስኬቱ ነው፡፡

• በሻምፒዮናው ላይ ጥቂት የማይባሉ ታዋቂ አትሌቶች በሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ፉክክር ላይ ተሳታፊ ሆነው ሲወዳደሩ መመልከት የተቻለ ሲሆን በተለይም በወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ላይ የታየው የኮከብ አትሌቶች ፉክክር ልዩ ነበር፡፡

• በውድድሩ ወቅት ለአትሌቲክስ ዳኞች የብቃት ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱም የውድድሩን ጥራት ለማሳደግ የሚረዳ እንደመሆኑ እሰየው የሚባል ነው፡፡
 
• እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሉት ክለቦች ለአትሌቲክስ ስፖርት የበለጠ ትኩረት በመስጠትና ተጠናክሮ በመቅረብ ከዚህ ቀደም በጠንካራነታቸው ከሚታወቁት መከላከያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የቅርብ ተፎካካሪ ሆነው መታየት፤ የኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ፖሊስ እና ሲዳማ ቡና ክለብ አትሌቶችም ጠንካራ ተሳትፎ ሳይዘነጋ የሻምፒዮናው ፉክክር ድምቀት ነበሩ፡፡ 
• የአንዳንዶቹ ተገቢነት አጠያያቂ ቢሆንም ብዛት ያላቸው የሻምፒዮናው ሪኮርዶች የተሻሻሉበት ውድድርም ነበር፡፡ 

አሉታዊ ጎኖች
• የሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ውድድር ውጤት አሁንም በኤሌክትሮኒክስ የሰዓት መቆጣጠሪያ የማይደገፍ መሆኑ በተለይም በአጭር ርቀት እና በሜዳ ላይ ተግባራት ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ልፋት ተገቢውን እውቅና እንዳያገኝ እያደረገ ይገኛል፡፡ የሻምፒዮናውን ውጤቶች በዘመናዊ እና ዓለም አቀፉን መለኪያ በሚያሟላ መልኩ አለመያዝ በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ ለተሳትፎ የሚያበቁ ውጤቶችን በማስመዝገቡ ረገድ የሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ አሁንም መፍትሄ ያልተበጀለት ጉዳይ ነው፡፡ 
 
• የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ሚዲያ/ለአጠቃላዩ ሕዝብ የሚያስተላልፈው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶችን ውጤት ብቻ መሆኑ አወዳዳሪው አካል የሚያደርገውን የራሱን ውድድርም ሆነ አትሌቶቹ የለፉበትን ውጤት ከማስተዋወቅ አኳያ በቂ አይደለም፡፡
 
• በወንዶች የጦር ውርወራ እና የሴቶች ምርኩዝ ዝላይ ብሔራዊ ሪኮርዶች እንደተመዘገቡ ይታመናል፤ በሴቶች 100ሜ መሰናክል እና የወንዶች 400ሜ መሰናክል የተመዘገቡት ሰዓቶችም የምንግዜውም ፈጣን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውድድሩ በኤሌክትሮኒክስ ታይሚንግ ያልተደገፈ እና የንፋስ ንባብ ያልነበረው መሆኑ ውጤቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።

• በ20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታዎች የተመዘገቡት ሰዓቶች ከሚጠበቀው በላይ እጅግ በጣም ፈጣን እና እውነታዊ አለመምሰላቸው በውድድሩ ላይ የተፈጠረ አንዳች ስህተት መኖሩን የሚያመላክቱ መሆኑ፡፡ እንዲህ አይነት ለማመን የሚከብዱ እና ጥርጣሬን የሚፈጥሩ አይነት ውጤቶች ሲመዘገቡም የተፈጠረ ስህተት መኖር አለመኖሩን ለማጣራት አለመሞከሩ፡፡
   
• የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ ለውድድር የማይፈቀድ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማን በመጠቀም የተመዘገበ ውጤት በሪኮርድነት ጭምር ተይዞ መፅደቁ። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከተከለከሉ ጫማዎች ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ሕገ ደንቦችን ማወቅና መተግበር ቢገባውም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ የተከሰተው ነገር የውድድር ሕገ ደንቦቹ መረጃ በፌዴሬሽኑ ውስጥ በትክክል የተሰራጩ እንዳልሆነ የሚያመላከት ነው፡፡ 

• በሴቶች 1500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይ አትሌት ዳዊት ስዩም የሻምፒዮናውን ሪኮርድ ያሻሻለችበት ውጤት እንደተመዘገበ በውድድሩ ወቅት በተደጋጋሚ ሲነገር ከተደመጠ በኋላ ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውጤቱ በሐዋሳው ውድድር ላይ ተሻሻሉ ከተባሉት የሻምፒዮናው አዲስ ሪኮርዶች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም የፌዴሬሽኑን ግልፀኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ለረጅም ግዜ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች በቅርበት ከመከታተሌ አንፃር በራሴ እይታ ያስቀመጥኳቸው እንደመሆናቸው አንዳንዶቹ ሀሳቦች አከራካሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የውድድር ደንቦችን በአግባቡ ከማስፈፀም አኳያ በታዩት ክፍተቶች ዙሪያ ምንም የሚያከራክር ጉዳይ ስለሌለ በወቅታዊ የውድድር ደንቦች ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት ላለባቸው የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ አስፈላጊውን ገለፃ እና ትምህርት መስጠት የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት ነው፡፡ ከውድድር ጋር የተያያዙ ደንቦችን ከመጣስ አኳያ በሀገር ውስጥ በሚደረጉ ውድድሮች እንደቀላል ነገር የሚታለፉ ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም ተደግመው እንደግል አትሌቶችን እንደቡድን ሀገርን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍሉ ይችላሉና አስፈላጊው ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ባለፈው መስከረም ወር በቪየና ሲቲ ማራቶን ውድድሩን በአሸናፊነት ጨርሶ የነበረው ኢትዮጵያዊው ደራራ ሁሪሳ የገጠመውን አንዘንጋው! 

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመልካም ጎኑ ስሟ እንዲነሳ በሚያደርገው እና በትልልቅ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ የኩራታችን ምንጭ በሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት እንደጎረቤታችን ኬንያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ የብቃት ደረጃ ላይ ደርሰን ማየት የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንም የውድድሮቹን ጥራት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ።   
   
የ10,000ሜ. አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር (Photo by EAF)

በመጨረሻም በሀዋሳ በተካሄደው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመሮጫ ጫማ ጋር የተያያዙ ደንቦችን በማስከበሩ ረገድ የተፈጠረውን ክፍተት እንደማስተማሪያ ብንጠቀምበት በሚል የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ፡-

የመሮጫ ጫማ ደንቦች ለትራክ ውድድር

64 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የዘንድሮ የራስ አል ካይማህ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በሐዋሳ በተከናወነው 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 31 ደቂቃ ከ21.5 ሰከንድ  በመግባት የ10,000ሜ. አሸናፊ ሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ዓለም አቀፉን ደንብ ከግምት ባላስገባ ሁኔታ ውጤቱን በአዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድነት ጭምር አፅድቆት አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ መጋቢት 20/2014 በተደረገው የሴቶች የፍፃሜ ፉክክር ላይ በኢትዮጵያ ምድር የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሰዓት የሆነው ውጤት በአለም አትሌቲክስ ዘንድ እውቅና ሊሰጠው የማይችል ነው።

ለምን?

አትሌቷ የሶል ውፍረቱ 40ሚሜ የሆነ ዙምኤክስ ቬፐርፍላይ (ZoomX Vaporfly) ጫማ አድርጋ በመወዳደሯ ምክንያት።

ደንቡ ምን ይላል?

በትራክ ውድድሮች ላይ የሚፈቀደው ከፍተኛው የሶል ውፍረት ፡-
– 20ሚሜ ከ 800ሜ በታች ለሆኑ ውድድሮች እና ለሁሉም የሜዳ ላይ ተግባራት (ከስሉስ ዝላይ በስተቀር)

– 25ሚሜ ለ800ሜ እና ከዛ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ

– 40ሚሜ ለትራክ ላይ የእርምጃ ውድድሮች

እነዚህ ደንቦች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 31, 2024 ድረስ በሥራ ላይ ይውላሉ። ከኖቬምበር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ለ800ሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ የሚፈቀደው ከፍተኛ የሶል ውፍረትም ወደ 20 ሚሜ ዝቅ የሚል ይሆናል።

የትራክ ላይ መወዳደሪያ ስፓይክ ጫማ ከሌለኝስ?  

ደንቡ የጎዳና ላይ የመሮጫ ጫማዎች በትራክ ላይ እንዳይደረጉ አይከለክልም ነገር ግን በ25 ሚሊ ሜትሩ ገደብ ምክንያት 30 ሚሜ ወይም 40 ሚሜ የሆኑ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማዎች በትራክ ውድድሮች ላይ እንዲደረጉ አይፈቅድም፡፡

ለበለጠ መረጃ :-
https://www.worldathletics.org/news/press-releases/new-athletic-shoe-regulations-approved-2022

Continue Reading

Opinions

On the TPLF’s Love Affair With ‘Genocide’

Published

on

WhatsApp-Image-2021-11-04-at-12.41.51-AM
Ethiopia's Lalibela, a UN World Heritage Site, now under Tigrayan forces control

Today, the joint investigation report by the Ethiopian Human Rights Council and the UNHR
on human rights violations committed in Tigray concluded that there is no evidence that genocide has taken place so far. While this is a bit of a setback for the TPLF, which has wanted the world to believe—since the 1990s, even as the TPLF was dominating power in Addis—that a genocide has been perpetrated against the people of Tigray, unfortunately the group still appears to be determined to make genocide a reality. This is confusing for people who don’t understand why the TPLF is obsessed with genocide, why its internet cadres began using #TigrayGenocide in April 2020, months before the war began. So many weapons have been deployed in this war, and among them: confusion and obfuscation.


In the past several months and more so in the past few weeks, we have been getting
testimony after testimony from allied Amhara forces fighting the TPLF that Tigrayan residents of cities in Wollo have been collaborating with the TPLF by a) attacking ENDF and allied forces from behind; b) forcing ENDF and allied forces to withdraw from towns and cities afraid of committing large scale massacres by firing back at the civilians (Tigrayans) firing at them; c) helping the TPLF locate and execute young Amharas believed to be a threat; and d) in at least one horrifying account by an IDP who managed to escape occupied territories, handing TPLF soldiers a list of women to rape. Another shocking development in the past several months has been the widespread use of child soldiers by the TPLF, which, according to experts who have studied the practice, is an “alarm bell” calling attention to possible plans to commit mass atrocities. The use of child soldiers by the TPLF and its attendant implications, along with the widespread deployment of civilian sleeper agents in Amhara cities the TPLF has taken over, serves to create an overall perception of every Tigrayan as a potential enemy, sowing fear and mistrust.

Many Ethiopians are looking at this and wondering: why are Tigrayan elites on the internet
either celebrating the TPLF’s advance via these toxic methods or silent about all this? How can they not see how dangerous this is for everyone, especially for Tigrayans who live outside Tigray? How can they not see that there is no “winning” after stoking all this lasting animosity? Do Tigrayan elites not understand that there can be no justice for Tigray—whether Tigray secedes or not—unless there is justice for her neighbors, for Tigray does not exist in a vacuum? The questions are being asked but nobody is answering them. Our academic class has largely failed to offer viable analyses of the ideas driving this war, as they failed over the past fifty years in regards to coming up with a fitting paradigm for understanding Ethiopia’s unique situation.


Here is my humble attempt to explain what I think is happening with the TPLF’s obsession
with—and with its active attempt to inspire—genocide:


The most successful psychopaths in any field understand that, in order to win anything, one
must risk everything, including the very thing one is supposedly fighting for. In the case of the
TPLF (and associated Tigrayan political elites), whose motto appears to be “give me supremacy or give me death,” that “everything” they are risking is the lives of ordinary Tigrayans in whose names they are fighting. We have seen over the past several months the extent to which the TPLF is willing to go to sacrifice ordinary Tigrayans in order to get what it wants: wave after wave after wave of young poorly armed and inexperienced Tigrayans were unleashed upon ENDF and Amhara and Afar forces in order to force the latter to waste ammunition and energy before the more experienced soldiers are sent.


So, for a political group who sends tens of thousands, if not hundreds of thousands, of
young Tigrayans towards open fire, violence against hundreds of thousands of Tigrayans is nothing if it means the TPLF will in the end win the “prize” it has been obsessed with for decades: genocide. You see, merely attaining power in Addis Ababa is not enough for the TPLF, whose core driving ideology is Tigrayan supremacy. Power is temporary; anybody can take it away from you, and the 2018 uprisings demonstrated that. Genocide is forever. Nobody can take away from you the story of genocide committed against your people.


The TPLF looked at countries like Israel and Rwanda and realized what a potent instrument
genocide is for establishing perpetual minority rule. We have some indications suggesting that the TPLF views Israel as a model. When the war between Ethiopia and the TPLF began in November 2020, Sekoutoure Getachew, a TPLF official, went on TV to tell us that the TPLF’s decision to launch a preemptive attack on the Northern Command was inspired by how the young state of Israel, feeling threatened by her neighbors, launched preemptive attacks against them in the “six-day war” of 1967. Another indication is the manner in which the TPLF, during its 27 years in power, invested heavily in creating a wealthy and strongly networked Tigrayan diaspora which has been used to lobby and influence western governments and organizations much in the same way as the Jewish diaspora aids the state of Israel. The TPLF has figured out that truth does not matter in politics, especially in international politics. If you have the wealth and the personnel to peddle your preferred narrative, if you have the military power to subdue the people you want to subdue, if you are willing to make concessions to external forces (US, Egypt, etc), you can do unspeakable things to others (much like the state of Israel does to Palestinians) and still manage to portray yourself as the victim.
This calculation is so far working for the TPLF, but nothing would seal the deal like the actual
commission of genocide—or something that looks like it—against Tigrayans. As we have seen over the past twelve months, western governments and organizations have shown their willingness to adopt TPLF’s narratives without scrutiny and can easily reward the TPLF with its much pursued prize, genocide, even if actual genocide doesn’t take place.


But why does the TPLF need genocide to establish minority rule? Because, as we saw in their
first tenure in power, you can only rule with an iron fist for a limited period of time. Leaders of the TPLF are adherents of Tigrayan supremacy: the idea that Tigrayans, as the “only” heirs of the Axumite empire, are the natural rulers of the Ethiopian state, and cannot be ruled by “barbarians” south of them. The only acceptable power arrangement for the TPLF is one in which Tigrayans are either directly dominating political power or are the perpetual kingmakers pulling all the major strings. Anything outside that, any system that forces Tigrayans to live on equal footing with everyone else, is unacceptable. And this kind of domination by a minority cannot coexist with a democratic system that the majority of Ethiopians clearly prefer. So, the TPLF needs something more potent than pure political/economic/military power to justify bypassing democracy to establish itself as the permanent ruler/kingmaker of Ethiopia. It needs a new and powerful raison d’être to justify its domination not just to Tigrayans and the rest of Ethiopians but, and most importantly, to the rest of the world. If a genocide were to be committed against Tigrayans (or if the U.S. decides to reward the TPLF with the genocide label even in the absence of it), then the TPLF can license itself to impose all manner of drastic measures aimed at “protecting Tigray and
Tigrayans.” This could be anything from redrawing internal borders (and taking debilitating
measures against the peoples whose lands are being robbed—most likely Amharas and Afaris—so that they will never be in a position to assert themselves) to ethnic cleansing and genocide against populations considered to be a threat. And when you oppose it, the TPLF will say “you committed a genocide against Tigrayans” over and over and over, and its western backers will repeat the same chorus. If they have been this loud over a non-existent genocide over the past twelve months, just imagine what it would be like if the U.S. or UN rewards them with that label.


And this is where the Ethiopian government’s major dilemma comes from: if ENDF and
Amhara forces fight to regain their cities and towns, they risk committing large scale massacres. The TPLF networks reported to be operating within these cities wear civilian clothing and fire at the armies from inside civilian establishments, in an apparent attempt to set up pro-Ethiopia forces. Pro-Ethiopia forces are essentially being dared to commit large scale massacres in order to win back their own cities. So far, they are choosing to withdraw from these towns and cities. But that is another problem: not only is the TPLF committing unspeakable violence against civilians and destroying infrastructure in those cities, the takeovers are emboldening it to continue pressing, giving young people back in Tigray false hope that they are winning and—this is very important—the false idea that they are being “welcomed” by locals in those cities. Then more and more and more young Tigrayans are sent to their deaths.


So the Ethiopian government is stuck between a rock and a hard place. One option is
allowing its forces to do whatever it takes to take back territory, thereby offering protection to its citizens in Wollo and elsewhere, but also risking the “genocide” label by western governments who have been eagerly waiting for such an opportunity so that they can blackmail the government into submitting itself to their wishes on GERD and other issues. Option two is avoiding large scale violence and allowing the TPLF to take power in Addis Ababa and do to Ethiopia what it wishes. One of the things it might do to Ethiopia, according to its leaked strategy document, is force a confederation that will no doubt privilege some states, i.e. Tigray, more than others, and that will no doubt be designed to subdue some populations—mainly Amharas and Afaris—who are considered obstacles to Tigray’s aspirations of domination and expansion (in the TPLF’s original manifesto, Afar is claimed as Tigray land).


And there is absolutely no doubt that the TPLF will make big concessions on the GERD in
order to compensate its western and Egyptian backers, if not redraw borders to make Benishangul Gumuz Tigrayan territory. If you think this is wild, read about the history of the state of Israel, the TPLF’s model state. The redrawing of borders that the TPLF undertook in 1991 was also wild at the time; people don’t think of it as outrageous anymore because the fact that they held onto the territory for 30 years has normalized the event in our minds. And that’s all the TPLF needs: another thirty years to normalize all the outrageous things they will do next.

One may argue that this is a false dichotomy, that there is a third or even maybe fourth option: winning these cities back without mass violence much in the same way the ENDF managed to do during its first campaign in Tigray. We all should pray for such a miracle, of course. However, one can also say that in the early days of the war, the TPLF was mostly withdrawing from Tigrayan cities to avoid urban warfare. And even when they engaged in urban warfare, it was not at the same scale and intensity as has been the case over the past four and half months or so. Starting in mid June, the TPLF’s use of civilians as human shields and fighters stopped being just another weapon in its arsenal and became a center of its operations. The near collapse of the ENDF inside Tigray right before its withdrawal was precipitated by the TPLF’s intensified use of “civilians” to trap the ENDF. Many ENDF soldiers chose to surrender rather than fire at those “civilians.” It is still possible to avoid large scale violence in the attempt to retake towns in Wollo, but the risk for it is very high, and is possibly behind the federal government’s reluctance to take decisive actions.


The point is: barring miracles, the Ethiopian government is positioned to lose something
one way or another. All that is left is choosing its preferred poison. Perhaps one thing to consider for the federal government is: the rights of Amharas and Afaris to defend themselves against the existential threats posed against them by the TPLF is much bigger than the national government’s concerns about its place and relationships with the rest of the world. If the federal government decides to risk the disintegration of Ethiopia, like it has done so far either due to incompetence or severe fear of committing large scale violence, that is fine for the federal government. But when you allow that disintegration to happen, please don’t leave the people of Amhara and Afar in a vulnerable position, unable to defend themselves and their lands. If we must return to the State of Nature, at least give these two peoples, who have so far shed more blood than anyone else in defense of their country, a chance to preserve their lives and their lands. Give them the resources they need to defend themselves before it is too late for them even if you feel it is too late for Ethiopia. Anything less is just a continuation of the gross criminal negligence that the federal government has been guilty of so far.

Continue Reading

Trending