Connect with us

Articles

በ2016 ዱባይ ማራቶን ፀጋዬ ከበደ እና ከዚህ ቀደም አሸናፊ የሆኑ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

Published

on

Women &  men Dubai 2016

በሴቶች የቀደሞቹ አሸናፊዎች ማሚቱ ዳስካ (የ2010 አሸናፊ)፣ ትርፊ ፀጋዬ (የ2013 አሸናፊ) እና ሙሉ ሰቦቃ (የ2014 አሸናፊ) ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን በወንዶች የውድድር ስፍራው ሪኮርድ ባለቤት አየለ አብሽሮ (የ2012 አሸናፊ)፣ ፀጋዬ መኮንን (የ2014 አሸናፊ)፣ ለሚ ብርሀኑ (የ2015 አሸናፊ) እና በዱባይ የመጀመሪያ ተሳትፎውን የሚያደርገው የለንደን ማራቶን የሁለት ግዜ አሸናፊ ፀጋዬ ከበደ ፉክክር ከፍተኛ ትኩረትን የሚስብ ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር የፊታችን ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በሚከናወነው የ2016 ስታንዳርድ ቻርተርድ ዱባይ ማራቶን ከዚህ ቀደም በተለመደው መልኩ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደሚሳተፉ የውድድሩ አዘጋጆች በተከታታይ እያደረሱን ከሚገኘው መረጃ የተረዳን ሲሆን እስካሁን በሁለቱም ፆታዎች ከዚህ ቀደም የውድድሩ አሸናፊ መሆን የቻሉ ስድስት አትሌቶችም ተሳታፊነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ 31ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታ የፊታችን ነሐሴ ወር ውስጥ በብራዚል ሪዮ ደ ጃኔይሮ አስተናጋጅነት ሊከናወን ዝግጅቶች እየተገባደዱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በርካታ ታዋቂ አትሌቶችን ለማፎካር ጥቂት ቀናት የቀሩት የዘንድሮው ዱባይ ማራቶን ተሳታፊ አትሌቶችም ጠቀም ላለው የገንዘብ ሽልማት ከሚያደርጉት ትንቅንቅ ጎን ለጎን በኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ሀገራቸውን ለመወከል የሚያበቃ ፈጣን ሰዓት ስለማስመዝገብ (ሚኒማ ስለማሟላት) የሚያልሙበት ጭምር ነው፡፡

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበር የወርቅ ደረጃ ያለው የዱባይ ማራቶን ውድድር ዳይሬክተር የሆነው ፒተር ኮኔርቶን ‹‹በዘንድሮው ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም አሸናፊ የሆኑ ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊ መሆናቸው ውድድራችን ለረጅም ርቀት ታዋቂ ሯጮች ምን ያህል አስፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ያሳያል፡፡ በመወዳደሪያ ስፍራው ላይ እየተመዘገቡ ያሉት ሪኮርዶች በራሳቸው የሚያስተላልፉት መልዕክት ያላቸው ሲሆን አስር አትሌቶች ከ2፡05 በታች የጨረሱበትን የውድድር ታሪክ በማስመዝገቡ ረገድም ግንባር ቀደሞቹ ነበርን፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ይህን ቁጥር ወደ 11 ከፍ አድርገነዋል፡፡ በሁለቱም ፆታዎች የሚፎካከሩት አትሌቶችም የአየር ሁኔታው ጥሩ ከሆነ ወጣ ገባ ባልበዛበት የመሮጫ ስፍራችን ላይ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ እንደሚችሉ በሚገባ ያውቁታል›› ብሏል፡፡

በወንዶቹ ምድብ ያለፈው ዓመት አሸናፊ የሆነው ለሚ ብርሀኑ እና የካቻምናው ባለድል ፀጋዬ መኮንን ፉክክሩን መቀላቀላቸውን ማረጋገጣቸው ቀደም ብለው በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ካሳወቁት አየለ አብሽሮ እና ፀጋዬ ከበደ (ሚስተር ኮንሲስተንሲ) ጋር በሚያደርጉት ትንቅንቅ የውድድሩን ድምቀት እና ጥራት ከፍ የሚያደርገው እንደሚሆን ተገልፃ*ል፡፡
የወንዶቹ ውድድር ተጠባቂ ተፎካካሪዎች
ለሚ ብርሀኑ (የ2015 አሸናፊ)

Berhanu wins Dubai Marathon 2015ባለፈው ዓመት ዱባይ ላይ በተሳተፈበት የሕይወት ዘመኑ ሁለተኛ የማራቶን ውድድር በ2፡05፡28 ከእርሱ የተሻለ ልምድ የነበራቸው ተፎካካሪዎቹን ቀድሞ ማሸነፍ የቻለው ለሚ ብርሀኑ ያስመዘገበው ውጤት የራሱን ምርጥ ሰዓትም በአምስት ደቂቃ ያሻሻለበት የነበረ ሲሆን ውጤት ባያመጣም በቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ ለመወዳደር በቅቷል፡፡ ከ12 ወራት በፊት ደስ የሚል ትዝታን ጥሎለት ያለፈ ትልቅ ድልን የተጎናፀፈው ለሚ ቀነኒሳ በቀለ ጭምር በነበረበት ውድድር ላይ ሳይጠበቅ አሸናፊ መሆን መቻሉ ፈፅሞ ያልጠበቀው ነገር እንደነበር አስታውሶ ስለዘንድሮው ውድድር ጠቅለል ያለ አስተያየቱን ሲሰጥ ‹‹ከቤይጂንግ ዓለም ሻምፒዮና ተሳትፎዬ በኋላ ሌላ ውድድር ስላልነበረኝ ላለፉት አምስት ወራት የዱባይ ማራቶንን በድጋሚ ስለማሸነፍ እያለምኩ በትኩረት ስዘጋጅ ቆይቻለሁ፡፡ በንድሮው ውድድር ላይም በጣም ጠንካራ የሆኑ ተፎካካሪዎች የሚገጥሙኝ ቢሆንም ዓላማዬ ማሸነፍ እና በሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ለመወከል የሚያበቃኝን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ነው›› ብሏል፡፡

ፀጋዬ መኮንን (የ2014 አሸናፊ)

Tsegaye Asefa Mekonnen Wins Dubai Marathon 2014በ2013 ዓ.ም. በአሯሯጭነት (ፔስ ሜከርነት) ተሳትፎ የነበረ ቢሆንም በማራቶን ይፋዊ የመጀመሪያ ተሳትፎው ሆኖ በተመዘገበለት የ2014ቱ ውድድር ለአሸናፊነት የበቃው ፀጋዬ መኮንንም የራሱ የሆነ ድንቅ ታሪክን ማፃፍ የቻለ ሲሆን በወቅቱ በ18 ዓመቱ በ2፡04፡32 ቀዳሚ ሆኖ የጨረሰበት ሰዓትም ይፋዊ ያልሆነ የዓለም ወጣቶች ሪኮርድ እንደሆነ ተገልፃ*ል፡፡ ከ24 ወራት በፊት ሕይወቱን የቀየረለትን ድል በዱባይ ያስመዘገበው ፀጋዬ ዘንድሮም ሌላ ከፍተኛ ድልን ስለመጎናፀፍ የሚያልም ሲሆን የ2014ቱ ድሉን አስታውሶ ሲናገር ‹‹ዱባይ ላይ ሳሸንፍ ባገኘሁት ሽልማት አዲስ አበባ ውስጥ ቤት ለመግዛት የቻልኩ ሲሆን ወደ ልምምድ የምመላለስበት መኪናም ገዝቻለሁ፡፡ ሙሉ ትኩረቴን በሩጫው ላይ ለማድረግ ስል ትምህርቴን ያቆምኩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እመራሁት ያለው ሕይወትም ከበዚህ ቀደሙ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው›› ብሏል፡፡

አየለ አብሽሮ (የ2012 አሸናፊ)

Abshero wins in Dubaiከአራት ዓመት በፊት በማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎውን በዱባይ ሲያደርግ የውድድሩ ሪኮርድ በሆነ 2፡04፡23 ሰዓት ለአሸናፊነት በመብቃት ብዙዎችን ያስደመመው አየለ አብሽሮ በአይ.ኤ.ኤ.ኤፍ የወርቅ ደረጃ ያለው ውድድር ላይ በመጀመሪያ ተሳትፎ የተመዘገበ ፈጣኑን ሰዓት ከመያዙም በላይ በወቅቱ ከዓለም የምንግዜም ፈጣን የማራቶን ሰዓቶች ተርታም በአራተኛነት ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በቅቶ ነበር፡፡ ከዛ ድሉ በኋላ የለንደን ኦሊምፒክን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ የበቃው አየለ በለንደን ማራቶን ሶስተኛ እና አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለባቸው ውጤቶቹም ይታወሳሉ፡፡ የታላቅ ወንድሙ ተሰማ አብሽሮን ፈለግ በመከተል ወደሩጫው ዓለም የመጣው አየለ በ2008 የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ በወጣት ወንዶች የብር ሜዳልያ አሸናፊ ከዓመት በኋላም በተመሳሳይ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን መቻሉም ይታወቃል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በትራክ ውድድሮች ላይ ከቆየ በኋላም ፊቱን ወደማራቶን አዙሮ ዘንድሮም ሌላ ትልቅ ድልን በሚያልምበት የዱባዩ ውድድር ድንቅ ጅማሮን አድርጓል፡፡ በ2012 የዱባይ ማራቶን ውድድሩን ሲያሸንፍ በዳውንታውን ዱባይ የጨረሰው አየለ ዘንድሮ በለስ የሚቀናው ከሆነ ውድድሩን የሚያጠናቅቀው በዱባይ ፖሊስ አካዳሚ አቅራቢያ ይሆናል፡፡
ፀጋዬ ከበደ (በዱባይ የመጀመሪያ ተሳትፎውን የሚያደርግ)

Tsegaye_Kebedeበማራቶን የቤይጂንግ ኦሊምፒክ እና የበርሊን ዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቱ ፀጋዬ በ2016ቱ የዱባይ ማራቶን ውድድር ላይ ከፍተኛ ተጠባቂነት ካላቸው አትሌቶች ግንባር ቀደሙ ሲሆን የ2010 እና 2013 ለንደን ማራቶን አሸናፊው ከዚህ በተጨማሪም በፓሪስ፣ ፉኩካ እና ቺካጎ ማራቶን ውድድሮች ላይ በተቀዳጃቸው ድሎች ይታወቃል፡፡ ፀጋዬ ዘንድሮ በሚሰጠው የሽልማት ገንዘብ የዓለማችን ሀብታሙ ውድድር ተብሎ በሚጠራው የዱባይ ማራቶን ላይ ለመፎካከር ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚያቀናው ከአሸናፊነቱ በተጨማሪ ለሪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ የሚያበቃውን ሚኒማ ማሟላትንም እያለመ ይሆናል፡፡ በ2012 የቺካጎ ማራቶንን ያሸነፈበት 2፡04፡38 የራሱ ምርጥ ሰዓት ሆኖ የተመዘገበለት ፀጋዬ በ2013 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁን ተከትሎም ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘው የወርልድ ማራቶን ሜጀርስ አሸናፊ መሆኑም ይታወሳል፡፡ የዱባይ ማራቶን ዳይሬክተር ፒተር ኮኔርቶን ‹‹ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከዓለማችን ታዋቂ እና ወጥ አቋም ያላቸው የማራቶን ሯጮች አንዱ የሆነው ፀጋዬ ከበደ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር በሚደረግበት ዓመት በእኛ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በመምረጡ በጣም ደስ ብሎናል›› ያለ ሲሆን ‹‹ካሉት ተወዳዳሪዎች ጥራት አንፃርም የውድድሩ ሪኮርድ ሊሰበር እንደሚችል ይጠበቃል›› በማለትም አክሏል፡፡

 

የሴቶቹ ውድድር ተጠባቂዎች
ሙሉ ሰቦቃ (የ2014 አሸናፊ)

Mulu Seboka Wins Dubai 2014በዱባይ ማራቶን በተከታታይ ሶስተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ በዝግጅት ላይ የምትገኘው ሙሉ ሰቦቃ በ2014 አሸናፊ የነበረች ሲሆን በ2015 አምስተኛ ሆና ስታጠናቅቅም 2፡21፡56 የሆነ የራሷን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች፡፡ በ2015 ዓ.ም. የወርልድ ማራቶን ሜጀርስ አካል በሆነው ቺካጎ ማራቶን ላይ ባደረገችው የመጀመሪያ ተሳትፎ አምስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ሙሉ ‹‹በ2014 ድል ያደረግኩበት እና በ2015 የራሴን ምርጥ ሰዓት ያስመዘገብኩበት የዱባይ ማራቶን ለእኔ ልዩ ውድድር ነው፡፡ በዘንድሮው ውድድር ላይም መሳተፍ እና የተሻለ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ የምፈልግ ሲሆን ከቺካጎው ውድድሬ በኋላም ትኩረቴን በሙሉ በዱባዩ ውድድር ላይ አድርጌ እየሰራሁ ነው›› ብላለች፡፡

ትርፊ ፀጋዬ (የ2013 አሸናፊ)

TIRFI TSEGAYEትርፊ ፀጋዬ በ2013 ለመጀመሪያ ግዜ የተሳተፈችበትን የዱባይ ማራቶን በ2፡23፡23 በአሸናፊነት መጨረስ የቻለች ሲሆን በመካከለኛ ምስራቅ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ 16ኛ ውድድር ላይም ሌላ ድል ለመቀዳጀት ትፎካከራለች፡፡ በ2008 በፖርቶ፣ በ2012 በፓሪስ፣ በ2014 በቶኪዮ እና በበርሊን የማራቶን ውድድሮች ላይም ማሸነፍ የቻለችው ትርፊ 2፡20፡18 የሆነ የራሷ ምርጥ ሰዓት ያላት ሲሆን በዘንድሮው የዱባይ ማራቶን ውድድር የአሸናፊነቱ የቅድሚያ ግምት ተሰጥቷታል፡፡

ማሚቱ ዳስካ (የ2010 አሸናፊ)

Daska_MarituFV-Dubai10በ2010 ዓ.ም. የዱባይ ማራቶን አሸናፊ ከሆነች ወዲህ የራሷን ምርጥ ሰዓት በ2011 የፍራንክፈርት ማራቶንን ስታሸንፍ ወደ 2፡21፡59 ዝቅ ማድረግ የቻለች ሲሆን ባለፈው መስከረም ወር በተከናወነው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ላይም በግማሽ ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት አትሌቶች ውጪም ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን አትሌቶች በውድድሩ ላይ ብርቱ ተፎካካሪ ሆነው ሊቀርቡ እንደሚችሉ እና ከተጠበቁት ውጪ የሆኑ አትሌቶችም ውድድሩን በበላይነት ሊጨርሱ የሚችሉበት ዕድል እንደሚኖር ይታመናል፡፡

በቤይጂንጉ የዓለም ሻምፒዮናም የኢትዮጵያን የማራቶን ቡድን በአሰልጣኝነት ከመሩት አንዱ የሆነውና በ2016 ዱባይ ማራቶን ላይ የሚሳተፉትን አራት ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በማሰልጠን ላይ የሚገኘው ገመዱ ደደፎ አትሌቶቹ በመጪው ሳምንት ለሚደረገው ውድድር እያደረጉት ያለው ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ በዘንድሮው ውድድር በሁለቱም ፆታዎች በእርሱ ስር የሚሰለጥኑ ስድስት አትሌቶች እንደሚወዳደሩ የጠቀሰው ገመዱ ‹‹ሁሉም አሰልጣኝ ልምምድ የሚያሰራው አትሌቱ የሚገባበትን ውድድር እንዲያሸንፍ በማለም ጭምር እንደመሆኑ እኔም ከአትሌቶቼ ሁሌም የምጠብቀው ውጤት የአሸናፊነቱን ደረጃ መውሰድ ነው፡፡ ለዘንድሮው ውድድር በወንዶች ልምድ ያላቸውና ያለፉትን ሁለት ውድድሮች በአሸናፊነት የጨረሱት ለሚ ብርሀኑ እና ፀጋዬ መኮንን በሴቶችም ከዚህ በፊት በዱባይ የአሸናፊነት ተሞክሮው ያላቸው ትርፊ ፀጋዬ እና ማሚቱ ዳስካ እንዲሁም በማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፏቸውን የሚያደርጉት መስፍን ተሾመ እና አማኔ በሪሶ ከእኔ ጋር በጥሩ ሁኔታ እየተዘጋጁ ይገኛሉ›› ብሏል፡፡

ከስያሜ ስፖንሰሩ ስታንዳርድ ቻርተርድ በተጨማሪ በዱባዩ ልዑል ሼክ ሀምዳን ቢን ሞሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም፣ በዱባይ ስፖርት ካውንስል፣ አዲዳስ፣ ዱባይ አይ 103.8 ኤፍ.ኤም፣ ዱባይ ሆልዲንግስ፣ ዱባይ ፖሊስ እና ዘ አርቲኤ ድጋፍ ሰጪነት የሚዘጋጀው የዱባይ ማራቶን በሶስት የተለያዩ ውድድሮቹ ወደ 30000 የሚሆኑ ሯጮችን እንደሚያሳትፍ የሚጠበቅ ሲሆን በ10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ውድድር እና በ4 ኪ.ሜ. ከሚደረገው ሩጫ በተለየ መልኩም ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘውና ታዋቂ አትሌቶችን የሚያፎካክረው የማራቶን ውድድሩ ከፍ ያለ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ በዱባይ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ከአንደኛ እስከ አስረኛ ባለው ደረጃ ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በቅደም ተከተላቸው መሰረት ከ100 ሺህ እስከ 8 ሺህ ዶላር ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን የዓለም ሪኮርድ መስበር የቻለም ተጨማሪ የ100 ሺህ ዶላር ጉርሻ ያገኛል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ከ2004 ዓ.ም ወዲህ በወንዶች ከአስራ ሁለቱ ዘጠኙ በሴቶች ከአስራ ሁለቱ አስራ አንዱ አሸናፊዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሲሆኑ በወንዶች ከ2012 በሴቶች ከ2007 ዓ.ም አንስቶም ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች የሌላ ሀገር አትሌቶችን ጣልቃ ሳያስገቡ በተከታታይ በማሸነፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

Continue Reading
Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የ5000ሜ ፉክክር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በአሸናፊነት አጠናቀዋል

Published

on

Dawit-Seyaum-1
ትላንት ምሽት በኖርዌይ ኦስሎ በተከናወነው የዳይመንድ ሊግ 5000 ሜ. ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉትን ደረጃዎች በመቆጣጠር አሸንፈዋል፡፡ 

በዝናባማ የአየር ሁኔታ ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፉክክር ዳዊት ስዩም በመጨረሻዎቹ መቶ ሜትሮች ውስጥ ፍጥነቷን በመጨመር ጉዳፍ እና ለተሰንበትን ቀድማ አንደኛ ወጥታለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሪገን 2022 የአለም ሻምፒዮና ከመረጣቸው ዕጩ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተችው ዳዊት በኦስሎ ያሸነፈችበት 14፡25.84 የሆነ ሰአት የራሷ ምርጥ ሲሆን እጅጋየሁ ታዬ (14.12.98) እና ለተሰንበት (14፡24.59) ባለፈው ወር በዩጂን ካስመዘገቧቸው በመቀጠልም የዘንድሮ የአለም ሶስተኛው ፈጣን ነው፡፡ በውድድሩ ላይ ከነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን መካከል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርቀቱ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ያደረገችው አልማዝ አያና በ14:32.17 ስድስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ ሀዊ ፈይሳ በ14:33.66፣ ፅጌ ገብረሰላማ በ14:43.90፣ እና አበራሽ ምንሴዎ በ14:47.98 በቅደም ተከተል ሰባተኛ፣ አስረኛ እና አስራ አንደኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ ሶስቱም ያስመዘገቡት ሰዓት የራሳቸውን ምርጥ ያሻሻሉበት ሆኗል፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ እ.ኤ.አ. በጁን 2008 ዓ.ም. ያስመዘገበችውና 14:11.15 የሆነው የኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የሴቶች 5000 ሜትር የውድድር ስፍራ ሪከርድ ይሰበራል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡  
ዳዊት ስዩም ውድድሩን በድል ካጠናቀቀች በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠችው አስተያየት ‹‹ዛሬ ለእኔ ደስታን ስላመጣልኝ በውድድሩ ሰዓት የነበረውን ዝናብ ወድጄዋለሁ ማለት እችላለሁ፡፡ ጠንካራ ተፎካካሪዎች የነበሩበት ከባድ ውድድር ነበር እናም ሁሉንም ለማሸነፍ በቅቻለሁ። በርቀቱ የራሴን ምርጥ ሰዓት ማሻሻል መቻሌም አስፈላጊ ነበር፡፡ በስታድየሙ ውስጥ በከፍተኛ ስሜት ድጋፍ ይሰጡን የነበሩ ወገኖቻችን ነበሩ። ለሰጡን ድጋፍ እናመሰግናለን።›› ብላለች፡፡
 
በኦስሎ የወንዶች 5000 ሜትር የመጨረሻ ፉክክሩ በኢትዮጵያውያኑ ጥላሁን ሀይሌ እና ሳሙኤል ተፈራ መካከል የነበረ ሲሆን ጥላሁን የ1500 ሜትር ስፔሻሊስቱ ሳሙኤልን በአጨራረስ ፍጥነት ቀድሞ በ13:03.51 በአንደኛነት አጠናቋል፡፡ ሳሙኤል ተፈራ የራሱ ምርጥ በሆነ 13:04.35 ሁለተኛ ሲወጣ ጌትነት ዋለ የግሉ የዓመቱ ምርጥ በሆነ 13:04.48 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። በውድድሩ ላይ የነበሩት ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሚልኬሳ መንገሻ በ13:05.94 አምስተኛ እንዲሁም አሊ አብዱልመናን የራሱ ምርጥ በሆነ 13:16.97 አስረኛ ወጥተዋል፡፡
ጥላሁን ሀይሌ ውድድሩን በአሸናፊነት ካጠናቀቀ በኋላ ለውድድሩ አዘጋጆች በሰጠው አስተያየት ‹‹ሶስት ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘን መጨረስ መቻላችን ጥሩ አፈጻጸም ነበር። እየጠነከርኩ እንደሆነ የተሰማኝ ሲሆን በውድድሩ እና ባስመዘገብኩት ሰዓትም ተደስቻለሁ። ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ ስለነበኩ ወደ አሸናፊነቱ መመለስ መቻሌ በጣም ጥሩ ነው።›› ብሏል፡፡

በኦስሎ የሴቶች 800ሜ. ውድድር ላይ ተፎካካሪ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ድሪቤ ወልቴጂ በ1፡58.69 አምስተኛ ሆና አጠናቃለች።
Continue Reading

Articles

የዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ሻምፒዮና በእኔ እይታ

Published

on

IMG_0110
ከመጋቢት19-24/2014 ዓ.ም በሐዋሳ አለም አቀፍ ስቴድዮም የተደረገው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሞላ ጎደል ስኬታማ በሚባል ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ ከአምስት አመት በኋላ በድጋሚ በአካል በመገኘት ስለተከታተልኩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና የግል ምልከታዬን እንደሚከተለው አጠናቅሬዋለሁ፡፡

የበለጠ ትኩረትን በሳቡት ውድድሮች ዙሪያ የተመዘገቡ ውጤቶችን በወፍ በረር በመዳሰስ ስጀምር ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የመጨረሻ ቀን የወንዶች 5000ሜ. የአለም ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና የ3000ሜ የብር ሜዳልያ አሸናፊው አሊ አብዱልመና 13፡45.0 በሆነ ሰዓት ከጥላሁን ሀይሌ፣ ጌትነት ዋለ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ቀድሞ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የፉክክሩ አካል የነበረው እና የርቀቱ የወቅቱ የአለም ሻምፒዮን ሙክታር እድሪስ ስድስተኛ ወጥቷል። 

ከ20 ዓመት በታች የ3000ሜ የአለም ሻምፒዮኑ ታደሰ ወርቁ በ28፡12.0 የወንዶች 10,000ሜ. ሻምፒዮን ሲሆን በ1996 ዓ.ም. በአትሌት ስለሺ ስህን ተመዝግቦ የነበረውን 28፡16.23 የሆነ የሻምፒዮናው ሪኮርድ ለማሻሻልም በቅቷል፡፡ በ10 ሺህ ሜትር የሴቶች ፉክክር ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በቀዳሚነት የጨረሰችበት 31፡21.5 የሆነ ሰዓት አዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በርቀቱ የከዚህ ቀደሙ ሪኮርድ  ለተሰንበት ግደይ ከሶስት ዓመት በፊት ያስመዘገበችው 32፡10.13 የሆነ ሰዓት ነበር፡፡

ሳሙኤል ፍሬው በዘንድሮ የወንዶች 3000ሜ. መሰናክል አፈፃፀም ከአለም ሁለተኛው ፈጣን በሆነ 8፡22.5 ሰዓት አሸናፊ ሲሆን ጌትነት ዋለ ከአራት ዓመት በፊት አስመዝግቦት የነበረውን 8፡28.98 የነበረ የሻምፒዮናው ሪኮርድም አሻሽሏል፡፡ በሴቶች 3000ሜ. መሰናክል ከ800ሜ ወደ ረጅም ርቀት የተሸጋገረችው ወርቅውሃ ጌታቸው በ9፡41.8 ሰዓት መቅደስ አበበን (9:43.8) በማስከትል በአሸናፊነት አጠናቃለች። 

አድሃና ካህሳይ (3:51.0) የወንዶች 1500ሜ ፉክክሩን በበላይት ሲያጠናቅቅ በሴቶች 1500 ሜ አያል ዳኛቸው (4:10.0) ተጠባቂዋ ዳዊት ስዩምን (4:11.1) በመቅደም በአንደኛነት አጠናቃለች። በ800ሜ. ወንዶች ቶሌሳ ቦደና (1:47.1) በሴቶች ወርቅነሽ መሰለ (2:02.1) አሸናፊ ሆነዋል።
ዮብሰን ብሩ በ400ሜ/400ሜ መሰናክል (45.9/50.5) ድርብ ድል ሲቀዳጅ፣ በወንዶች ጦር ውርወራ ኡታጌ ኡባንግ ብሔራዊ ሪኮርድ በሆነ 73.28ሜ. አሸንፏል፡፡ የኋልዬ በለጠው እና ዮሃንስ አልጋው በእርምጃ ሩጫ የሻምፒዮንነት ክብርን ተቀዳጅተዋል።

ጥቂት አስተያየቶች፡-
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪ እንደሆነ እና ለዕድገቱ እንደሚቆረቆር ሰው በብሔራዊ ሻምፒዮናው ላይ ስለተመለከትኳቸው አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ጥቂት አስተያየቶቼን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፡-

አዎንታዊ ጎኖች
• ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉትን ተግዳሮቶች በሙሉ በመቋቋም ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ከአዲስ አበባ ውጭ አካሂዶ በሰላም ማጠናቀቅ መቻሉ አንደኛው ስኬቱ ነው፡፡

• በሻምፒዮናው ላይ ጥቂት የማይባሉ ታዋቂ አትሌቶች በሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ፉክክር ላይ ተሳታፊ ሆነው ሲወዳደሩ መመልከት የተቻለ ሲሆን በተለይም በወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ላይ የታየው የኮከብ አትሌቶች ፉክክር ልዩ ነበር፡፡

• በውድድሩ ወቅት ለአትሌቲክስ ዳኞች የብቃት ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱም የውድድሩን ጥራት ለማሳደግ የሚረዳ እንደመሆኑ እሰየው የሚባል ነው፡፡
 
• እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሉት ክለቦች ለአትሌቲክስ ስፖርት የበለጠ ትኩረት በመስጠትና ተጠናክሮ በመቅረብ ከዚህ ቀደም በጠንካራነታቸው ከሚታወቁት መከላከያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የቅርብ ተፎካካሪ ሆነው መታየት፤ የኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ፖሊስ እና ሲዳማ ቡና ክለብ አትሌቶችም ጠንካራ ተሳትፎ ሳይዘነጋ የሻምፒዮናው ፉክክር ድምቀት ነበሩ፡፡  
• የአንዳንዶቹ ተገቢነት አጠያያቂ ቢሆንም ብዛት ያላቸው የሻምፒዮናው ሪኮርዶች የተሻሻሉበት ውድድርም ነበር፡፡ 

አሉታዊ ጎኖች
• የሀገሪቱ ትልቁ የአትሌቲክስ ውድድር ውጤት አሁንም በኤሌክትሮኒክስ የሰዓት መቆጣጠሪያ የማይደገፍ መሆኑ በተለይም በአጭር ርቀት እና በሜዳ ላይ ተግባራት ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ልፋት ተገቢውን እውቅና እንዳያገኝ እያደረገ ይገኛል፡፡ የሻምፒዮናውን ውጤቶች በዘመናዊ እና ዓለም አቀፉን መለኪያ በሚያሟላ መልኩ አለመያዝ በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ ለተሳትፎ የሚያበቁ ውጤቶችን በማስመዝገቡ ረገድ የሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ አሁንም መፍትሄ ያልተበጀለት ጉዳይ ነው፡፡ 
 
• የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ሚዲያ/ለአጠቃላዩ ሕዝብ የሚያስተላልፈው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶችን ውጤት ብቻ መሆኑ አወዳዳሪው አካል የሚያደርገውን የራሱን ውድድርም ሆነ አትሌቶቹ የለፉበትን ውጤት ከማስተዋወቅ አኳያ በቂ አይደለም፡፡
  
• በወንዶች የጦር ውርወራ እና የሴቶች ምርኩዝ ዝላይ ብሔራዊ ሪኮርዶች እንደተመዘገቡ ይታመናል፤ በሴቶች 100ሜ መሰናክል እና የወንዶች 400ሜ መሰናክል የተመዘገቡት ሰዓቶችም የምንግዜውም ፈጣን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውድድሩ በኤሌክትሮኒክስ ታይሚንግ ያልተደገፈ እና የንፋስ ንባብ ያልነበረው መሆኑ ውጤቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ነው።

• በ20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ላይ በሁለቱም ፆታዎች የተመዘገቡት ሰዓቶች ከሚጠበቀው በላይ እጅግ በጣም ፈጣን እና እውነታዊ አለመምሰላቸው በውድድሩ ላይ የተፈጠረ አንዳች ስህተት መኖሩን የሚያመላክቱ መሆኑ፡፡ እንዲህ አይነት ለማመን የሚከብዱ እና ጥርጣሬን የሚፈጥሩ አይነት ውጤቶች ሲመዘገቡም የተፈጠረ ስህተት መኖር አለመኖሩን ለማጣራት አለመሞከሩ፡፡
     
• የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ ለውድድር የማይፈቀድ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማን በመጠቀም የተመዘገበ ውጤት በሪኮርድነት ጭምር ተይዞ መፅደቁ። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከተከለከሉ ጫማዎች ጋር የተያያዙ ዓለም አቀፍ ሕገ ደንቦችን ማወቅና መተግበር ቢገባውም በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ የተከሰተው ነገር የውድድር ሕገ ደንቦቹ መረጃ በፌዴሬሽኑ ውስጥ በትክክል የተሰራጩ እንዳልሆነ የሚያመላከት ነው፡፡  

• በሴቶች 1500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይ አትሌት ዳዊት ስዩም የሻምፒዮናውን ሪኮርድ ያሻሻለችበት ውጤት እንደተመዘገበ በውድድሩ ወቅት በተደጋጋሚ ሲነገር ከተደመጠ በኋላ ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውጤቱ በሐዋሳው ውድድር ላይ ተሻሻሉ ከተባሉት የሻምፒዮናው አዲስ ሪኮርዶች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም የፌዴሬሽኑን ግልፀኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ለረጅም ግዜ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች በቅርበት ከመከታተሌ አንፃር በራሴ እይታ ያስቀመጥኳቸው እንደመሆናቸው አንዳንዶቹ ሀሳቦች አከራካሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የውድድር ደንቦችን በአግባቡ ከማስፈፀም አኳያ በታዩት ክፍተቶች ዙሪያ ምንም የሚያከራክር ጉዳይ ስለሌለ በወቅታዊ የውድድር ደንቦች ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት ላለባቸው የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት በሙሉ አስፈላጊውን ገለፃ እና ትምህርት መስጠት የፌዴሬሽኑ ኃላፊነት ነው፡፡ ከውድድር ጋር የተያያዙ ደንቦችን ከመጣስ አኳያ በሀገር ውስጥ በሚደረጉ ውድድሮች እንደቀላል ነገር የሚታለፉ ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም ተደግመው እንደግል አትሌቶችን እንደቡድን ሀገርን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍሉ ይችላሉና አስፈላጊው ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ባለፈው መስከረም ወር በቪየና ሲቲ ማራቶን ውድድሩን በአሸናፊነት ጨርሶ የነበረው ኢትዮጵያዊው ደራራ ሁሪሳ የገጠመውን አንዘንጋው! 

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመልካም ጎኑ ስሟ እንዲነሳ በሚያደርገው እና በትልልቅ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ የኩራታችን ምንጭ በሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት እንደጎረቤታችን ኬንያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ የብቃት ደረጃ ላይ ደርሰን ማየት የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንም የውድድሮቹን ጥራት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ።      
      
የ10,000ሜ. አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር (Photo by EAF)

በመጨረሻም በሀዋሳ በተካሄደው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመሮጫ ጫማ ጋር የተያያዙ ደንቦችን በማስከበሩ ረገድ የተፈጠረውን ክፍተት እንደማስተማሪያ ብንጠቀምበት በሚል የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ፡-

የመሮጫ ጫማ ደንቦች ለትራክ ውድድር

64 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የዘንድሮ የራስ አል ካይማህ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር በሐዋሳ በተከናወነው 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 31 ደቂቃ ከ21.5 ሰከንድ  በመግባት የ10,000ሜ. አሸናፊ ሆናለች፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ዓለም አቀፉን ደንብ ከግምት ባላስገባ ሁኔታ ውጤቱን በአዲስ የሻምፒዮንሺፕ ሪኮርድነት ጭምር አፅድቆት አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ መጋቢት 20/2014 በተደረገው የሴቶች የፍፃሜ ፉክክር ላይ በኢትዮጵያ ምድር የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሰዓት የሆነው ውጤት በአለም አትሌቲክስ ዘንድ እውቅና ሊሰጠው የማይችል ነው።

ለምን?

አትሌቷ የሶል ውፍረቱ 40ሚሜ የሆነ ዙምኤክስ ቬፐርፍላይ (ZoomX Vaporfly) ጫማ አድርጋ በመወዳደሯ ምክንያት።

ደንቡ ምን ይላል?

በትራክ ውድድሮች ላይ የሚፈቀደው ከፍተኛው የሶል ውፍረት ፡-
– 20ሚሜ ከ 800ሜ በታች ለሆኑ ውድድሮች እና ለሁሉም የሜዳ ላይ ተግባራት (ከስሉስ ዝላይ በስተቀር)

– 25ሚሜ ለ800ሜ እና ከዛ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ

– 40ሚሜ ለትራክ ላይ የእርምጃ ውድድሮች

እነዚህ ደንቦች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 31, 2024 ድረስ በሥራ ላይ ይውላሉ። ከኖቬምበር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ለ800ሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ውድድሮች እንዲሁም ለስሉስ ዝላይ የሚፈቀደው ከፍተኛ የሶል ውፍረትም ወደ 20 ሚሜ ዝቅ የሚል ይሆናል።

የትራክ ላይ መወዳደሪያ ስፓይክ ጫማ ከሌለኝስ?  

ደንቡ የጎዳና ላይ የመሮጫ ጫማዎች በትራክ ላይ እንዳይደረጉ አይከለክልም ነገር ግን በ25 ሚሊ ሜትሩ ገደብ ምክንያት 30 ሚሜ ወይም 40 ሚሜ የሆኑ የጎዳና ላይ መሮጫ ጫማዎች በትራክ ውድድሮች ላይ እንዲደረጉ አይፈቅድም፡፡

ለበለጠ መረጃ :-
https://www.worldathletics.org/news/press-releases/new-athletic-shoe-regulations-approved-2022

Continue Reading

Opinions

On the TPLF’s Love Affair With ‘Genocide’

Published

on

WhatsApp-Image-2021-11-04-at-12.41.51-AM
Ethiopia's Lalibela, a UN World Heritage Site, now under Tigrayan forces control

Today, the joint investigation report by the Ethiopian Human Rights Council and the UNHR
on human rights violations committed in Tigray concluded that there is no evidence that genocide has taken place so far. While this is a bit of a setback for the TPLF, which has wanted the world to believe—since the 1990s, even as the TPLF was dominating power in Addis—that a genocide has been perpetrated against the people of Tigray, unfortunately the group still appears to be determined to make genocide a reality. This is confusing for people who don’t understand why the TPLF is obsessed with genocide, why its internet cadres began using #TigrayGenocide in April 2020, months before the war began. So many weapons have been deployed in this war, and among them: confusion and obfuscation.


In the past several months and more so in the past few weeks, we have been getting
testimony after testimony from allied Amhara forces fighting the TPLF that Tigrayan residents of cities in Wollo have been collaborating with the TPLF by a) attacking ENDF and allied forces from behind; b) forcing ENDF and allied forces to withdraw from towns and cities afraid of committing large scale massacres by firing back at the civilians (Tigrayans) firing at them; c) helping the TPLF locate and execute young Amharas believed to be a threat; and d) in at least one horrifying account by an IDP who managed to escape occupied territories, handing TPLF soldiers a list of women to rape. Another shocking development in the past several months has been the widespread use of child soldiers by the TPLF, which, according to experts who have studied the practice, is an “alarm bell” calling attention to possible plans to commit mass atrocities. The use of child soldiers by the TPLF and its attendant implications, along with the widespread deployment of civilian sleeper agents in Amhara cities the TPLF has taken over, serves to create an overall perception of every Tigrayan as a potential enemy, sowing fear and mistrust.

Many Ethiopians are looking at this and wondering: why are Tigrayan elites on the internet
either celebrating the TPLF’s advance via these toxic methods or silent about all this? How can they not see how dangerous this is for everyone, especially for Tigrayans who live outside Tigray? How can they not see that there is no “winning” after stoking all this lasting animosity? Do Tigrayan elites not understand that there can be no justice for Tigray—whether Tigray secedes or not—unless there is justice for her neighbors, for Tigray does not exist in a vacuum? The questions are being asked but nobody is answering them. Our academic class has largely failed to offer viable analyses of the ideas driving this war, as they failed over the past fifty years in regards to coming up with a fitting paradigm for understanding Ethiopia’s unique situation.


Here is my humble attempt to explain what I think is happening with the TPLF’s obsession
with—and with its active attempt to inspire—genocide:


The most successful psychopaths in any field understand that, in order to win anything, one
must risk everything, including the very thing one is supposedly fighting for. In the case of the
TPLF (and associated Tigrayan political elites), whose motto appears to be “give me supremacy or give me death,” that “everything” they are risking is the lives of ordinary Tigrayans in whose names they are fighting. We have seen over the past several months the extent to which the TPLF is willing to go to sacrifice ordinary Tigrayans in order to get what it wants: wave after wave after wave of young poorly armed and inexperienced Tigrayans were unleashed upon ENDF and Amhara and Afar forces in order to force the latter to waste ammunition and energy before the more experienced soldiers are sent.


So, for a political group who sends tens of thousands, if not hundreds of thousands, of
young Tigrayans towards open fire, violence against hundreds of thousands of Tigrayans is nothing if it means the TPLF will in the end win the “prize” it has been obsessed with for decades: genocide. You see, merely attaining power in Addis Ababa is not enough for the TPLF, whose core driving ideology is Tigrayan supremacy. Power is temporary; anybody can take it away from you, and the 2018 uprisings demonstrated that. Genocide is forever. Nobody can take away from you the story of genocide committed against your people.


The TPLF looked at countries like Israel and Rwanda and realized what a potent instrument
genocide is for establishing perpetual minority rule. We have some indications suggesting that the TPLF views Israel as a model. When the war between Ethiopia and the TPLF began in November 2020, Sekoutoure Getachew, a TPLF official, went on TV to tell us that the TPLF’s decision to launch a preemptive attack on the Northern Command was inspired by how the young state of Israel, feeling threatened by her neighbors, launched preemptive attacks against them in the “six-day war” of 1967. Another indication is the manner in which the TPLF, during its 27 years in power, invested heavily in creating a wealthy and strongly networked Tigrayan diaspora which has been used to lobby and influence western governments and organizations much in the same way as the Jewish diaspora aids the state of Israel. The TPLF has figured out that truth does not matter in politics, especially in international politics. If you have the wealth and the personnel to peddle your preferred narrative, if you have the military power to subdue the people you want to subdue, if you are willing to make concessions to external forces (US, Egypt, etc), you can do unspeakable things to others (much like the state of Israel does to Palestinians) and still manage to portray yourself as the victim.
This calculation is so far working for the TPLF, but nothing would seal the deal like the actual
commission of genocide—or something that looks like it—against Tigrayans. As we have seen over the past twelve months, western governments and organizations have shown their willingness to adopt TPLF’s narratives without scrutiny and can easily reward the TPLF with its much pursued prize, genocide, even if actual genocide doesn’t take place.


But why does the TPLF need genocide to establish minority rule? Because, as we saw in their
first tenure in power, you can only rule with an iron fist for a limited period of time. Leaders of the TPLF are adherents of Tigrayan supremacy: the idea that Tigrayans, as the “only” heirs of the Axumite empire, are the natural rulers of the Ethiopian state, and cannot be ruled by “barbarians” south of them. The only acceptable power arrangement for the TPLF is one in which Tigrayans are either directly dominating political power or are the perpetual kingmakers pulling all the major strings. Anything outside that, any system that forces Tigrayans to live on equal footing with everyone else, is unacceptable. And this kind of domination by a minority cannot coexist with a democratic system that the majority of Ethiopians clearly prefer. So, the TPLF needs something more potent than pure political/economic/military power to justify bypassing democracy to establish itself as the permanent ruler/kingmaker of Ethiopia. It needs a new and powerful raison d’être to justify its domination not just to Tigrayans and the rest of Ethiopians but, and most importantly, to the rest of the world. If a genocide were to be committed against Tigrayans (or if the U.S. decides to reward the TPLF with the genocide label even in the absence of it), then the TPLF can license itself to impose all manner of drastic measures aimed at “protecting Tigray and
Tigrayans.” This could be anything from redrawing internal borders (and taking debilitating
measures against the peoples whose lands are being robbed—most likely Amharas and Afaris—so that they will never be in a position to assert themselves) to ethnic cleansing and genocide against populations considered to be a threat. And when you oppose it, the TPLF will say “you committed a genocide against Tigrayans” over and over and over, and its western backers will repeat the same chorus. If they have been this loud over a non-existent genocide over the past twelve months, just imagine what it would be like if the U.S. or UN rewards them with that label.


And this is where the Ethiopian government’s major dilemma comes from: if ENDF and
Amhara forces fight to regain their cities and towns, they risk committing large scale massacres. The TPLF networks reported to be operating within these cities wear civilian clothing and fire at the armies from inside civilian establishments, in an apparent attempt to set up pro-Ethiopia forces. Pro-Ethiopia forces are essentially being dared to commit large scale massacres in order to win back their own cities. So far, they are choosing to withdraw from these towns and cities. But that is another problem: not only is the TPLF committing unspeakable violence against civilians and destroying infrastructure in those cities, the takeovers are emboldening it to continue pressing, giving young people back in Tigray false hope that they are winning and—this is very important—the false idea that they are being “welcomed” by locals in those cities. Then more and more and more young Tigrayans are sent to their deaths.


So the Ethiopian government is stuck between a rock and a hard place. One option is
allowing its forces to do whatever it takes to take back territory, thereby offering protection to its citizens in Wollo and elsewhere, but also risking the “genocide” label by western governments who have been eagerly waiting for such an opportunity so that they can blackmail the government into submitting itself to their wishes on GERD and other issues. Option two is avoiding large scale violence and allowing the TPLF to take power in Addis Ababa and do to Ethiopia what it wishes. One of the things it might do to Ethiopia, according to its leaked strategy document, is force a confederation that will no doubt privilege some states, i.e. Tigray, more than others, and that will no doubt be designed to subdue some populations—mainly Amharas and Afaris—who are considered obstacles to Tigray’s aspirations of domination and expansion (in the TPLF’s original manifesto, Afar is claimed as Tigray land).


And there is absolutely no doubt that the TPLF will make big concessions on the GERD in
order to compensate its western and Egyptian backers, if not redraw borders to make Benishangul Gumuz Tigrayan territory. If you think this is wild, read about the history of the state of Israel, the TPLF’s model state. The redrawing of borders that the TPLF undertook in 1991 was also wild at the time; people don’t think of it as outrageous anymore because the fact that they held onto the territory for 30 years has normalized the event in our minds. And that’s all the TPLF needs: another thirty years to normalize all the outrageous things they will do next.

One may argue that this is a false dichotomy, that there is a third or even maybe fourth option: winning these cities back without mass violence much in the same way the ENDF managed to do during its first campaign in Tigray. We all should pray for such a miracle, of course. However, one can also say that in the early days of the war, the TPLF was mostly withdrawing from Tigrayan cities to avoid urban warfare. And even when they engaged in urban warfare, it was not at the same scale and intensity as has been the case over the past four and half months or so. Starting in mid June, the TPLF’s use of civilians as human shields and fighters stopped being just another weapon in its arsenal and became a center of its operations. The near collapse of the ENDF inside Tigray right before its withdrawal was precipitated by the TPLF’s intensified use of “civilians” to trap the ENDF. Many ENDF soldiers chose to surrender rather than fire at those “civilians.” It is still possible to avoid large scale violence in the attempt to retake towns in Wollo, but the risk for it is very high, and is possibly behind the federal government’s reluctance to take decisive actions.


The point is: barring miracles, the Ethiopian government is positioned to lose something
one way or another. All that is left is choosing its preferred poison. Perhaps one thing to consider for the federal government is: the rights of Amharas and Afaris to defend themselves against the existential threats posed against them by the TPLF is much bigger than the national government’s concerns about its place and relationships with the rest of the world. If the federal government decides to risk the disintegration of Ethiopia, like it has done so far either due to incompetence or severe fear of committing large scale violence, that is fine for the federal government. But when you allow that disintegration to happen, please don’t leave the people of Amhara and Afar in a vulnerable position, unable to defend themselves and their lands. If we must return to the State of Nature, at least give these two peoples, who have so far shed more blood than anyone else in defense of their country, a chance to preserve their lives and their lands. Give them the resources they need to defend themselves before it is too late for them even if you feel it is too late for Ethiopia. Anything less is just a continuation of the gross criminal negligence that the federal government has been guilty of so far.

Continue Reading

Trending