Connect with us

Articles

በገብረመድህን አርአያ – በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል

Published

on

Hand Draw - Ethiopa Map 1

በገብረመድህን አርአያ
በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል

ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው።
ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ ፕሮግራም በማለት አውግዘውት ነበር። ከነዚህ ካወገዙት መካከል ለምሳሌ ለመጥቀስ፤ አስገደ ገብረሥላሴ፣ ካህሳይ በርሄ (ዶ/ር ግንጽል)፣ ተሾመ ጉዶ፣ ሲሆኑ እነዚህ በህይወት ያሉ ሲሆን፣ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋእድ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዘርኡ ገሰሰ (አጋአዚ) ገሰሰው አየለ፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ ዘወንጀል በየነ፣ መሃረ ተክሌ ወዘተ እነዚህ ፕሮግራሙን በጠነከረ አቋም ስለተቃወሙ የተገደሉ ናቸው። ተሓህት የፕሮግራም ዝግጅቱን ንድፈ ሃሳብ የጀመረው ገና በረሃ ሳይወጣ ማገብት ተብሎ በሚጠራበት ከ1966 ጀምሮ ነው። ይህንን ፕሮግራም በሃላፊነት ያዘጋጀው አረጋዊ በርሄ ሲሆን፣ ጥር 1967 ለወታደራዊ ስልጠና ኤርትራ፣ ስህል ወርደው
ፕሮግራሙን በማጠናከር የተሰማሩት የትጥቅ ትግሉ መሪዎች አረጋዊ በርሄ፤ በዋና ሃላፊነት፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አስፍሃ ሃጎስ፣ በህመም የሞተ፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ በወያኔ የተገደለ፣ ሥዩም መስፍን፣ ሃይሉ /ነጠበ/መንገሻ ሲሆኑ ብዙ የጎደለው እንዳለ ተስማምተው በይደር ወደ ደደቢት ተዘዋወረ።


የካቲት 11፣ 1967 ታጋዮቹ ደደቢት በረሃ እንደገቡና የትጥቅ ትግሉ እንደተጀመረ፣ ግንባር ቀደም ተግባራቸው ሶስት ነጥቦች ላይ ነበር ትኩረት ይሰጠው። 1ኛ፣ የድርጅቱን ስም ማውጣት፣ 2ኛ፣ ለወደፊቱ ለምትመሰረተው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የግዛት ስፋት ከውጭ ሃገር፣ ሱዳን በሚገኘው መልኩ ማዘጋጀት፤ 3ኛ፣ ፕሮግራሙን ለመጨረሻው ዝግጅቱ ታማኝ ታጋዮችን በማሰባሰብ ለሚከተሉት ሰዎች፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ሥዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ስየ አብርሃ፣ ግደይ ዘርአጽዮን ወዘተ ሃላፊነቱ ተሰጠ። ለዚህ መሰናዶ ከበጌምድር ጠቅላይ ግዛት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ፣ ወልቃይት እንዲሁም ከወሎ ጠ/ግዛት፣ ራያና ቆቦ፣ ወልድያ፣ አላማጣ እስከ ላይኛው ሃሸንጌ ሃይቅ ድረስ በማጠቃለል የትግራይ መሬት ነው ተብሎ በመወሰን የፕሮግራሙን አቋም ደመደመ። ይህ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ወደ 30 ገጽ የሚሆን ተባዝቶ በመጽሓፍ መልክ ተጠርዞ በብዛት ተያዘ።በሃላፊነት የጻፉት አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ ናቸው። በየቦታው እንዲሰራጭም ተደረገ።

ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ኢትዮጵያን ለመበታተን፣ ሕዝቧን በዘርና በጎሳ የከፋፈለ፣ አማራውን ደመኛ ጠላት ብሎ ያወገዘ ሆኖ የመጣና እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የሆነ አስተሳሰብ ነበር።
አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው፣ ከሚለው ቀጥሎም ለብዙ ዓመታት ነፃ ሃገር ትግራይ ነፃነቷ ተገፎ በአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ አገዛዝ ወድቃለች፣ በማለት ብዙ ይተነትናል። በአጼ ዮሃንስ ዘመነ መንግሥት ሃይሏ በርትቶ በአካባቢዋ የነበሩትን ነገሥታት በቁጥጥር ስር አውላ ነበር። ይሁን እንጂ አፄ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ትግራይ በሸዋው ማእከላዊ ግዛት ስር ወደቀች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው አማራው የመሳፍንት ቡድን እና ተከታዮቹ የትግራይን ነፃነት ገፈው የህዝቧን አንድነት ያናጉት። በግልጽና ስውር በሆነ ዘዴዎች (ሸዋዊ ዘይቤዎች) የትግራይ ህዝብ በድንቁርና፣ በበሽታ፣ በረሃብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት እያለ ይቀጥላል። ከላይ የተጠቀስውና ሌላውን ጨምሮ ተሓህት የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራ ነው፣ ነፃ ሃገር የነበረቸው ትግራይ ሃገርህ በአማራ (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ሆና አንተ ለክፉ መከራ ተረግህ በማለት አመራሩ በሙሉና የተሓህት ታጋዮች ወደ ህዝቡ ተበታትነው ፖለቲካቸውን አስተማሩት። ማንኛውም የትግራይ ህብረተሰብ ይህ የምትናገሩት ሁሉ ፈጽሞ ከእውነት የራቀና የራሳችሁ የፈጠራ ፖለቲካ ነው። አማራ ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ አይደለም፣ ወንድሙና እህቱ እንጂ። ሁላችንም ተቃቅፈን በጋብቻ ተሳስረን በፍቅርና በሰላም የምንንሮር የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነን። ከትወልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ፍቅርና ወንድማማችነትን እህታማችነት አታፍርሱብን። አማራ (ኢትዮጵያ) ትግራይን በቅኝ ግዛት ስር አድርጋለች የምትሉት ከየት ያገኛችሁት እንደሆነ እኛ አናውቅም። ትግራይ ዱሮም አሁንም የኢትዮጵያ የታሪክ ማእከል ናት በማለት የትግራይ ህዝብ ከገጠር እስከ ከተማ ተቃውሞ አደረሰባቸው። በዚህም ምክንያት የገጠርና የከተማ ኗሪው በቀን እና በሌሊት እየተለቀመ በሽብርተኞች ቡድን ተገደለ፣ ቤቱ ፈረሰ፣ ህፃናት በየቦታው ወድቀው ቀሩ። ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ከፋሽስቱ ጣሊያን ጋር የተዋጉ የትግራይ ኢትዮጵያዊ አርበኞች በወያኔ ትሓህት ከየቤታቸው እየተለቀሙ ሃለዋ ወያኔ ገብተው በጥይት እየተረሸኑ መስዋእትነት ከፈሉ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ በ1969 የተሓህት መሪዎች ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃየ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሥዩም መስፈን፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ ተሰባስበው በትግራይ ውስጥ የሚኖረው አማራ፣ ኦሮሞና ሌላውም ከትግራይ ይውጡ፣ ትግራይ2 ለትግራይ ህዝብ ብቻ ናት የሚል አዋጅ አስተላለፉ። ይህንን ሃሳብ ያልደገፉት ግደይ ዘርአጽዮን እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ብቻ ነበሩ።

በዚህ የዘረኝነት አጥር ውስጥ የገባው የተሓህት አመራር ከ1969 መጨረሻ በፕሮግራሙ ያካተተው የትግራይ መሬት ብሎ ያስቀመጠው ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ቃፍታ ላይ ማነጣጠር ጀመረ። በተቻለ መጠንም በፍጥነት ተቆጣጥረን በትግራይ ውስጥ ገብተው በተሓህት አመረር ስር መተዳደር አለባቸው የሚል እቅድ ያዘ። ከዚህ ቀደም ብሎ በአርከበ እቁባይ የተዘጋጀ ካርታ ከበጌምድር ጠ/ግዛት ከላይ የተጠቀሱትን ቦታዎ ች፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ራያና ቆቦ፣ አላማጣ፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ ለምትመሰረተው አዲሲቷ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትግራይ ሲካተቱ፣ በምእራብ በኩል ደግሞ ወልቃይት፣ ሁመራ ፀለምት፣ ፀገዴ ተጨምረው ትግራይ ከሱዳን ጠረፍ ጋር እንደትገናኝ፣ በደቡብ በኩል ደግሞ ወደውሃ ምላሽ ትግራይ እንድትሰፋ ሲወስን፣ እነዚህቦታዎች ሁሉ ለምና ሃብታም መሬቶች ናቸው። ይህንን ውጥን ለማሳካት በወልቃይት ፀገዴ ተሓህት ህዝቡን እያፈነ ማጥቃት ጀመረ። የወያኔ/ህወሓት/ተሓህት መሰረታዊ የታሪክ ወንጀል የወላቅይት ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ ለብዙ ሺህ ዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ታሪካዊ ቦታዎች የበጌምድር (ጎንደር) ግዛት መሬት ነው። ታሪክም የሚያረጋግጠው ይህ ነው።። በምንም ተአምር ከትግራይ ግዛት ጋር ግንኙነት የለውም። የሚገናኙበት ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊነት ነው። በጌምድርም ሆነ ትግራይ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። በሃይማኖትና በጋብቻ ተያይዘዋል። ይህ ደግሞ በሁለቱ ህዝብ ማካከል ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ውስጥም ያለ ነው። ኦሮሞው ከትግሬ፤ ትግሬው ከአማራ፣ አፋሩ ከጋምቤላው፣ ጉራጌው ከሌላው ዘር ጋር ወዘተ የተደባለቀ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በደም የተቆራኘና አንድ ህዝብ ነው። አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ በመጠባበቅ የቆየው የተሓህት አመራር በየካቲት መጨረሻ በ1968 በድርጅቱ የተሰባሰቡት ታጋዮች ዲማ በተባለው በአጋሜ አውራጃ ውስጥ የዲማ ኮንፈረንስ በመባል የሚታወቅ ኮንፈረንስ በማካሄድ ከ150 የማይበልጡ ታጋዮች በአረጋዊ በርሄ ሊቀመንበርነት በሚመራ ስብሰባ ፕሮግራሙ ቀርቦ እንዲጸድቅ ቢጠይቅም ታጋዩ አልተቀበለውም። ይሁንና፣ ሊቀመንበሩ ጸድቋል ብሎ የድረጅቱ የፖሊሲ አቋም ሆኖ እስከመጨረሻው ቀጥሏል። የተሓህት የሰሜን በጌምድር የወረራ ዝግጅት ተሓህት ወደ ሰሜን በጌምድር/ጎንደር በቀጥታ ሃይሉን አሰባስቦ አልገባም። ምክንያቱም፡

1. በመጀመሪያ ጊዜና ሁኔታውን ማስተከካል ፈለገ፤
2. ኢህአፓ በአካባቢው በስፋት ይንቀሳቀስ ስለነበር በአቅምና በትጥቅ ጥራት ህወሓት ዝቅተኛ ስለሆነ፣ ኢህአፓዎቹ ይመቱናል፣ ያጠቁናል የሚል ስጋት ስለአደረበት፣
3. የወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ህዝብ አይቀበለኝም ብሎ በማመኑ፣ አቅሙን እስኪያጠናክር መዘግየቱን እንደ አማራጭ ወሰደ። ቢሆንም ግን፣ ተሓህት በድብቅ በ1969 መጨረሻ ወደ ፀገዴና ፀለምት መሽሎክሎኩን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ ደጀና ውስጥ ሽሬላ ተብላ በምትታወቀው ትንሽ ከተማ የተሓህት ታጋዮች ቅዳሜ ቀን ህዝቡን ሲያንገላቱ በነበሩበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ቡድን ሁለቱን የተሓህት ታጋዮች በገበያው መሃከል ገደሏቸው። በታህሳስ 1972 በሻእቢያና በጀብሃ፣ በወያኔና በኢህአፓ መካከል በተነሳው ጦርነት በኢህአፓ በሰነዘረውጥቃት ተበታትነው ሱዳን ገቡ። በወልቃይት ፀገዴ ፀለምት የኢህአፓን ሠራዊት በበላይነት ሲመሩት የነበሩት ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ታደሰ ቅንጥሾ ወዘተ አስቀድመው ለወያኔ ህወሓት እጃቸውን ስለሰጡ፣ እየመሩም የኢህአፓን ሠራዊት እንዲጠቃ አደረጉ። በጥቃቱም ብዙዎቹ ተገደሉ፣ ተማረኩ፤ የተማረኩትም ተረሸኑ። ለዚህ ተጠያቂቆቹ ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ናቸው። ይህ ጊዜ ወያኔ ህወሓት ፍላጎቱ የተሳካበት ወቅት ነበር። አሁን ያለው የህወሓት አመራር በ1971 የካቲት 5 ቀን የተመረጡት፤ ስብሃት ነጋ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር፤ አረጋዊ በርሄ፣ ወታደራዊ አዛዥ፤ አባይ ፀሃየ፤ ግደይ ዘርአጽዮን፤ ስዩም መስፈን፤ መለስ ዜናዊ፤ አውአሎም ወልዱ፤ አርከበ እቁባይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤ ተወልደ ወ/ማርያም፤ ገብሩ አስራት፤ ስየ አብርሃ፤ ጽድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ በወያኔ የተገደለ፤ አስፍሃ ሃጎስ፣ ታሞ የሞተ ናቸው። የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩና ሁሉን ትእዛዝ የሚሰጡት ደግሞ፣ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ፤ አረጋዊ በርሄ፤ አባይ ፀሃየ፤ ስዩም መስፍን፤ ግደይ ዘርአጽዮን ናቸው። በወልቃይት ፀገዴ ጥቃቱን ያቀነባበሩት አመራሮች፤ ስየ አብርሃ፤ አርከበ እቁባይ፤ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤
አውአሎም ወልዱ ናቸው። እነዚህ በሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት ፀገዴ ትእዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ሲሆኑ፤ ይህንን ሁሉ በበላይነት የመራው ስብሃት ነጋ ሲሆን፤ የቅርብ ተባባሪዎቹ ደግሞ አባይ ፀሃየና አርከበ እቁባይ ነበሩ። ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር የሰሜን ጎንደር ኗሪ ሰላማዊ ህዝብ ለማጥቃት የታየው ሁኔታ አመራሩ ዝግጅት ያደረገው ነበር። በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን
ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን 3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።
ሁመራን በተመለከተ ወያኔ ተሓህት/ህወሓት የትግራይ ነው ቢልም በወቅቱ እስከ ግንቦት 1983 የኢትዮጵያ ምድር ጦር ሰፊ ጥበቃ ስለነበረው፣ ወያኔ ህወሓት መሬቱን የተቆጣጠረው አዲስ አባባን በያዘበት ጊዜ ነው። ወያኔ ህወሃት በትግ ላይ በነበሩበት ጊዜ 17 ዓመታት ሙሉ ሁመራ አልገባም፣ አልተቆጣጠረም። በአካባቢውም ድርሽ አላለም። ከላይ የተጠቀስው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መኮንን ዘለለው የህዝቡን አንበገርም ባይነትና የሰሜን በጌምድር አማሮች ነን ባይነት፣ ለወራት የቆየበትን ሪፖርት ለህወሓት አመራር ለስብሃት ነጋና ሌሎችም አቀረበ። ስብሃት ነጋ በመኮንን ዘለለው ላይ ወረደበት፣ ወዲያውኑም ከሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊነት አወረደው። በዚህ ክስተት ባይታሰርም የአእምሮ በሽታ ሰለባ በማድረግ አሰቃዩት። ከዚህ በመቀጠል የተነሳንበትን ታሪካዊ ትንተና በተጨባጭ ለማረጋገጥ የቀድሞውን የሃገራችን ኢትዮጵያን ካርታ በ “ሀ” እንዲሁም ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ ከያዘ በኋላ ያዘጋጀውን ካርታ በ”ለ”፣ የበጌምድር ጠ/ግዛትን እና የትግራይን ጠ/ግዛት የወሰን ክልል ደግሞ በ “ሐ” ና “መ” ላይ በማነጻጸር እንመልከት።

(ስእሎቹን ከታች ይመልከቱ )

Hand Draw - Ethiopa Map 1Hand Draw - Ethiopa Map 2Hand Draw - Ethiopa Map 3Hand Draw - Ethiopa Map 4

“ሀ” በሚለው የኢትዮጵያ ካርታ በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታትና ህዝብ ያመኑበት፣ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካአንድነት ድርጅት ተቀባይነት ያለው የኢትዮጵያ ግዛት መልክአ ምድር ካርታ ነው። በኢትዮጵያ በቅደም ተከተል የመጡ መሪዎች እስከ ደርግ ዘመን መንግሥት ይህንኑ ተቀብለውና አምነው ኢትዮጵያና ህዝቧ አንድነቱን ጠብቆ የሃገሪቷን ዳር ድንበር በመጠበቅ ኢትዮጵያን የመሩበት ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ካርታ ነው። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ የጠቃላይ ግዛቶች የወሰን ድንበር ሳይካልለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ በፈለገውና በመረጠው ጠ/ግዛት ሄዶ በመንግሥት ሥራ፣ በእርሻ፣ በንግድ፣ በአንጥረኛነት፣ በሸማኔነት ወዘተ በመሥራትና የሃገሪቱን ሕገመንግሥት በመከተል ትዳር መስርቶ፣ ኢትዮጵያዊነትን ከደመ ስጋው ቀላቅሎና ኮርቶ የሚኖር ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ በልጆቿ ተከብራ ለዘመናት የቆየች ሃገር ናት። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባት ሃገርም ነበረች። ዛሬስ? የሚለውን ጥያቄ እንደሚከተለው እንመለከተዋለን። ታሪካዊው የጠ/ግዛቶች የንድንበር ክልል የኢትዮጵያ ጠ/ግዛቶች ድንበር በ “ሀ” ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ካርታን ብንመለከተው በቂ ግንዛቤ ይሰጠናል። ይህ ደግሞ ለዘመናት ጸንቶ የቆየ ነው። ለዚህም ነው ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተቆራኘው። የበጌምድር ጠ/ግዛትና የወሎ ጠ/ግዛትን ስንመለከት የበጌምድር ጠ/ግዛትና የትግራይ ጠ/ግዛት ድንበርን ያካለለው ታሪካዊው የተከዜ ወንዝ ነው። ተከዜ ወንዝ በምእራብ በኩል በጌምድርን፣ በምስራቅ በኩል ትግራይን ለይቶ በማካለል ለብዙ ዘመናት ጸንቶ የቆየና የኢትዮጵያ ነገሥታትም ያመኑበት ድንበር ነው። ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ስለሚገኙም ሰሜን በጌምደር (ጎንደር) ተብለው ይጠራሉ። ይህ ደግሞ በተልያዩ የታሪክ መጽሐፍት የሚገኝ እውነት ነው። የኢትዮጵያ ግዛቶች በወሰን ክልላቸው የሚታወቁት ከጥንት ተያይዞ የመጣ በመሆኑ በትግራይና በጌምድር፣ በትግራይና በወሎ እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ድረስ ያስነሳው ግጭትም ሆነ ይገባኛል የሚል ጥያቄ ተንስቶም አያውቅም፣ አይታሰብብምም። የትግራይ ህዝብ ሰሜን በጌምድር የትግራይ ነው አላለም። ይህንን ተስፋፊነት የፈጠረው የተሓህት አመራር ነው።ይህ በህ.ወ.ሓ.ት የተፈፀው ሰባአዊ መብት ረገጣም በከፍተኛ የወንጀል ተጠያዊው ወያኔ ነው።ሰሜን ጎንደር ‹፣አማራ ነው ግዛቱም የጎንደር ነው። በኢትዮጵያ ታሪክም የሚታወቀው ወልቃይት..ፀገዴ..ፀለምት..ሁመራ..ወ፣ዘ፣ተ.የጎንደር ግዛቶች መሆናቸው ነው። የድንበርን ቋንቋ በተመለከተ በዚህ ዓለም በድንበር የሚገናኙ የተለያዩ ሃገራት አንዱ የአንዱን ቋንቋ ይናገራሉ። ለምሳሌ፤ ቤልጂየምን ብንመለከት፣ ፈረንሳይና፣ደች፣ ጀርመንኛ የሚናገሩ ሕዝቦ አሏት። ነገር ግን የቤልጂየም ዜጎች እንጂ ቋንቋውን በመናገራቸው የፈረንሳይ፣ ጀርመን ወይም የኔዘርላንድ ዜጎች አይደሉም። በኢትዮጵያ ውስጥም በድንበር የሚዋሰኑ ጠቅላይ ግዛቶች፣ አፋሩ ትግርኛና አማርኛ ይናገራል፤ ትግራይም አማርኛና ትግርኛ ይናገራል፤ አማራውም ኦሮምኛና ትግርኛ፣ አርጎብኛ፣ ጉራጌኛ ይናገራል። በቋንቋ ድንበርን ለመወሰን ፈጽሞ አይቻልም። ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት ግን የታላቋን የትግራይ ሪፓብሊክ ለመፍጠር፣ የበጌምድር ጠ/ግዛትን እና የወሎ ጠ/ግዛትን ለም መሬቶች ትግርኛ ይናገራሉ በሚል ቁንጽል አስተሳሰብ በጉልበቱ መሬት ነጥቋል። የሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት፤ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ፣ ባህላቸውና ቋንቋቸው አማራ ነው። ይህም ለብዙ ዘመናት እየዳበረ የመጣ ሲሆን፣ በተከዜ ወንዝ ዳር የሚኖሩ ዜጎች ትግርኛ መናገር ቢችሉም ዋናው ቋንቋቸው አማርኛ ነው። ሙሉው የዘር ሃረጋቸውም አማራ ነው። ስለሆነም እነዚህ ዜጎች የአማራ ሕብረተሰብ አካል ናቸው። ከትግራይ ሕብረተሰብ ጋር የሚያገናኛቸው ኢትዮጵያዊነታቸው ነው። በጋብቻ በመተሳሰር በሰላምና በፍቅር የኖሩ፣ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ ህዝብ ናቸው። በዚህም ምክንያት የትግራይ ህዝብም በበጌምድርና በወሎ ህወሓት የፈጸመውን ተስፋፊነት አልተቀበሉትም። በእነዚህ ሶስት ጠ/ግዛቶች፣ ማለትም በጌምድር፣ ትግራይና ወሎ የመሬት ይገባኛል የድንበር ክልል ተነስቶ አያውቅም። የሚነሳበት ምክንያትም የለም። የሕግ መሰረት እነዚህ ከበጌምድር ጠ/ግዛት በተሓህት/ህወሓት የተነጠቁት መሬቶች፣ ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ደግሞ ደቡብ ወሎ የተነጠቁት ቦታዎች ሕገወጥ ናቸው። ተስፋፊው ተሓህት በፕሮግራሙ መቅድም በሚለው አርእስት ያካተተው የትግራይ ቦታዎች ናቸው የሚለው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያው፣ ከ1969 ጀምሮ በቁርጠኝነት የተቃወመው ነው። እኛን ከህዝቡ በመነጠል ችግር እንዲፈጠር አታድርጉ፤ የምትሉት መሬት በታሪክም የትግራይ አልነበረም ባለበት ጊዜ ነበር “ትግራዋይ ሸዋዊ” የሚል ስም የሰጡት። ህዝብ ያልተቀበለው ተስፋፊነት ደግሞ አምባገነን እና ፋሽስትነት ነው። ስለሆነም በሕግ ተቀባይነት የለውም።ተሓህት/ህወሓት በጉልበት የነጠቃቸው መሬቶች ካለምንም ውጣ ውረድ ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ይመለሳሉ። ህዝብ በጠራራ ጸሓይ መሬቱ አይነጠቅም አይፈናቀልም ።በህዝብ ሬፈሬንደም ይወሰናሉ፣ ለምን? በካርታ “ሀ” ላይ የተመለከተውን ታሪካዊ የሚያደርገው፣ በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ተቀብለውት የጸና ሆኖ ብዙ ዘመናት ያስቆጠረ ስለሆነ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ አምኖበት የተቀበለው፣ በምንም መልኩ የድንበር ግጭትና ኹከት ያልፈጠረ፣ ዜጎች
ሁሉ አምነውበትና ኮርተውበት ኢትዮጵያውያዊነታቸውን አጠናክሮና አቅፎ የተጓዘም ስለሆነም ነው።
አንዳንድ የተሓህት/ሀውሓት አመራርና ነባር አባላቱ የድንበሩ ጉዳይ በህዝበ ወሳኔ ይፈታ የሚሉ አሉ። ይህ በተሓህት/ህወሓት የተፈጸመው የመስፋፋት ጉዳይ ሕገወጥ ነው። የሰሜን በጌምድር መሬት፣ የደቡብ ወሎ መሬት ለድርድር ሳይቀርቡ በቀጥታ ወደ ቀድሞ ግዛታቸው ይመለሳሉ። ለህዝበ ውሳኔ ይቅረብ ማለት ፌዝና ቀልድም ጭምር ነው። ስለሆነም ህዝበ ውሳኔ ሕገወጥ ነው። ፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ፀለምት፣ ሁመራ የበጌምድር (የጎንደር) ግዛት ናቸው። በወሎም፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ፣ ራያና ቆቦ፣ አላማጣ የወሎ ጠ/ግዛት ናቸው። የወያኔ ህወሓት አመረራርና አባላቱም ጭምር ይህንን አምነው መቀበል ግዴታቸው ነው። የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጄል ተሓህት/ህወሓት ሲፈጠር ተስፋፊነትን የፖሊሲው አቋም አድርጎ የተነሳ ድረጅት ነው። 5ኛ ፕሮግራሙን እንመልከት።

ተስፋፊነት ደግሞ ፋሽስት፣ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ ምህረት የለሽ ነው። ተፈጥሯዊው ባህሪውም ስለሆነ በዚሁ ነው የሚያድገው። ተሓህት/ህወሓት ታህሳስ 1972 በቀጥታ የዘመተው ወደ ሰሜን በጌምድር ነበር። ዘመቻው ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን የአማራ ዜጎችን ለማጥፋት የወጣ እቅድ ነው። በትግራይ ውስጥም አማራ ደመኛ ጠላትህ ነው ሲሉት፣ አማራ ለትግራይ ጠላት አይደለም፣ ወንድማችን ነው፣ በጋብቻና በዘር ደማችን የተቀላቀለ ኢትዮጵያዊ ነን በማለት በቆራጥነት አቋሙን የገለጸ ህዝብ ነው። “የትግራይ የሸዋ” በሚል ከገጠሩ ጀምሮ እሰክ ከተሞች የግድያ እልቂት የሚፈጸምበት ጊዜም ነበር። የትግራይ ህዝብ አማራ ወንድሜ፣ እህቴ፣ ልጆቹ ልጆቼ፣ ሁላችንም የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነን በማለቱ በስንት ሺህ የሚቆጠር ህዝብ በህወሓት 06 ሓለዋ ወያነ እየገባ በጥይት ተደብድቦ ከባድ መስዋእትነት የከፈለ የአማራው አጋር ኢትዮጵያዊ ነው። ወያኔ ህወሓት ወደ ሰሜን በጌምድር ሲዘምት ዋናው አስተባባሪ ሆኖ እልቂቱ እንዲፈጸም ያስተባበረው የድርጅቱ ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ነበር። ከስብሃት ነጋ ጋር በመተባባር በተግባር የዘር እልቂት እንዲፈጽሙ የተመደቡት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ፣ አርከበ እቁባይ፣ ስዩም መስፈን፣ ዘርአይ አስገዶም፣ ስየ አብርሃ ናቸው። በእልቂቱ የታሰተፉ ተዋጊ ሃይሎች የተመሩት ደግሞ፣ በሳሞራ የኑስ፣ ተከስተ እስጢፋኖስ፣ ታደሰ ወረደ፣ መኮንን አሊሱም ሲሆኑ፤ ክርቢት ተብለው የሚታወቁት ሽብርተኛ ጋንታ የተመሩት ደግሞ፤ በሻሸይ በላይ፣ አሰፋ ማሞ፣ ጸጋይ ቆማጥ፣ መሃሪ፣ ዳሳ ጉግሳ ነበሩ። አምስተኛ ክርቢት ደግሞየተመራው በአርከበ እቁባይ ሲሆን፣ ስምሪታቸው በፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ፀለምት ነበር። እዚህ የሚኖረው ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ነው። እኛ በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን አማሮች ነን በማለታቸው፣ በቀንና በሌሊት እሳተ ነበልባል ወረደባቸው። በስብሃት ነጋ በሚመራው የህወሓት ሰራዊት ከያሉበት እየተለቀሙ በጥይት እየተደበደቡ አለቁ። ሃብት ንብረታቸው፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ የጋማ ከብት፣ ያፈሩት ንብረት ሁሉ በህወሓት እየተዘረፈ ወደ ትግራይ እየመጣ የሰራዊቱ ቀለብ ሆነ። ቤት ፈረሰ፣ ወላጆች፣ ህፃናትን ጨመሮ በህወሓት አለቁ። ቤተሰቦች እየተሰበሰቡ እቤት ወስጥ እየታጎሩ አርከበ እቁባይ በሚመራው ክርቢት እሳት እየተለቀቀባቸው በእሳት አጋይተው ጨረሷቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ በብስራት አማረ የሚመርው ጨካኝና አረመኔ ሰራዊት፣ የቡድኑ አባላት፤ አሰፋ ጉሬዛ፣ ሃይሉ በርሄ፣ ልኡል በርሄ፣ ዘርአይ ይህደጎ፣ ካህሳይ ቆራጽ፣ ዘውዱ፣ ገብረዮሃን ለህወሓት የስለላ ሥራ ወልቃይት ፀገዴ ተሰማርተው ነበር። በፀለምት በኩል ደግሞ በዘአማኑኤል ለገሰ የሚመራና ተጠሪነቱ ለብስራት አማረ የሆነ ቡድን ተሰማርቶ ነበር። የቡድኑ አባላት፣ አደም፣ ታደሰ 06፣ ታደስ መሰረት፣ ተስፋየ አፅብሃ (አፍርሰው)፣ መሃመድ፣ ፍሬ ጎይትኦም (ሴት) ነበሩ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ሃለዋ ወያኔ እያስገቡ መግደል ስለሚመቻቸው፣ ለወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት አመቺ የሆኑ ሃለዋ ወያኔ ተከፈቱ። እነሱም፣
1. ፍየል ውሃ ፀገዴ፣ በክንፈ ገ/መድህን የሚመራ፣
2. ባኽላ ሳሞረ፣ የፀገዴ ዳር፣ በሙሉጌታ ወዛም (ማይዶ አስክን) ዛሬ በአሜሪካ የሚኖር፣
3. ሱር ለፀለምት አቅራቢያ፣ በአበበ ተክላሃይማኖት የሚመራ (የአየር ሃይል አዛዥ ጄነራል ነበር)
የወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ህዝብ በነብስራት፣ አማራው በቀንና በሌሊት እየታፈነ በሶስቱ ሃለዋ ወያኔ እየገባ በአማራው የሰሜን
በጌምድር ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጄል ህወሓት በመፈጸም ላይ እንዳለ፣ ቦታው በመጣበቡ ምክንያት ሌላ ሃለዋ ወያነ መጀመሪያ በሃሰን ሹፋ የሚመራ ሃለዋ ወያነ የአማራው ሕይወት ተቀጠፈ፤ በጅምላ ጉድጓዶች እየገቡ በፍየል ውሃ፣ በባኸላ፣ በሱር፣ በገሃነብ፣ በህወሓት ጥይት እየተደበደበ ያለቀው ህዝብ ቤት ይቁጠረው። መሬቷና በአካባቢው ከሞት የተረፈው ምስክርነት ይሰጥበታል። ተሓህት/ህወሓት የአማራውን ህዝብ ዘር ማጥፋት የጀመረው ከ1969 መጀመሪያ ቢሆንም በክፉና
አሰቃቂ መልኩ የጀመረው በ1972 ታህሳስ ሲሆን ለረጅም አመታት ግድያው ቀጠለ።
ከዚህ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰበት የወልቃይት ፀጋዴ ፀለምት ህዝብ አሁን በእድል ከሞት ተርፎ ቤተሰቦቹ ያለቁበት ዜጋ፣ በዛን ጊዜ የህወሓት አመራር ጠላቶቼ እነማን ይሆኑ? የሚል አእምሮውን የሚረብሹ ጥያቄዎች አሉ። ስለሆነም እዚያ የነበሩ የተሓህት/ህወሓት መሪዎች እነሆ ተቀበሉ። ጊዜውም ከ1967 እሰከ 1977 ነበር።
1. ስበሃት ነጋ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ፖሊት ቢሮ
2. አረጋዊ በርሄ፣ ወታደራዊ አዛዥ ፖሊት ቢሮ
3. ግደይ ዘርአፅዮን፣ የህወሓት ም/ሊቀመንበር ፖሊት ቢሮ፣ ፕሮግራሙን ያልጠበቀ
4. አባይ ፀሃየ፣ ፖለቲክዊ ጽ/ቤት ፖሊት ቢሮ
5. ሥዩም መስፈን፣ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ፖሊት ቢሮ
6. መለስ ዜናዊ፣ የፖለቲካ አዘጋጅ ማ/ኮ
7. አውአሎም ወበዱ፣ የሪጅን 1-2 ሃላፊ ማ/ኮ
8. አርከበ እቁባይ፣ ወታደራዊ ማ/ኮ
9. ስየ አብርሃ፣ ወታደራዊ ማ/ኮ
10. ዘርአይ አስገዶም፣ ከተማ ግንኙነት ማ/ኮ
11. ተወልደ ወ/ማርያም፣ የገጠር ግንኙነት ማ/ኮ በህመም ምክንያት ሱዳን የሄደ
12. ገብሩ አስራት፣ የሪጅን 3 ሃላፊ ማ/ኮ
13. አስፍሃ ሃጎስ፣ የውጭ ጉዳይ ማ/ኮ
14. አታክልት ቀፀላ፣ በአመራሩ የተገደለ ማ/ኮ፣ በ1971 የተገደለ
15. ጻድቃን ግ/ተንሳይ፣ ወታደር ማ/ኮ

ከዚህ የዘር ማጥፋት ወንጄል፣ የአማርኛ ቁንቋ የአማራው ገዢ መደብ ቋንቋ ስለሆነ አብሮ መጥፋት አለበት ተብሎም ከዘመቻው አንዱ ሆነ። ከዚህ በተጨማሪ፣ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ስር የሰደደ እምነት አብሮ ይጠፋል ሲሉ ነበር። የህወሓት ፋሽስት ቡድን ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ከዚህ ቀጥዬ የማቀርበው፣ እኔ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በወቅቱ የነበርኩት አዲስ አበባ ውስጥ ነበር። እነሱ ኢትዮጵያን ወረው ሲቆጣጠሩ ደግሞ ዩጋንዳ፣ ካምፓላ ስለነበርኩ የማቀርበው ሃተታ በትግሉ ወቅት ጓዳኛዬ የነበረ፣ በ1968 በተሓህት አበርን የተሰለፍን ግለሰብ የነገረኝን ነው። ገና ከመነሻው ጀምሮ የጋንታ መሪ፣ የሃይል መሪ፣ የባታልዮን መሪ፣ የብርጌድ መሪ፣ የክፍለ ጦር መሪ፣ እየሆነ የመጣ በትግሉ ታዋቂ የነበረ ታጋይ ነበር። ኢትዮጵያን እነደተቆጣጠሩ፣ የሽግግር መንግሥት ተብሎ ሲቋቋም በጸረ- መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ተፈርጄ ህዳር 1984 ተባረርኩ ያለኝ የህወሓት ታጋይ የነበረ ነው። ይህ ግለሰብ ከህወሓት ሰራዊት ብቻውን ሳይሆን በርካቶች መባረራቸውን ነግሮኛል። አሁን የምተዳደረው በግሌ በአነስተኛ ንግድ ነውም ብሎኛል። የተገናኘነው ዩጋንዳ፣ ካምፓላ ለግል ሥራ በመጣ ጊዜ ነበር። ወሩና ዓ. ምን ጭምር እቤቴ እንደገባሁ በማስታወሻ ይዤው ነበር። ህወሓት በኔ ላይ በዙ ችግሮች እየፈጠረብኝ የነበረበት ጊዜ ስለነበር፣ እንኳን ለማነጋገር ለመቆም እንኳን አእምሮዬ ሊቀበልልኝ አልቻለም። እሱም እንደተጠራጠርኩት ስላወቀ፣ እኔን አትጠራጠረኝ፣ በኔ ላይ የፈጸሙብኝን ብነግረህ ታለቅሳልህ ሲለኝ በመጠኑም ቢሆን ተቀበልኩት። የተገናኘነው ሚያዚያ 1985 ነበር። ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ምንም ችግር ሳይገጥመን ካለ ምንም ጦርነት ከትግራይ በመኪና ተጭነን አዲስ አበባ መጥተን ነበር። ሃገሪቷ በእጃችን በወደቀችበት ጊዜበየመንገዱና በየቦታው የሃገሪቷን ሃብትና ንበረት ዘርፈናል። ደርግ ዘራፊ ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን አንዲት ብር ሳትነሳ ያገኘነው ባንክ ቤቶች፣ የመንግሥት ግምጃ ቤቶች፣ ያለውን ገንዘብ ጠራርገን ነበር የወሰድነው። አዲስ አበባ ስንገባ ሁለት ክፍለ ጦሮች ባንክና ማንኛውንም የገንዘብ ተቋሞች እንድንጠብቅ ከተመደቡት አንዱ የኔ ክ/ጦር ስለነበር፣ የህወሓት አመራር በቀንና በሌሊት ፖሊት ቢሮ አመራር የበላይ ሆነው የሚቆጣጠሩት ስብሃት ነጋና አዲስ አበባ ስንገባ ለሁለት ቀናት ለንደን የቆየው መለስ ዜናዊ ሆነው ለዘርፊያ ተሰማሩ። በዝርፊያው የተሰማሩት የፖሊት ቢሮ አባላትም፣ ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ አርከበ እቁባይ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ ስየ አብርሃ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አባይ ፀሃየ፣ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ) በዋናነት የሃገር ሃብት፣ ገንዘብ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ ውድ ቅርሳቅርስ ዘርፈዋል። የተዘረፈው ሃብትም መለስ ዜናዊ በሚኖርበት ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ተከመረ። እኛም ዘርፈናል በማለት የጀመረውን ጨዋታ ቀጠለ። ይህ የትግል ጓደኛዬ በአድዋ አውራጃ ቢወለድም አብዛኛው ቤተሰቦቹ ጎድንደርና አዲስ አበባ ይሚኖሩ ናቸው። የትምህርት ደረጃው ከአንደኛ ደረጃ ባይዘልም በኢትዮጵያ ላይ ጥሩ አመለካከት እንዳለው ከፊቱ ይነበባል። ከአጫወተኝ ሁሉ ትኩረት የሰጠሁት፤

1ኛ፣ የህወሓት ፖሊት ቢሮ ኢትዮጵያን እንደሚቆጣጠርና እንደሚመራ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት በእርግጠኝነት ሲናገሩ፣ የኢትዮጵያ ምድር ጦር፣ አየር ሃይል፣ ባህር ሃይል በቀላሉ እንደማይሸነፉ ያውቁ ስለነበር፣ ሁለቱ መንግሥታት ይጨነቁ ስለነበር፣ በርካታ የጦር መሳሪያ ለህወሓት ይሰጧቸው ነበር። 2ኛ፣ የህወሓት የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ተብሎ ኢትዮጵያን ለመምራት ስለማይችል በፍጥነት ስማቸውን እንዲለውጡ ማድረግ። በዚህ መሰረትም የህወሓት ፖሊት ቢሮ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣ ስየአብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አርከበ እቁባይ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ አውአሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ ተወልደ ወ/ማርያም ህዳር 1982 መቀሌ ከተማ ተሰብስበው የሚፈለገው ስም ለማውጣት አራት ቀን ተዘግተው በጭንቀት ላይ ቆዩ። በመጨረሻም ተወልደ ወ/ማርያምና አለምሰገድ ገ/አምላክ የመጨረሻ አማራጭ በለው ያቀረቡት ስም፣ “የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር” (ኢህአዴግ) እንዲባል ፖሊት ቢሮ ተቀብሎ አጸደቀው። እንደ ወጥ ማጣፈጫ የሚጠቀሙበት ብአዴን በግንባሩ ውስጥ ከተቀላቀለ ኢህአዴግ አስተማማኝና ተቀባይነት ያለው ስም ይሆናል ተባለ። ውሳኔውን እንግሊዝና
አሜሪካም ተቀብለውታል። ብአዴን የተጨመረው አማራ ብሄር ሆኖ፣ “ህዝቦች” የምትለው ቃል ስትሸፍን፣ ‘አብዮት’ የምትለው ቃል ደግሞ ወያኔን ትሸፍናለች። የህወሓትን የበላይነትንም ታረጋግጣለች። በሌላ መልኩ ደግሞ፣ ህዝቦች የሚለው ቃል የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ኢትዮጵያ ሳይሆን በዘፈቀደ የተሳባሰበ ነው ለማለትና በዘርና በቋንቋ ከፋፍለው ለመግዛት የሚጠቀሙበት፣ ለሥልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ የሚያደርጉበት ነው። 3ኛ፣ ህወሓት በሚከተለው ፖሊሲ መሰረት የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ አለ መሆኑ ሻእቢያም የኤርትራ መሬትና ወደብ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ነው፣ በማለት ስለአረጋገጡ አሰብን ወደ ኢትዮጵያ አካለለች። እንግሊዝ ሃገር ልካችሁ ካርታችሁን አዘጋጁ የሚል ሃሳብም ቀርቦላቸዋል። ፖሊት ቢሮው በሙሉ ወደ እብደት ወሰዳቸው። አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም፣ አሰብን አናካትትም በማለት፣ በተለይም ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ ብርሃን ገ/ክርስቶስ ወዘተ በጥብቅ በማውገዛቸው የተነሳ እንግሊዝና አሜሪካም ሃሳባቸውን በመቀልበስ ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ አደረጓት። ይህንን ሁሉ የነገረኝ ይህ የቀድሞ ጓደኛዬ በንጹህ ልቦና ቢሆንም፤ እኔ ግን የህወሓትን እርኩስ ተግባር ስለማውቀው እስክንለያይ ድረስ መጠርጠሬ ከፍተኛ ነበር። ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ከማንም የማላገኘው እውነታ በመሆኑ ጥሩ ግንዛቤ ስጥቶኛል። ቀደም ብዬ የማውቀው የወያኔ ህወሓት ፀረ-ሃገርና ፀረ-ህዝብ የመሆኑን እምነቴን አዳብሮልኛል። በተለይ በአማራውና በኦሮም ህዝብ ላይ የሚፈጸምውን ክፈተኛ ግፍ በጽናት አውግዞታል። ይህንን ካልኩ በኋል ወደ ወናው ሃሳቤ ስመለስ፣ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ፣ ፋሽስቱ ህወሓት ወያኔ ከሰኔ 1983 ጀምሮ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ካርታ ሃገር የሚያፈርስ፣ ህዝብ የሚበትን፣ ደመኛ ጠለትነቱን ያረጋገጠ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በትክክል ያውቃል። ሆኖም፣ ሃሳቦቼን በገጽ 5 ስላስቀመጥኩት፣ በትኩረት እንመልከተው። በ “ለ” ላይ የተመለከተው የኢትዮጵያ ካርታ የተዘረዘሩት የህወሓት አመራር ያዘጋጀውና ሆን ተብሎ የተሰራና የተወጠነ ነው። ምክንያቱም፣1ኛ፣ ካርታው እንደሚያመለክተው፣ የአማራውን ነገድ በታትኖ ዘሩን ለማጥፋት፣ ሰሜን በጌምድር ፀለምት፣ ፀገዴ፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ፣ ሁመራ፣ በቀጥታ ወደ ትግራይ ግዛት ሲካለሉ ከወሎ ደግሞ ራያና ቆቦን፣ አላማጣን፣ አፍላ ደራ፣ ወልዲያ፣ እነዚህንም ወደ ትግራይ ግዛት ተካለሉ። ህወሓት ታላቋን ትግራይ በጉልበቱ ነጥቆ ፈጠራት። ወሎ አሁንም ቀድሞ ከነበረው ግዛቷ ከግማሽ በላይ ወደ አፋር ተካለለ። የቀድሞዋ ጠ/ግዛት ወሎ አሁን የለችም። የቀድሞዋ የበጌምድር ጠ/ግዛት አሁን የለችም። ጎጃም፣ ሸዋ የሉም። መተማና ሌሎች ወረዳዎች ወደ ቤኒሻንጉል ተካለዋል። ወያኔ ህወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ አማራው ተበታትኖ መኖሪያ አልባ ሆነ። ከተወለደበት፣ ካደገበት ቀዬ ተባረረ። ከርታታና ማደሪያ የሌለው ሆኖ ለረሃብ፣ ለበሽታና ለብዙ ችግር ተዳረገ። የአማራው ህዝብ የሚኖርባት ክልል ከአንድ አውራጃ ያነሰች ሆነች።
2ኛ፣ ይህ የህወሓት የካርታ ክልል ኢትዮጵያዊነንት ፍጽሞ የሚያጠፋ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አንድ ህዝብ ሆኖ በአንድነቱና በኢትዮጵያዊነቱ እንዳልኖረ ሁሉ፣ የህወሓት አመራር ይህን እውነታ በመጻረር ሃገርን በጎሳ፣ በቋንቋ ከፋፍለውታል። የቀድሞው የወያኔ ግፈኛው ፋሽስት መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በጻፈው “TPLF’s Strategies for Establishing its Hegemony and Perpetuating its Rule” በሚለው ጽሁፍ የህወሓትን ዓላማ፣ ማለትም ሁሉንም የሃገሪቷን ጉዳይ በመቆጣጠር በቀጣይነት መግዛት ነው፣ በማለት አስቀምጦታል። ይሄንን ከገቡ ለማድረስ፣ ተቃዋሚ ሃይሎችን ማጥፋት፣ ነፃ ሚዲያን በማጥፋት የህወሓት ልሳናትን ማሳደግ፣ የህወሓት ደጋፊዎችን የሥራ እድል መስጠት፣ ቁልፍ የፕሮፓጋንዳ መሥሪያ ቤቶችን፣ ማለትም፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ የብዙሃን መገናኛዎችን፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ሬዲዮ፣ ቲሌቪዥን ወዘተ በመቆጣጠር የህወሓት አገልጋይ ማድረግ በማለት ጽፏል። በዋናናት ያስቀመጣቸው ደግሞ፣ ሃይማኖት ከአድሃሪው ህብረተሰብ ጋር የተቆራኙ ስለሆነ ያ መቋረጥ እንዳለበት ጽፏል። መለስ ዜናዊ አድሃሪ ህብረተሰብ የሚለው፣ ሙስሊሙን፣ ክርስቲያኑን፣ ወዘተ ነው። አስከትሎም፣ አድሃሪ፣ የለውጥና የእድገት ተቃዋሚ የሚላቸው ደግሞ መላውን ኢትዮጵያዊ ሲያንቋሽሽ ነው።
3ኛ፣ ያለፈው የአማራው ትምክህተኛ አገዛዝ ኢትዮጵያዊነት ዘልቆ የተዋሃደውና ከደመ ነፍሱ ጋር የተሳሰረ ነው። ይህንን ከህዝቡ ሰነአእምሮ ነቅለን ለመጣል፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቁንቋ ማደራጀትና በዚህ ዓላማ የሚመሩ ድርጅቶችን መፈጠር ይላል። እነዚህ ከላይ የተጠቀስኳቸው የህወሓት መርሆዎች ገና ትግሉ እንደተጀመረ በኢህአፓ ላይ የፈጸመውን ወንጀል ማስታወስ ይበቃል። ኢህአፓ በኢትዮጵያዊነቱ ያመነና የተደራጀ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ፣ ማለትም አፋን፣ አማራውን፣ ትግሬውን፣ ኦሮሞውን፣ ጉራጌውን፣ ኦጋዴኑን፣ ጋምቤላውን ወዘተ ያቀፈ፣ በዘር፣ በቋንቋ የማያማን ድርጅት ነበር፤ ለዚህም ነው በህወሓት የተደመሰሰው። በሃይማኖቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍም ህወሓት ገና በትግሉ ጊዜ እስልምና እና ክርስትናን ለማጣፋት ታጥቆ የተነሳ እንደነበርና አሁንም በትገባር እያሳየው ያለ ጉድይ ነው። ህወሓት ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳውም ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ነው። እንደዋናው ዓላማው አድርጎ የተጠቀመበት ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አስቀድመን አማራውን ማጥፋት ብሎ ከ1969 መጀመሪያ ጀምሮ ነበር። አማራውን ከትግራይ ውጡ በማለት የግፍ ግድያ የተፈጸመባቸው በዚህ ምክንያት ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ህወሓት የአማራን ዘር ማጥፋቱን ቀጠለበት፣ አሁንም አላቋረጠም። የካርታው ዓላማ ህወሓት በዘር፣ በጎሳና በቋንቋ የከፋፈለው፣ የህወሓት መሪዎችን የግዛት እድሜአቸውን ለማራዘም ነው። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የመግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖር ለማድረግ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛ የህዝብ መግባቢያ ቋንቋ በመሆኑ ይህንን በማጥፋት ኢትዮፕያዊነቱን እና አንድነቱን ለማጥፋት የሸረበው ተንኮል ነው። አዲሱን ትውልድ በጥቅማ ጥቅም በመያዝ ሊያዘናጋ ቢሞክርም፣ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዱሮው በበለጠ አማርኛ ቋንቋን በንግግርና በሥነጽሑፍ አስፋፍቶ በኢትዮጵያ ውስጥና ውጩንም ጨምሮ ኢትዮጵያዊነቱን በማጠናከርና በማቀፍ በበለጠ እድገት እየተራመደ ነው። የወያኔ ህወሓት መሪዎች እቅድ ከሽፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ይበልጥ ኢትዮጵያዊንቱን በማጠናከር ተከፋፍለን አንገዛም በማለት ሁሉም በሃይማኖቱ፣ ሙስሊሙ፣ ካቶሊኩ፣ ፕሮቴስታንቱ፣ ኦርቶዶክሱ አንድነት ፈጥረው የህወሓት ፋሽስቱን መሪዎች መፈናፈኛ ያሳጣቸው ጊዜ አድርገውታል። ከዚህም የተነሳ የመለስ ዜናዊ ጽሑፍ ውድቅ ሆኖ ቀረ። (ይህንን የመልስ ዜናዊን ጽሑፍ ያገኘሁት፣ Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE) ድረገጽ ሲሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው የህወሓት ወያኔን ዓላማ ለማወቅ ያስችለዋል። አርእስቱ፣ “TPLF’s Strategies for Establishing its Hegemony and Perpetuating ኢts Rule” ነው።

በህወሓት አመራ የተፈጸመ የዘር ማጣፋት ወንጄል
ወደ ዘር ማጥፋት ከማቅናታችን በፊት ህወሓት ማን ነው የሚለውን በአጭሩ እንመልከት፤
1ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ከመጀመሪያ ጀምፎ ቅጥረኛ ነፈሰ ገዳይ ሆኖ የተፈጠረ፣ የባእዳንን ተልእኮ ለማስፈጸም የተደራጀ ድርጅት ነው። ጥቁር የአፍሪካ ናዚ።
2ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ተስፋፊ ድርጅት ነው። ታላቋን የትግራይ መንግሥት ለመመስረት ከበጌምድር ጠ/ግዛትና ከወሎ ጠ/ግዛት በህገወጥ መንገድ የነጠቀውን ቦታዎች እንመልከት፣
3ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ጠባብ፣ ዘረኛ፣ ፀረ-የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና ፀረ-የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነና በባእዳን የተፈጠረ ድረጅት ነው፣
4ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ሽበርተኛ ድርጅት ነው። ከ1969 ጀምሮ በጠራራ ፀሃይና በሌሊት ፈዳያን ብሎ ባሰለጥገናቸውና በብስራት አማረ በመመራት ህዝብ ፈጁ
5ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት ፀረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሕዝብ ሆኖ የተፈጠረ ድረጅት ነው። ይህ የማፊያ ድረጅት ኢትዮጵያን ለ24 ዓመታት እየገዛ ያለ ድርጅት ነው።
6ኛ፣ ተሓህት/ህወሓት የሰው ሃብት ቀማኛና የሃገር ታሪካዊ ቅርሶችን፣ የሃገር ሃብትን ዘራፊ ድርጅት ነው። ከዚህም አልፎ፣ ህዝብ እያፈናቀለ ኢትዮጵያን ለባለሃብት ባእዳን ሃገሮች በመሸጥ የተሰማራ ድርጅት ነው። ይህ የባእዳን ቅጥረኛ ደርጅት ብዙ የከፋ ባህሪ ያለው ድርጅት ነው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ብዙ ነገሥታትን ያሳለፈች፣ ዝነኛና ባለታሪክ ሃገር ናት። እንደ ወያኔ ህወሓት የመሰለ በታሪኳ አጋጥሟት አያውቅም። በ845 በዮዲት ጉዲት፣ በ15ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ መሃመድ አጥፊ ወራሪ ቢገጥማትም፤ ህወሓትን የመሰለ አረመኔና ፋሽስት፣ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማጥፋት የተሰማራ፣ ተወዳዳሪ የሌለው እኩይ ድርጅት ህወሓት ብቻ ነው። የህወሓት የዘር ማጥፋት ዓላማና ተግባር ህወሓት በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጄልን ስራዬ ብሎ የተያያዘው ከ1969 ጀምሮ ነው። በትግራይ ሰላማዊ ዜጎችና ታጋዮችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ጎን ለጎን ማካሄዱን ቀጠለበት። ማሰቃየትና መግደል የተጀመረው በዚሁ ወቅት ነበር። ህወሓት በአሁኑ ወቅት ከሚጠቀምባቸው

የዘር ማጣፍት ወንጄሎች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት፤
1ኛ፣ በየክልሉ በወያኔ ሰራዊትና ካድሬዎች ዜጎችን በግልጽ በመትረየስና በነብስ ወከፍ ጠመንጃ መጨፍጨፍ፣
2ኛ፣ ቤት ውስጥ አሰባስቦ በሩን በመዝጋት በእሳት ማጋየት፣
3ኛ፣ አፍኖ በመሰወር፣
4ኛ፣ ብርሃን እና ነፋስ በማይገባበት የጉድጓድ እስር ቤቶች ወስጥ በማጎርና በማጨናነቅ በተላላፊ በሽታ እንዲያልቁ ማድረግ። ዓይነ ስውር እንዲሆኑና አእምሮአቸውን በመሳት እንዲያብዱ ማድረግ፣
5ኛ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ወዘተ በመሆኑ ብቻ ያለምንም ፍርድ ወህኒ ቤት ተሰቃይቶ እንዲሞት ማድረግ፣ ከዘመድ አዝማድ በማራቅ በሌላ ክልል ወስዶ ማሰር፣
6ኛ፣ በዘጠኙ ክልሎች በወያኔ የተቋቋሙት እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ታሳሪዎች ሲታመሙ ህክምና ማግኘት ስለማይፈቀድላቸው፣ ብዙ ታሳሪዎች በዚህ ምክንያት በበሽታ እንዲያልቁ ማድረግ፣
7ኛ፣ በፈዋሽ መድሃኒት ስም ጽንስ የሚያሰውርድና የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት ዘር ማጥፋት፣
8ኛ፣ የህወሓት መሪዎች እንደትልቅ ፖሊሲ አድርገው የያዙት ድርጊት፣ ወጣት ሴቶችና ወንዶች ሃገር ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ ሃገሪቱን የወደፊት ተረካቢ በማሳጣት የሥልጣን ጊዜአቸው እንዲራዘም ማድረግ፣
9ኛ፣ መሬት ነጠቃ፣ ህወሓት (ወያነ) ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ፣ በእድገትና ሰላም ስም ሕዝቡን በግዴታ ከተወለደበትና ከሚኖርበት ቀየው እያፈናቀለ ለባእድ ሃገሮች ለምና ሰፋፊ መሬቶችን በርካሽ በሊዝ በመስጠት ኗሪውን
ህዝብ፣ ለረሃብ፣ ለችግርና ለስደት መዳረግ። ይህ ግፈኛና ፋሽስት መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸመውና በመፈጸም ላይ የሚገኘው ግፍ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም።

የኦሮሞ ህዝብ በፋሸስቱ ገዢ ህወሓት የደረሰበት ግፍና ሰቆቃ
የኦሮም ህዝብ ትልቁ የኢርዮጵያ ነገድ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ በሙሉ ልቡ የሚያምን እና የሚኮራ ዜጋ ነው። እናት ሃገሩን ኢትዮጵያን ከተለያዩ የጠላት ወራሪዎች በመከላከል ለብዙ ዘመናት ከኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመሰለፍ ደሙን ያፈሰሰና አጥንቱን የከሰከሰ ጀግና ህዝብ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ጠብቆ ለትውልድ ያስተለለፈ ህዝብ ነው። ልጆቹም በኢትዮጵያ በተለያዩ ወታደራዊ ክፍሎች ውስጥ፣ በውጭ ሃገር ከፍተኛ ትምህርት ተምረው፣ በአየር ሃይል፣ በምድር ጦር፣ በባህር ሃይል፣ በፖሊስ ወስጥ ተሰማርተው ሃገራቸውን ያገለገሉና የወገን ኩራትና አለኝታ የሆኑ ናቸው። ለአብነት ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፣ ጄነራል ጃገማ ኬሎ፣ ጄነራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ጄነራል ደምሴ ቡልቶ፣ ጄነራል ዋቅጅራ ሳርዳ፣ ጄነራል ገብረክርስቶስ ቡሊ፣ ጄነራል አስራት ብሩ፣ ጄነራል ቀልቤሳ ቤካ፣ ጄነራል አበበ ገመዳ የመሳሰሉትን ማንሳት ይበቃል። የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ የትመህርት መስክ ተሰማርተው በቀሰሙት እውቀትና ብቃት እናት ሃገራቸው ኢትዮጵያን ያገለገሉና በማገለጋል ላይ የሚገኙ ዜጎች ናቸው። የህወሓት መሪዎች ዛሬ የኦሮሞን ህዝብ ሽብርተኛ ብሎታል። ሽብርተኛው ግን ራሱ ህወሓት ነው። ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠር ከ1984 መጀመሪያ አንስቶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል በርካታ ጥቃት ፈጽሞበታል። ግድያ ፈጽሞበታል፣ ሰቆቃ በመፈጸም አፍኖ አጥፍቶታል፣ ከየሥራው አፈናቅሎታል፣ ወንድ ሴት ሳይለይ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩትን ወጣት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አባርሯል፣ በወታደርነት፣ በፖሊስ ወዘተ ተሰማርተው የሚያገለግሉትን የኦሮሞ ተወላጆች ከሥራ በማባረር ለችግር ዳርጓቸዋል፣ ከመሬቱ ተፈናቅሎ መሬቱን በእድገትና በልማት ስም ለውጭ ባእዳን አገሮች ሸጦበታል። ኢትዮጵያዊው የኦሮሞ ህዝብ አሁንም በህወሓት እየተሰቃየና እየተገደለ ነው። ህወሓት የኦሮሞ ህዝብ በሙሉ የኦነግ ደጋፊና አፍቃሪ ነው በማለት በተለያዩ ቦታዎች በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞና የሌሎች ነገድ ሰዎች የወያኔን እስር ቤቶች አጨናንቀውታል። እንዲሁም ማንም በማያውቃቸው ድብቅ ወህኒ ቤቶች፣ ማለትም፣ ገሃንነብ (ቃሌማ)፣ ፍየል ውሃ የመሳሰሉ፣ በወልቃይት ፀገዴ የሚገኙና ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ጥልቀት ባላቸው እስር ቤቶች በማጎር ያሰቃያቸዋል። በአጠቃላይ እስር ቤቶች በሞላ በኦሮሞ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ተጣበዋል። በወህኒ ቤቶች ካለፍርድና ፍትህ የሚማቅቀው የኦሮሞ ህዝብ ቁጥሩ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ እስር ቤት ያልገባውም ኦሮሞም የህወሓት እስራኛ ነው። አማራው ወያኔ ተሓህት/ህወሓት ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት ያቀደ ነው። ይህንንም በፕሮግራሙ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል። ተሓህት/ህወሓት ለውጭ ጠላት የሚውለውን ‘ጠላት’ የሚል ቋንቋ በአማራው ኢትዮጵያዊ ላይ መጠቀሙ የሃገርና የወገን ከሃዲዎች መሆናቸውን በግልጽ ያመለክታል። ወያኔ ተሓህት/ህወሓት አማራው ጠላቴ ነው በማለት ዘሩን ለማጥፋት የተነሳው ከ1969 ጀምሮ ሲሆን፣ አሁንም በአማራው ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት እየፈጸመበት ይገኛል።
1. ተስፋፊው ህወሓት በ1967 ይዞት ወደ ደደቢት በረሃ በወረደው ፕሮግራሙ ላይ፣ ሰሜን በጌምድርን በሙሉ፣ ወልቃይት ፀገዴን፣ ሁመራን፣ ፀለምትን ወደ ትግራይ ለማቀላቀል መሬቱ ከአማራ መጽዳት አለበት በማለት በታህሳስ 1972 ገልጾታል። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት፣ በሰሜን በጌምድር ጾታን ሳይለይ፣ ከህጻናት እስከ ሽማግሌ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል። እቤት ወስጥ እየታጎሩ በእሳት ጋይተዋል። ወያኔ ህወሓት በተለያየ ዘዴ አማራ የተባለውን እያደነ የዘር ማጥፋት ድርጊት ፈጽሞበታል። ነፍሳቸውን ያተረፉት ለስደት ሲዳረጉ፣ የቀሩት ጥቂቶቹ ደግሞ ከቤት ንብርታቸው እንዳይፈናቀሉ በመፍራት የሚደርስባቸውን ስቃይ እየተቀበሉ እየኖሩ ነው።
2. ወያኔ ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠረ ‘ለ’ ተብሎ እንደተምለከው ካርታ አይነት በማዘጋጀት ሆን ብሎ አማራውን በዘዴ ለማጥፋት ያቀደ ክልል የሚል ስምና ካርታ አዘጋጅቶ አማራውን በዚሁ አጠፋዋለሁ በማለት። ይህንንም ለማሳካት ከበጌምድር፣ ከወሎ፣ ከጎጃም ለም መሬቶችን እየመረጠ ወደ ትግራይ አካሏል። በነዚህ ለም መረቶች ላይ ሲኖር የነበረው የአማራው ህዝብ አብዛኛው ተገድሏል፤ ቀሪውም ተሰዷል። ያማራው ሕዝብ በቀጥታና ዘዴ በተላበሰ መንገድ በወያኔ ህወሓት የግፍ እልቂት ተፈጽሞበታል። አለመታደል ሆነ እንጂ አማራ እኮ የኢትዮጵያ ጋሻ መታ ነው። ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ከወራሪ ጠላት እየተከላከል የመጣ ባለታሪክ ህዝብ
ነው። ወደ ሌላ ሃሳብ ከመግባታችን በፊት፣ ኢትዮጵያውያን በብሄር ብሄረሰቦች በመተባበር ለረጅም ዘመናት አብሮ የኖረና በዳበረ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ትስስር የቆየ ህዝብ ነው። አሁንም ወያኔ የሚፈልገውን መንገድ አንከተልም በማለት የተጠናከረ ህብረት ፈጥሮ በሙሉ ልቦና እና ኢትዮጵያዊነት ተሰባስበው እየተራመዱ ነው። እምቢ ለወያኔ አልገዛም እምቢ ለወያኔ የእድሜ መግዣ አልሆንም አማራ ነኝ አማራነቴም የሚነጥቀኝ ሀይል የለም ።የመብት ገዴታየም በህዝባዊ አመፅ አከብራሉ የኦሮሞ ህዝብም እንደዚሁ ፡ሌላው ኢትዮጵያዊ ህዝብም እንደዚሁ ተነስተዋ ግለቱ እየጨመረ ።የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት ስርአት በዚች አመት ከርሰ መቃብሩ መግባቱ እይቀሬ ነው።ህዝብ ሀያል ነው፤ህዝብ ከተነሳ የሚመልሰው ሀይል በዚች አለም የለም።የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን የትቀጣጠለው ህዝባዊ አመፅ ሀገር አቀፍ ሆኖ ዳሩን እናድርስው ነፃነታች እናስመልስ ። ህ.ወ.ሓ.ት የመሰለ ክፉ ጠለት የለም።

ጋሜቤላ

የጋምቤላ ኢትዮጵያዊ ዜጋም ልክ በአማራውና በኦሮሞው ህዝብ ላይ የሚደርሰው ዓይነት ሰቆቃ፣ እስራት፣ ግድያ፣ አፈና በወያኔ ህወሓት እየተፈጸመበት ዘሩ እንዲጠፋ እየተደረገ ነው። በአማራው ላይ የተፈጸመው በመድሃኒት ስም በግድ ለወንዶችና ለሴቶች የሚሰጠው የማምከኛ መድሃኒትም ለጋምምቤላ ሕዝብ እየተሰጠ ዘሩ እየጠፋ ነው። በህወሓት የሚመራው ሽብርተኛ ስርዓት በጋምቤላው አኝዋክ ህዝብ ላይ በጄነራል ጸጋዬ የሚመራው 43ኛው ክፍለ ጦር በቀን ከ425 በላይ ገበሬዎችን፣ ሴቶችን እና ህጻናትን ገድሏል፣ ቤታቸው ተቃጥሏል፣ የተረፈውም ተሰዷል። ይህ ሳይበቃው፣ የህወሓት ሽበርተኛ ስርዓት የጋምቤላ ህዝብ በእርሻ ላይ ተሰማርቶ የሚኖረውን ገበሬ የሚጠቀምበትን መሬት
ለባእዳን ባለሃብቶች በመስጠት ለችግርና መከራ ዳርጓቸዋል። ዛሬ፣ የጋምቤላ ህዝብ በደረሰበት የዘር ማጥፋት ምክንያት ህልውናው የተመናመነ ሆኗል።

ኦጋዴን

ወያኔው የህወሃት ፋሽስት መሪዎች በኦጋዴን ህዝብ ላይም ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጄል ፈጽመዋል። ይህ ኢትዮጵያዊው ህዝብ የኦነግ አባል ነህ በሚል ሰንካላ ምክንያት በቀን እና በሌሊት እያደነ መጠን የሌለው ግድያ በመፈጸም ዘሩን አጥፍቷል። እቤት ውስጥ አሰባስቦ ቤቱን በመቆለፍ በህይወት እያሉ በላያቸው ላይ እሳት በመለኮስ በእሳት ጋይተው እንዲሞቱ አድርጓል። በሌላው ዘር ላይ እንደተፈጸመው አይነትም ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉና እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል። አስገድዶ የማምከኛ መርፌና ኪኒን በመስጠት ዘሩ እንዲጠፋ አድርጓል። በየቦታው በማይታወቁና በሚታወቁ የወያኔ ህወሓት ወህኒ ቤቶች በበሽታ፣ በረሃብ ቤተሰባቸው በማያውቀበት ሁኔታ ታስሮ ዘሩ እያለቀ ነው። አፋር የአፋር ኢትዮጵያዊው ዜጋም ከላይ በተጠቀሰው ዓይነት በህወሓት የዘር ማጥፋት ደርሶባታል። ከመሬቱ ተፈናቅሎ በገዛ ሃገረ ሰደታኛና ባይተዋር ተደርጓል። ትግራይ የትግራይ ህዝብ ገና ወያኔ ሲፈጠር ይዞት የመጣውን ፕሮግራም አልቀበልም በማለት፣ አማራው ደመኛ ጠላትህ ነው ሲባል፣ አማራው ወንድሜና እህቴ፣ ደሜና ስጋዬ ነው፣ አማራው ለትግራይ ህዝብ ጠላት አይደለም፣ እናንተ የወያኔ መሪዎች የምታወሩትና ከወገናችን ለማቃረን የሸረባችሁት ዘዴ ነው እንጂ፣ ሁለቱ ህዝቦች ለብዙ ዘመን በፍቅር፣ በሰላም ተጋብቶና በደም ተቆራኝቶ የኖረ ህዝብ ነው። አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ሳይሆን ወንድምና እህት እንዲሁም ወገንና መመኪያ ነው። ትግራይ የኢትዮጵያ አካል እንጂ ነፃ ሃገር ነበረች የምትሉትን ተረታችሁን አንቀበለውም በማለቱ ከባድ መሰዋእትነት የከፈለ፣ ወገኔን አትንኩ በማለቱ “የትግራይ ሸዋ” የተባለ ህዝብ ነው። በዚህም ምክንያት በወያኔ ተሓህት/ህወሓት ከፍተኛ ጥቃት ደርሶባታል፣ ተገድሏል፣ ንበርቱ ተወርሶ ለከፋ ችግር ተዳርጓል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለደረሰው ለዚህ ሁሉ ጥቃት ተጠያቂዎቹ እነማን ናቸው? በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጄል በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላው፣ በኦጋዴኑ፣ በአፋሩ፣ ወዘተ ላይ ተፈጽሟል። ከተወለደበት ካደገበት መሬት ተፈናቅሏል፤ በመድሃኒት አንዳይዋለዱና እንዳይባዙ ተደርገዋል፣ ንጹሃን ወገኖች በጅምላ ተገድለዋል፤ እንዚህ ሁሉ ከዘር ማጥፋት ድርጊት ያላነሱ ተግባሮች ናቸው። እስከ አሁን በወያኔ ህወሓት አመራር የተገደለው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከ9 ሚሊዮን በላይ እንደደረሰና ቁጥሩ በማደግ ላይ እንድሆነ ጥቆምዎች ያመለክታሉ። ከ34 ሚሊዮን በላይ ደግሞ ከመሬታቸውና ከትውልድ ቦታቸው ተፈናቅለው መኖሪያ አልባ በመሆን ለስደት፣ ለረሃብ፣ ለበሽታና ለሞት፣ ተዳርገዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ነው። በእኩይ ታግባራቸው ታሪክ ሊረሳቸውና ሊፋረዳቸው የሚገባቸውን እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ፤መለስ ዜናዊ፣ ቢሞትም የሰራው የወንጄል ድርጊት ተጠያቂ ያደርገዋል፣ አዜብ መስፈን፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፈን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ገብሩ አስራት፣ ፃድቃን ገብረተንሳይ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ ሳሞራ የኑስ፣ ሃየሎም አርአያ፣ ብስራት አማረ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋይ በርሄ፣ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ አባዲ ዘሞ፣ አረጋሽ አዳነ፣ ተወልደ ወ/ማርያን፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ ገብረአብ ባርኖባስ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ የማነ ኪዳነ ጃማይካ፣ ብርሃን ገብረክርስቶስ፣ ሙሉጌታ አለምሰገድ፣ ቢተው በላይ፣ አባይ ወልዱ፣ በየነ ምክሩ፣ አዲስዓለም ባሌማ፣ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ታደሰ መሰረት በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በነዚህ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት። በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊፋረዳቸው የሚገቡ፤
– ከ1967 ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው የማ/ኪሚቴ አባላት በሙሉ፣
– ከላይ እስከታች ያሉት የደህንነት አባላት፣
– በማእካላዊ ወህኒ ቤት ያገለገሉና የሚያገለግሉ በሙሉ፣
– የህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በሙሉ፣
– በዘራቸው ምክንያት የተሾሙት የህወሓት ጄነራሎች በሙሉ።
-የብአዴን ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣
ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ በረከት ስምኦን፣ አየለ ጎበዜ፣ ዓለምነው መኮንን፣ ብናልፍ አንዱዓለም፣ አህመድ አብተው፣ ተፈራ ደርቤው፣ አምባቸው መኮንን፣ በተጨማሪም የማ/ኮሚቴው አባላት በሙሉ። የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሶፍያን መሃመድ፣ በዙ ዋቅቢያካ፣ አስቴር ማሞ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሙክታር ከዲር፣ ዲሪባ ኩማ፣ አከይል አዚዝ መሃመድ፣ ኡመር ሁሴን፣ አለማየሁ ቶምሳ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ግርማ ብሩ፣ እነዚህና ጠቅላላው የማ/ኮሚቴው።

የደቡብ ህዝብ ሥራ አስፈጻሚ የነበሩና የሆኑ፣
ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ መኩሪያ ሃይሉ፣ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ሽፈራው ተ/ሃይማኖት፣ አለመየሁ አሰፋ፣ ደሴ ዳልከ፣ እነዚህና ጠቅላላው የማ/ኮሚቴው። ከላይ ከተጠቀሱት ባልተናነሰ ሁኔታ በዘር ማጥፋት መጠየቅ ያለባቸው፤ የትግራይ ክልል፣ የአማራ ክልል፣ የአፋር ክልል፣ የሶማሊ ክልል፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የሃረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአዲስ አባባ አስተዳደር፣ የድሬደዋ አስተዳደርም ተጠያቂዎች ናቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የቅጥረኛ ቅጥረኛ ሆነው በማገልገል፤ የህወሓት ተባባሪ በመሆን የኢትዮጵያን ሉአላዊንት አፍርሰዋል፤ በዘር ማጥፋት ድርጊት ተካፋይ ሆነዋል፣ ኢትዮጵያውያንን ከመሬታቸው በማፈናቀልና በመግደል እንዲሁም ንብረታቸውን
በመንጠቅ ከፍተኛ ግፍ ፈጽመዋል፤ ከወያኔ በመተባባር የማምከኛ መድሃኒት እየወጉ ዘር በማጥፋት ድርጊት ተሰማርተዋል፤ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን መንግሥት እንዲሸጥ በማድረግ ተባብረዋል፤ በየክልላቸው ድብቅ እስርቤቶችን በመሥራት ተቃዋሚዎችን እና ንጹሃን ዜጎችን ያለፍርድ አስረዋል፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ስብአዊ መብቱን በመንፈግ ለግፍና መከራ ዳርገውታል። ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!! ከትግራይ የመጣውና አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ፋሺስቱ ህወሓት ሃገራችንን ተቆጣጥሮ በቅኝ ግዛት መዳፍ ውስጥ ካደረጋት እነሆ ዛሬ 24 ዓመታት አልፈዋል። በነዚህ ዓምታት ውስጥ ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ሃገር ሆናለች፣ ለም መሬቷ ከሁመራ እስከ ሞያሌ ያለው የድንበር ሃገራችን ለሱዳን በምልጃ ለወያኔ ጥቅም እየተሰጠ ነው፣ ህዝብ ሊፈናቀል ነው፣ ከሃገሩ ከተወለደበት ካደገበት ተፈናቅሎ የት ሊገባ ነው? ይህ የአማራ ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጋ የሚመለከት ነው፣ የኢትዮጵያ ዜጋ በሙሉ ካለአንዳች ልዩነት በአንድነት በመነሳት የሚፈለገውን የህይወት መስዋእትነት ከፍሎ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችንን የመሬት ወረራ እናድን። ታሪካዊ መሬት፣ ለም መሬት አሳልፈን ለሱዳን ወራሪ መንግስት በወያኔ የባንዳ ስርአት ኢትዮጵያ በሱዳን አትወረርም። በየቦታው ያሉት ለም መሬቶች ለባእዳን ሃገሮች እየተቸበቸቡ ነው፣ በዚህም ምክንያት የሃገራችን ህዝብ መሬትና ሃገር አልባ በመሆን፣ ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለበሽታና ለሞት ተዳርጓል፣ ግፉና በደሉ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ስለዚህ፣ ረሃብና በሽታ በየጊዜው እየተፈራረቁብህ እስከመቼ በባርነት ትኖራልህ? ነፃነትህ ያለችው በእጅህ ላይ ስለሆች እምቢ ለወያኔ፣ አሁንስ በቃኝ ብለህ ተነሳ፣ አሁን የተጀመረውን ህዝባዊ አመጽ በሀይልና በግለት አጠናክር። የህዝብን ቁጣ ምንም ዓይነት ሃይል ስለማይቋቋመው ሆ ብለህ በመነሳት ሃይልህን በማሳየት ሃገራችን ኢትዮጵያን ነፃ አውጣ። የወያኔ ባርነት፣ ግድያ፣ ረሃብ፤ ስደትና ተመጽዋችነት ይብቃህ። ከኢትዮጵያዊ ዜግነትህ አልባ ሆነህ የባንዳ ልጆችና ባንዳዎች አገርህን እየዘረፉ፣ የኢትዮጵያን ሉእላዊነት እያፈረሱና እየሸጡ እያየህ እስከመቸ ነው ዝምታው? አሁንስ በቃ። ፋⶥሽቱን ወያኔ የተዘረጋውን ክንዳችንን አናሳርፍበት።

ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነው
ፐርዝ፣ አውስትራሊያ
ታህሳስ 2008 (ዲሴምበር 2015)

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

  • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending