Connect with us

Articles

‹‹መፍትሔው አሠልጣኝን ማባረር ሳይሆን ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት መቻል ነው››

Published

on

23ebad3ea3f6bf5cb16d8b8767ae7f7b_XL

09 FEBRUARY 2014 | በ ተጻፈ

አቶ ሰውነት ቢሻው፣ የቀድሞው ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ

አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ‹‹ሰውነት›› ሆነውት ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል በአስገራሚና በአነጋጋሪ ጉዞ ዋሊያዎቹን መርተዋል፡፡

ከቡድኑ ያልተጠበቁ ቁም ነገሮችም ተገኝተዋል፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በጀመረው መንገድ መቀጠል ያልቻለው የዋሊያዎቹ ስብስብ የጀመረውን የውጤት መንገድ መሳትና ጅማሬው ላይ እንደነበረው ላለመቀጠሉ ምክንያት ከተደረጉት መካከል፣ በአቶ ሰውነት የሚመራው የአሠልጣኞች ቡድን ተጠያቂ ሆኖ እንዲሰናበት መደረጉ ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው ረቡዕ በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ሆኗል፡፡ ስንብቱን ተከትሎ ነገሮች ግን በተቋማዊ ማንነት ላይ ከማተኮር ይልቅ ወደ ግለሰቦች ማነጣጠር ጀምረዋል፡፡ ግልጽ ለማድረግ የአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስንብት ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው እየተባለ ከአገር ውስጥ አልፎ በውጭ የስፖርት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር ሲነገር ተደምጧል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ፣ ለአሠልጣኝ ሰውነትና ረዳቶቻቸው ስንብቱን ያደረገው ተገቢውን ግምገማ ካካሄደ በኋላ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይባስ ብሎም ‹‹በቻን ውድድር ዋንጫ እናመጣለን ግን ስንት ብር እንደምንሸለም ንገሩን›› በማለት ዋሊያዎቹ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ጭምር የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡ ያም ሆኖ በተቋሙ አሠራርና እግር ኳሱ በሚመራበት ደካማና ጠንካራ ጐን ላይ መነጋገር፣ መተቻቸትና መነቃቀፍ ሲገባ አቅጣጫውን ስቶ ወደ ግለሰቦች ሰብዕና ማዘንበሉ መነጋገሪያ መሆን ጀምሯል፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻው፣ በተለይም የእሳቸው ስንብት ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው ስለሚባለውና በሌሎችም ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ባለፈው ዓርብ ከደረጀ ጠገናው ጋር ባደረጉት የአፍታ ቆይታ የሚከተለውን ብለዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ከአሠልጣኝነትዎ መነሳትዎን ተከትሎ የተለያዩ የውጭ የመገናኛ ብዙኃን ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት እያስነበቡ ናቸው፡፡ ጐል ዶት ኮምና ሌሎችም ዘገባዎች አሠልጣኝ ሰውነት ከኃላፊነት እንዲነሱ ምክንያት የሆናቸው በተለያዩ ጊዜያት በሚሰጡዋቸው መግለጫዎች የተቋሙንና በአጠቃላይ በአገሪቱ ያለውን ደካማ የስፖርት መሠረተ ልማት ስለሚተቹ ነው ይላሉ፡፡ የሚሉት ይኖርዎታል?

አቶ ሰውነት፡– ይኼን አላውቅም፣ ሲጀመርም እኔ የእግር ኳስ አሠልጣኝ እንጂ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ ለስንብቴም በዚህ መስመር የመጣ ውሳኔ ነው የሚል አንዳችም ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ሊሆንም እንደማይችል ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ምክንያቱም የማውቀው ኳስና ኳስን ብቻ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለስንብትዎ ምክንያት የሚሉት ሌላ ተጨማሪ ነገር ይኖራል የሚል እምነት አለዎት?

አቶ ሰውነት፡- ተሰናብተሃል ከሚለው የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ውጪ የተለየ ምክንያት ስለሚባለው ነገር ደግሜ ደጋግሜ ላረጋግጥልህ የምችለው ምንም ነገር አለመኖሩን ነው፡፡ እዚህ ላይ ሌላ የምጨምረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለምን አሰናበተኝም የሚል መከራከሪያ የለኝም፡፡ አንድ እንድታውቅ የምፈልገው እግር ኳሱ መመራት ያለበት በሙያተኞችና በሙያተኞች ብቻ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ፌዴሬሽኑ በሙያተኞች እየተመራ አይደለም ብለው ያምናሉ?

አቶ ሰውነት፡- ይኼን ለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? ምክንያቱም ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው የብሔራዊ ቡድኑ ግምገማ ወቅት በግልጽ የተነገረ አይደለም እንዴ?

ሪፖርተር፡- በእርስዎ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ወደ ደቡብ አፍሪካ ከማምራቱ በፊት ዋንጫውን ይዞ እንደሚመጣ፣ ይህንኑ መነሻ ያደረጉት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ዋንጫ ማግኘት ካልሆነ ደግሞ ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃ ያለውን ይዞ ለማጠናቀቅ ዕቅድ እንደነበራቸው ተነግሯል፡፡ እርስዎና ተጨዋቾቹ ደግሞ ‘ዋንጫ እናመጣለን፣ ነገር ግን ከዚያ በፊት እኛ ዋንጫ ብናመጣ ፌዴሬሽኑ ምን ያህል የገንዘብ ሽልማት ይሰጠናል?’ የሚል የመደራደሪያ ቅድመ ሁኔታ ማቅረባችሁም ተሰምቷል፡፡

አቶ ሰውነት፡– ብሔራዊ ቡድን ቀርቶ የትኛውም ሰው የዕለት ተዕለት ክንውኑን ለማስፈጸም ዕቅድ ይኖረዋል፡፡ ዕቅድ ለምን ታቀደ ብሎ ነገር የለም፣ ማቀድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በእግር ኳስ እንደ ፋብሪካ የተጠየቀው ሁሉ መቶ በመቶ ይሳካል ማለት አይቻልም፡፡ ፋብሪካ እንኳ በመብራትና በመሳሰሉት ምክንያቶች ያቀደውን ያህል ምርት የማያገኝበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ እግር ኳስ ደግሞ ከእነዚህ ሁሉ ወጣ ያለ የራሱ መገለጫዎች ያሉት የሙያ ዘርፍ ነው፡፡ በእግር ኳስ ማሸነፍ፣ እኩል መውጣትና መሸነፍ የግድ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች መኖራቸው እየታወቀ ግን ‹‹እሸነፋለሁ›› ብሎ የሚያቅድ የለም፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰላማዊ ጦርነት ውስጥ የሚሆነውን ለመተንበይ ከባድ ነውና፡፡ ውጤትና ውድቀት የግድ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ማንም በሙያው የሚኖር ሰው የምሄደው ዋንጫ እወስዳለሁ ብሎ እንጂ እሸነፋለሁ ብሎ እንዳልሆነም ሊታወቅ ይገባል፡፡ እኔም የተከተልኩት ይህንኑ መንገድ ነው፡፡ ዋንጫ ለማግኘት ነው ብሎ መናገር ሌላው ጥቅሙ ደግሞ ዋንጫ ይዞ ለመምጣት ተብሎ ሳይሆን የተጨዋቾችን ሥነ ልቦና ለመገንባትም ተብሎ ነው፡፡ በውስጤ ያለውን ነገር ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ የምነግረው ለቻን ቀርቶ ለማንኛውም ውድድር ዝግጅት የማደርገው ለዋንጫና ዋንጫ ብቻ መሆኑን እንዲያውቅ ነው፡፡ በዚህ አባባሌ ዛሬ አይደለም ወደፊትም እንደማላፍር ቅንጣት ታህል አልጠራጠርም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ አመራሮች ለቻን ዝግጅት እያደረግን ባለንበት ወቅት መጥተው አነጋግረውናል፡፡ እደግመዋለሁ የምሄደው ዋንጫ ለማምጣት ነው ብዬ ነው የመለስኩላቸው፡፡ ተጨዋቾቹም ይህንኑ ነው ያረጋገጡት፡፡

ሪፖርተር፡- ለቅድመ መደራደሪያነት የተቀመጠውን የገንዘብ ሽልማት በተመለከተ አልመለሱልኝም እኮ?

አቶ ሰውነት፡- እንሸለማለን ወይ ብሎ መጠየቅ በየትም አገር የተለመአ ነው፡፡ ስለዚህ መጠየቅ ምን ነውር አለው?

ሪፖርተር፡- ያወሩት ሌላ የሆነው ደግሞ በተቃራኒው ነውና ዛሬስ ምን ይላሉ? 

ሰውነት፡– ከቻን ውድድር ከምድብ ድልድል መውጣት ድክመትን ብቻ የሚያመላክት ሊሆን አይችልም፡፡ ለምን ለሚለው ተያይዘው መነሳት ያለባቸው በርካታ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ማለት ነው፡፡ እነዚያን ነገሮች በዚህ ወቅት አንስቶ ለመከራከር ጊዜው ስላልሆነ አልፈዋለሁ፡፡ ከዚሁ ጋር ሌላው ልንመለከተው የሚገባን፣ ሁሉም እንዳስተዋለውና እንደተከታተለው የቻንን ዋንጫ የወሰደው የሊቢያ ቡድን ነው፡፡ ሊቢያ ግን እ.ኤ.አ. ለ2015 የአፍሪካ ዋንጫ እንደ ኢትዮጵያ ቡድን ቀጥታ ምድብ ድልድል ሳይሆን የገባው የማጣሪያ ማጣርያ አድርጐ ወደ ምድብ ድልድሉ እንዲመጣ ነው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የወሰነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋንጫ ስላላገኘ ወደ ማጣሪያ ማጣሪያ እንዲገባ አልተደረገም፡፡ ምክንያቱም ዋንጫ ማግኘት አንድ ነገር ሆኖ፣ ነገር ግን ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ መሥፈርቶች መኖራቸውን እንረዳለን፡፡ እኛ ግን መሥፈርቶቻችን ዋንጫና ዋንጫ ብቻ ሆነው ብዙ ነገር እየተባለ ነው፡፡ ያውም ከቡድናችን ጀርባ ያለው እውነተኛ መገለጫ ሳይታይ ማለት ነው፡፡ የምናገረው ሳይቆራረጥ እንዲወጣ እፈልጋለሁ፡፡ ዋንጫና ደረጃ ውስጥ አልገባም ተብሎ የሚተቸው የሰውነት ቡድን ከአፍሪካ ምርጥ ሦስት ቡድኖች አንዱ ተደርጐ ተመርጧል፡፡ ካፍ 21 አገሮች ከማጣርያ ማጣርያ ውጪ እንዲሆኑና ቀጥታ ወደ ምድብ ድልድሉ እንዲገቡ ሲወስን፣ የኢትዮጵያ ቡድን በ12 ድምፅ 16ኛ ደረጃ አግኝቶ ነው ወደ ምድብ ድልድሉ የተካተተው፡፡ ይኼ የሆነው ሰውነትን ለመደገፍ ተብሎ አይደለም፣ እውነታው ነው፡፡ ይኼ የሚይሳየው እንደሚባለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ መውደቁን ነውን? በግሌ አይመስለኝም፡፡

ሪፖርተር፡- ቡድንዎ ከውድድር መውጣቱ ብቻ ሳይሆን ጐል ማስቆጠር እንኳ እንዳልቻለ ታይቷል፣ እየተተቸም ነው፡፡ 

አቶ ሰውነት፡- በውድድር ዓለም ያጋጥማል፡፡ ይኼ ታላላቅ የእግር ኳስ አገሮችን ሳይቀር የገጠመ ነው፡፡ ፈረንሳይ እ.ኤ.አ. በ2010 የዓለም ዋንጫ ለድል ከተጠበቁት አንዷ ሆና፣ ነገር ግን ከምድብ ድልድሉ እንኳ ማለፍ ተስኗት የተባረረችበት ሁኔታ ነበር፡፡ የሩቁን ትተን የእግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለፈው ዓመት አሸናፊ ማንቸስተር ዩናይትድ ዘንድሮ የሚገኝበትን ደረጃ መመልከት በቂ ነው፡፡ ይኼ ሁሉ ሽንፈት እየደረሰበት አሠልጣኝ ዴቪድ ሞይስ አልተባረሩም፣ እየሠሩ ናቸው፡፡ ምክንያት ከተባለ አብሮ መታየት ያለባቸው ነገሮች ስለሚኖሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ስንብቱ ተገቢ አይደለም እያሉ ነው?

አቶ ሰውነት፡– አልወጣኝም፣ እኔ ተባርሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማደግና የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ ከቻለ ስንብቱን በፀጋ የምቀበለው መሆኑን ደግሜ ደጋግሜ የምናገረው ነው የሚሆነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር ሲቀጥረኝ፣ ስምምነታችን ብሔራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ እንዳበቃ ነው፡፡ ያንን ደግሞ አሳክቻለሁ፡፡ ከዚህ ባለፈ የቻንን ዋንጫ በሚመለከት አልተነጋገርንም፣ ይኼ ለእኔ ቦነስ ነው፡፡ ሌላው ባለፈው ቅዳሜ በኢሊሌ ሆቴል በተደረገው የብሔራዊ ቡድኑ ግምገማ ላይ አሠልጣኝ ሰውነት በቻን ውድድር ላይ ዋንጫ ስላላመጣ መባረር አለበት የሚል ግምገማ አልቀረበም፡፡ ግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረገው የፌዴሬሽኑ አጠቃላይ አደረጃጀት፣ ጽሕፈት ቤቱና ቴክኒክና ልማቱ ላይ ያለው ድክመት ላይ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የፌዴሬሽኑ አመራሮች ለስንብትዎ ከጠቀሱዋቸው ምክንያቶች አንዱ፣ በግምገማው ወቅት በእርስዎ ላይ የቀረበውን ትችት መሠረት አድርገው መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ 

አቶ ሰውነት፡- እኔም እየነገርኩህ ያለው በግምገማው ላይ የተነሳውን ተጨባጩንና እውነታውን ነው፡፡ ስናገርም ለምን ተሰናበትኩ እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን ስሰናበትና እኔን ጠርተው ሲያነጋግሩኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አሁን ከሚገኝበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ስለምንፈልግ፣ ለዚያ ደግሞ ጠንካራና ከፍ ያለ ደረጃ ያለው አሠልጣኝ ማምጣት እንፈልጋለን ምን ይመስልሃል ቢሉኝ፣ ውሳኔውን የምቀበለው በደስታ ነበር፡፡ ምክንያቱም የተባለው አሠልጣኝ ቢመጣ የአገሪቱ ወጣት አሠልጣኞች ጭምር ትምህርት ስለሚያገኙበት ማለት ነው፡፡ እውነትም ዓላማው ለዚህም ቢሆን ከተቋሙ ውሳኔ በፊት በክብር መሰናበት እንደሚገባኝ እኔ ራሴ ነበርኩ መልቀቅ እንደሚገባኝ የምጠይቀው፡፡

ሪፖርተር፡- ንግግርዎ አሁንም በፌዴሬሽኑ የስንብት ውሳኔ ደስተኛ እንዳልሆኑ ያመላክታል፡፡

አቶ ሰውነት፡– መጡ አስወጡኝ፡፡ ከዚያ ውጪ መናገር ካለብኝ ይኼ አሁን ያለው አመራር ስለ ቻን ውድድር ምንም የሚይውቀው ነገር የለም፡፡ ሲጀመር ቡድኑን ለዚህ ሻምፒዮና እንዲበቃ ትልቁን ሚና የተጫወተው የቀድሞው አመራር ነው፡፡ ክብሩም ሆነ ትችቱ የሚገባው ለቀድሞው ነው፡፡ ስለተላለፈብኝ ውሳኔ ከሆነ ጥሩ ነው እቀበለዋለሁ፡፡ ምክንያቱም አዳዲሶቹ አመራሮች ሲናገሩ እንደሚደመጡት ከሆነ ተቋሙ አዳዲስ አሠራሮችና አደረጃጀቶች ስለሚያስፈልጉት የግድ ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግ አለብን ነው፡፡ ደስ እያለኝ ነው ይህንንም የምቀበለው፡፡ በግምገማው ፌዴሬሽኑ አሁን ባለበት የትም መድረስ እንደማይችል ነው በአብዛኛው ሲያሳስብ የተደመጠው፡፡ እውነት ሆኖ መመልከት ደግሞ ሌላው የምጠብቀው መሆኑ እንደተጠበቀ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የተደረገው ለለውጥና ለጥሩ ነገር ነው ተብሎ ስለሚታመን እኔም ስንብቱን የምቀበለው በፀጋ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የእርስዎና የረዳትዎችዎ ስንብት ብቻውን መፍትሔ እንደማያመጣ የሚናገሩ አሉ፡፡

አቶ ሰውነት፡- ትልቁና መነሳት ያለበት እኔም መናገር ካለብኝ መናገር የምፈልገው እዚህ ላይ ነው፡፡ የምናወራው ስለ እግር ኳስ ነው፡፡ እግር ኳስ ደግሞ ሙያ ነው፡፡ ይህ ሙያዊ ተቋም ደግሞ መመራትና መተዳደር ካለበት በሙያተኞችና በሙያተኞች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ውጪ አሠልጣኝ ማባረር ብቻውን መፍትሔ አይሆንም፡፡ መፍትሔው ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት መቻል ነው፡፡ ይኼ የተቋሙ መሪዎችና አስተዳዳሪዎችን ጭምር ይመለከታል፡፡ ለዚህ በርካታ ምሳሌዎች ለማንሳት እገደዳለሁ፡፡ አንድ ወታደራዊ ተቋም በአንድ የምህንድስና ሙያ ባለው ሰው አይመራም፡፡ አንድ ተዋጊ የጦር አውሮፕላን የሚያበርን ሙያተኛ አንድ የእግር ኳስ አሠልጣኝ ሊመራው አይችልም፡፡ እግር ኳሱም እንደዚያው ነው፡፡ ይኼ ጥሬ እውነት እስካልገባን ድረስ የምንፈልገው ለውጥ ከወዴትም አይመጣም፡፡ ማሰናበቱና መቅጠሩ ግን ይቀጥል ይሆናል፡፡ እግር ኳስ ኳሱን ጠንቅቀው በሚያውቁ ሙያተኞች መመራት መቻል ይኖርበታል፡፡

ሪፖርተር፡- ውሳኔው ከሙያው አኳያ አይመጥነኝም እያሉ ነው?

አቶ ሰውነት፡- እስከዛሬ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ለማሠልጠን ከአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ በርካታ አሠልጣኞች ተሞክረዋል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሠልጣኞችም ሆኑ የውጭ አሠልጣኞች መጥተው ተሰናብተዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ሙያተኛ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ይዘው ለአፍሪካ ዋንጫ ያበቁ ግን ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ እነሱም መንግሥቱ ወርቁና ሰውነት ቢሻው ናቸው፡፡ ይኼን የምለው ስለተሰናበትኩ አይደለም፣ ቅር የሚለው ካለ በማስረጃ መነጋገርም ይቻላል፡፡ የእግር ኳሱ ቤተሰብ ለውጥ ለውጥ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ተቋሙ በሙያተኞችና በሙያተኞች ብቻ እንዲመራ ካላደረግን ለውጡም ጩኸት ሆኖ ይቀራል፣ ተቋሙም እንደዚሁ፡፡ ተወደደም ተጠላ ለአገሪቱ እግር ኳስ መሠረቱ ላይ መሠራት አለበት፡፡ ኅብረተሰቡ ተተኪ ተተኪ እያለ ለሚናገረው መልስ የሚሆነው ከእኔ ጀምሮ ይመለከተናል የምንል የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዘን መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጪ አሁን ባለው የሰውነትንም ሆነ የሚመጣውን የአሠልጣኞች ስብስብ በማሰናበትና በመሾም ለውጥ አይታሰብም፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ እርስዎ ስንብትና ግምገማ እንመለስና እንዴት አገኙት? ምክንያቱም ፌዴሬሽኑ በሙያተኞች መመራት እንዳለበት ሁሉ፣ እግር ኳሳዊ ግምገማም መደረግ ካለበት በሙያተኞች ሊሆን እንደሚገባ ደጋግመው አንስተዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የበቀደሙ 

ግምገማ በእርስዎ አተያይ ትክክለኛ ነው ብለው ያምናሉ?

አቶ ሰውነት፡- ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ከእኔም በላይ አሁን እየጠየቅከኝ ያለኸውም ሆነ ሌሎች የሚዲያ ተቋማት ሁሉ እንደተከታተላችሁት የግምገማ መድረክ ለመሆኑ እምነት አለኝ፡፡ የግምገማው አካሄድ ተሳታፊዎች በሲንድኬት (በቡድን) ተከፋፍለው እያንዳንዱ በብሔራዊ ቡድኑ የቻን ተሳትፎም ሆነ በሌሎች አስተዳደራዊና ቴክኒካዊ ክፍተቶች ላይ የሚመስለውንና ያመነበትን ብሏል፡፡ በዋናነት ግን ለአገሪቱ እግር ኳስ ዕድገት ማነቆ ተደርጐ በሁሉም የቡድን ተወካዮች እንደ ድክመትና ክፍተት ተደርጐ ሲነገር የተደመጠው፣ የተቋሙ ጽሕፈት ቤትና ቴክኒክና ልማቱ ላይ የተሠራ ሥራ እንዳልነበረ ነው፡፡ ሰውነት ዋሽቶ ከሆነ የግምገማውን ፊልም መመልከት ይቻላል፡፡ በዕለቱ የተገኙት የስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አንበሳው እንየው ሳይቀር አስረግጠው ሲናገሩ የተደመጠው፣ ፌዴሬሽኑ በተደበላለቀ አሠራር ውስጥ እንደሚገኝ፣ በዚህ ሁኔታ ደግሞ ኅብረተሰቡም ሆነ መንግሥት የሚፈልጉት የእግር ኳስ ልማት እንደማይመጣ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሰውነት በሠራው ቡድን ሕዝብና መንግሥት አፍረዋል፣ ስለዚህ ይኼ ሰውዬ መኖር የለበትም ብሎ የደመደመ የለም፡፡ ይልቁንም በተጀመረው መስመር ለመቀጠል በመተጋገዝ መሥራት ቢቻል ወደተሻለ ደረጃ መሸጋገር እንደሚቻል ነው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር

Continue Reading
18 Comments

18 Comments

 1. Anonymous

  February 13, 2014 at 6:41 pm

  sewnet is arrogant ……..always his interview full of contradict idea cos he has not enough knowledge what is his responsibility and duty……..

 2. Anonymous

  February 12, 2014 at 2:44 pm

  He did good,But we need change.Give him a hero good bye

 3. Desalegn belay

  February 12, 2014 at 9:24 am

  thank you Gashe Sewenet
  he absolutely changed the team to be great but bad news heard us behind this change .he was full confidential and he was also so chance full .and after this we never expect the next coach more than sewnet
  Long live to sewnet bishaw

 4. Anonymous

  February 12, 2014 at 6:16 am

  sewunet will be the next coch

 5. abubekr

  February 11, 2014 at 9:26 am

  gash sewunet tilik tilik tilik tilik tilik sew kibir yigebachewal egr kuwas ezih dereja endiders yaderegu tilik sew

 6. Berhane

  February 11, 2014 at 9:22 am

  This is the wright time, what i expect & should be. Because even if the team was good in the past (African $ World), it would have been OK & get better result had good players like Fikru Tefera had been selected with out considering the player with u.

 7. zuta

  February 10, 2014 at 8:24 pm

  hodam federation…. sewnet bisha sinager endashaw lemanem ged yelew, anbesa new sewnet, gena leminew yimelsuhal

 8. yeneneh

  February 10, 2014 at 4:31 pm

  THANK YOU Sewnet Beshaw

 9. Mengistie

  February 10, 2014 at 2:19 pm

  Gashe Sewnet, you did good work. For you it is a relief, rather the headache and agony for the next coach and even Ethiopian football association officials is just started because you set the limit high. So, good luck for you and your family.

 10. Anonymous

  February 10, 2014 at 12:31 pm

  Thank You Sewnet! We are proud of you and thankful for what you have done.

 11. Anonymous

  February 10, 2014 at 11:26 am

  what’s wrong with this guy …. they gave him a chance …. he did what you could …. but Walays deserve a better place now …. beweleta yemiset sira yelem …. He did a good job …. I think he gave what we don’t have …. but now we need more … this is natural …. thanks sewenet …you did great …. you took the national team further place …. now we are asking you more and you couldn’t give us ….Chaw !

 12. Gashaw Gismu

  February 10, 2014 at 11:04 am

  Ayyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyyy Ethiopia

 13. Hadis Meresa

  February 10, 2014 at 10:33 am

  sewunet bishaw ke aselitagninetu bekibir enji be endezi ayinet menged mwutat alineberbetim mikniyatu le aberachi alifo le mela alem buku techawatoch yafera new lemisale ene saladin,getaneh ,adisu,simelish ….

 14. yonatan

  February 10, 2014 at 10:17 am

  kahun behuala sele football mawerat lenakom new mashenef berkachen new yemihonew medere leba federetion hulu.

 15. silesh

  February 10, 2014 at 10:06 am

  thanks big Sewunet Bishaw

 16. koka

  February 10, 2014 at 9:31 am

  Interesting saying; I hate Said Kiar b/c he do for nothing!

 17. Anonymous

  February 10, 2014 at 8:47 am

  yamrar thankyou

 18. Anonymous

  February 10, 2014 at 8:24 am

  ደረጄ ጠገናው thank u! yehene seid bihon sentun yetetamem neger neber yemenanebew.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Articles

የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ተሳትፎ ድህረ ምልከታ

Published

on

Medal Winners

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወረቀት ደረጃ ከውድድሩ መጀመር በፊት ቡድኑ ባመዛኙ በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ወጣት አትሌቶችን ስላካተተ ቢያንስ የለመድናቸውን ሁለት ወይም ሶስት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች እንደማያሳጣን ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ ሆኖም የሜዳ ላይ ውጤቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያ በውጤታማነቷ በምትታወቅበት የአትሌቲክስ ፉክክር በአንድ የወርቅ፣ አንድ የብር፣ እና ሁለት የነሐስ በድምሩ በአራት ሜዳልያዎች ከዓለም 14ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች፡፡ ይህም ሁሌም ለአፍሪካ የበላይነት ከምንፎካከራት ኬንያ ጋር ያለን ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋ አድጎታል፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ተቀናቃኛችን እየሆነች ከመጣችው ኡጋንዳም አንሰን እንድንገኝ አድርጎናል፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ከ1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ ወዲህ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችበትም ሆኖ አልፏል፡፡

አሉታዊ ጎኖች
ቶኪዮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ውጤታማነት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በ1964 ዓ.ም. በተከታታይ ሁለተኛ የኦሊምፒክ ማራቶን ድሉን የተቀዳጀባት ከተማ ናት፡፡ እናም በቶኪዮ ከተማ በተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የሱን ክብር የሚያጎሉባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ የሆኑት ነገሮች ግን በተለይ በቡድኑ አስተዳዳሪዎች በኩል ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና ከጠበቅኩት በተቃራኒው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቶች ምርጫ አንስቶ በቡድኑ የዝግጅት ወቅት በተካረረ ውዝግብ ውስጥ ነበር የከረሙት፡፡ የኦሊምፒክ ቡድኑን የማዘጋጀት እና የመምራት የጋራ ኃላፊነት የነበረባቸው ሁለቱ አካላት ይባስ ብለው ውዝግቡን ቶኪዮ ድረስ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሁለቱን አካላት በማቀራረብ በትልቁ ውድድር ላይ ያለንን ተሳትፎ እንከን አልባ ማድግ የሚጠበቅባቸውም ተመልካች ከመሆን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። የውዝግቡ አሉታዊ ትሩፋት በአትሌቶች ስነልቦና እና በአጠቃላይ የቡድኑ ውጤት ላይ የበኩሉን ተፅዕኖ ሳያሳርፍ እንዳላለፈ አያጠራጥርም፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ልዑካን የመምራት ትልቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኃላፊነት የጎደላቸው ነበሩ። የስፖርቱ አስተዳደሪዎች ትላልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በአትሌቶች ምርጫ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እንዲያቆሙልን እመኝ ነበር። ጭራሽ እራሳቸው ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ በመሮጫ መም ወይም በጎዳና ላይ በሚደረጉ ውድድሮች መሸነፍን በስፖርቱ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያሉ የነበሩ እና ወደፊትም የሚኖሩ ነገሮች ስለሆኑ በፀጋ መቀበል ይቻላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የስነልቦና ጥንካሬን ሊፈጥሩላቸው የሚገቡ ኃላፊዎች የእርስ በርስ ሽኩቻ ተቃራኒውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳርፍ ማየት ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ለነገሩ ከስፖርቱ እድገት ይልቅ የፖለቲካ ግዴታቸው የሚያስጨንቃቸው የስፖርት አመራሮች በበዙባት ሀገር ስፖርቱ እንዲህ የማንም መጫወቻ ሲሆን ማየት አዲስ ነገር አይደለም፡፡  

የስፖርት አመራሮች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ትኩረታቸውን ስፖርቱን በማስፋፋቱ እና ማሳደጉ ላይ አድርገው የሚሰሩ ስለስፖርቱም በቂ እውቀት እና ፍቅሩ ያላቸው ቢሆኑ መልካም ነው፡፡ ለቦታው በሚመጥን እና ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት በሚችል የስፖርት አመራር የሚመራ የስፖርት ተቋምን መገንባት በተመሳሳይ ሰዓት የሀገር ግንባታን የሚደግፉ ሶስት ነገሮችን ስኬታማ ያደርጋል፡፡ በስፖርት ጤናውን የሚጠብቅ ማሕበረሰብ በመፍጠር በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ እና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይም የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በቶኪዮ ላይ የተመለከትናቸው የሀገርን ክብር ዝቅ ያደረጉ ግዴለሽነቶች ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊታዩና አጥፊዎቹ ሊጠየቁበት ይገባል፡፡ በመጪዎቹ ዓመታት በሚጠብቁን ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም የቶኪዮ ኦሊምፒኩን አይነት ሀፍረት እንዳይገጥመን ከወዲሁ ለችግሮቹ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡

ባለፉት ዓመታት ኦሊምፒክ በመጣ ቁጥር በልዑካን ቡድኑ ውስጥ እየተካተቱ በሕዝብ ገንዘብ የሚዝናኑት የኦሊምፒክ ቱሪስቶች ጉዳይ ዘንድሮም ያልተቀረፈ ችግር ሆኖ ተስተውሏል፡፡ ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ተጠባባቂ አትሌቶችን ይዞ መጓዝ ይጠይቅ በነበረው ውድድር ላይ አትሌቶቹን ትቶ ምንም የማይሰሩ ሰዎችን ይዞ መሄድ ትልቅ ቀልድ ነው፡፡  

ከሜዳ ውጭ የነበረው ውዝግብ ዋነኛ የትኩረት ማዕከል የነበረ መሆኑ በሜዳ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች ሊያስረሳንም አይገባም፡፡ ስድስት የጎዳና ላይ ተወዳደሪዎቻችን እና አንድ የመም ተወዳዳሪ ውድድራቸውን ማቋረጣቸው በቶኪዮ ከታዩት ደካማ ጎኖቻችን መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ችግሩ በዚህ ምክንያት ነው የተከሰተው ብሎ ለይቶ ለመናገር ባይቻልም ብዙ ግዜ ሲፈትነን ለሚስተዋለው የሞቃታማ ቦታ ውድድር የምናደርጋቸው ዝግጅቶችን መለስ ብሎ መመልከትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ የተጎዳች አትሌትን ወደውድድር እንድትገባ ማድረግ እና በሁለት ደቂቃ ውስጥ ለማቋረጥ መገደዷም የአትሌቶች የጤና ክትትል ላይ ክፍተት እንዳለ የጠቆመን ክስተት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ወደውድድር ስፍራው ካቀናበት ግዜ ጀምሮ በቶኪዮ ምንም አይነት ቡድኑን የተመለከቱ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ወይም ፕሬስ ሪሊዞች አልነበሩም፡፡ ይህም እንደተለመደው የሕብረተሰቡን እና የመገናኛ ብዙሀንን ስለቡድኑ ቀጥተኛ መረጃ የማግኘት መብት የገደበ ነበር፡፡ ጋዜጠኞችም ሚዛናዊ ሆኖ ከመዘገብ ይልቅ ጎራ ለይተው ቃላት መወራወራቸው የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የነፈገ ነው፡፡ 

አዎንታዊ ጎኖች
ሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10,000 ሜትር ወርቅ፣ ለሜቻ ግርማ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ብር፣ ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5000 ሜትር ነሐስ፣ እና ለተሰንበት ግደይ በሴቶች 10,000 ሜትር ነሐስ ማስመዝገብ መቻላቸው የሚደነቅ ስኬት ነው፡፡

የመጪው ትውልድ አካል የሆኑት ተስፈኞቹ መቅደስ አበበ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ጌትነት ዋለን ጨምሮ አምስት አትሌቶች ለሜዳሊያ የቀረበ የአራተኛነት ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ መቻላቸውም መልካም ነው፡፡ በተለይ ወጣቶቹ ያስመዘገቡት ውጤት በመጪዎቹ ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ ካገኙ የምንጓጓለትን ድል ሊያስገኙልን እንደሚችሉ ያመላከተን ነው፡፡

የሀብታም አለሙ በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ በሴቶች 800 ሜትር ለመጀመሪያ ግዜ ለፍፃሜ ተወዳዳሪነት መብቃት ምንም እንኳ በፍፃሜው የሜዳልያ ድል ባይቀናትም በአዎንታዊ ጎን ሊጠቀስ የሚችል ስኬት ነው፡፡

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች በሚሰጥ ነጥብ ድምር መሰረት በወጣው የነጥብ (ፕሌስመንት) ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በ64 ነጥብ ዘጠነኛ ሆነን ማጠናቀቃችንም እሰየው የሚያስብል ነው፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ አጠናቀው ነጥብ ያስገኙ እና የዲፕሎማ ተሸላሚ የሆኑት አትሌቶች፡-
4ኛ – ፍሬወይኒ ሀይሉ – በሴቶች 1500 ሜትር
4ኛ – መቅደስ አበበ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል
4ኛ – ሮዛ ደረጀ – በሴቶች ማራቶን
4ኛ – በሪሁ አረጋዊ – በወንዶች 10,000 ሜትር
4ኛ – ጌትነት ዋለ – በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል
5ኛ – እጅጋየሁ ታዬ – በሴቶች 5000 ሜትር
6ኛ – ሀብታም አለሙ – በሴቶች 800 ሜትር
6ኛ – ሰንበሬ ተፈሪ – በሴቶች 5000 ሜትር
8ኛ – ዮሚፍ ቀጄልቻ – በወንዶች 10,000 ሜትር
8ኛ – ዘርፌ ወንድማገኝ – በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል

 • የአትሌቲክስ የነጥብ ደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ባሉት ደረጃዎች ውስጥ የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በሚያስመዘግቡት ነጥብ ድምር መሰረት የሚወጣ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡም ለአንደኛ ደረጃ 8 ነጥብ፣ ለሁለተኛ ደረጃ 7 ነጥብ፣ ለሶስተኛ ደረጃ 6 ነጥብ፣ ለአራተኛ ደረጃ 5 ነጥብ፣ ለአምስተኛ ደረጃ 4 ነጥብ፣ ለስድስተኛ ደረጃ 3 ነጥብ፣ ለሰባተኛ ደረጃ 2 ነጥብ፣ እና ለስምንተኛ ደረጃ 1 ነጥብ ነው።

ከፊታችን ምን  እየጠበቀን ነው? ምንስ እናድርግ?
ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ወረርሺኝ ምክንያት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሌላ ግዜ እንዲተላለፉ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ቀጣዮቹ አራት ዓመታት በተከታታይ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚካሄዱባቸው ይሆናሉ፡፡ በ2022 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2023 የዓለም ሻምፒዮና፣ በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፣ እና በ2025 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ይኖራሉ፡፡ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 8 – 17/2014 በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጆች ሙሉ የውድድሩን ፕሮግራም፣ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ የዓለም ሻምፒዮናውን ውድድር በኃላፊነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ለዛ ውድድር ተሳትፎ የሚጠበቅበትን አቅዶ መንቀሳቀስ ይኖበርታል፡፡

ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጭቅጭቆችን ለማስቀረት ከወዲሁ ሁሉም አትሌቶች አውቀውት በውስጡ የሚያልፉበትን ገዢ የሆነ የመምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ቀዳሚው ተግባር መሆን አለበት፡፡ የመምረጫ መስፈርት ሁልግዜም በግላዊ ምልከታ እና ፍላጎቶች ላይ በሚመሰረት ምክንያት አነጋጋሪ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ቢሆንም ባለድርሻ አካላቱን በሙሉ ባሳተፈ መልኩ ውይይት ተደርጎበት ቢወጣ ሁሉንም ገዢ እና ከጭቅጭቅ የፀዳ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተከሰቱት ሁኔታዎች አንፃር የሌሎች ሀገሮችንም ተሞክሮዎች በመዳሰስ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትልልቅ ውድድሮች በመጡ ቁጥር በተደጋጋሚ እንደታዘብነው አንዳንድ አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ለመካተት የሚያደርጉትን ተገቢ ያልሆነ ሙከራም ማቆም አለባቸው፡፡ ከፋም ለማም ስፖርቱን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሚያወጣቸውን መስፈርቶች ማክበርና በዛ ውስጥ ተመራጭ ለመሆን መሞከር ግድ እንደሚላቸውም መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ማኔጀሮች እና አሰልጣኞች በተለይ በማራቶን የራሳቸውን አትሌት ለማስመረጥ የሚያደርጓቸው አላስፈላጊ ግፊቶችም ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ለውድድሮች የምናደርጋቸውን ዝግጅቶች ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከውድድሮች በኋላ መገምገም እና መታረም ያለባቸው ነገሮች ካሉ ማረም፡፡ ከፍተኛ ሙቀት በነበረባቸው በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ሶስቱም የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በሞስኮ 2013 የዓለም ሻምፒዮና ሁለቱ የሴቶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን፣ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ አምስት የማራቶን (ሶስቱም ወንዶች እና ሁለት ሴቶች) ተወዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የሴቶች እርምጃ ተወዳዳሪያችን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ በጎዳና ላይ ውድድሮች ከባድ ሙቀት ለሚኖርባቸው ቦታዎች እንዴት መዘጋጀት አለብን የሚለው ጉዳይም በደንብ ሊታይ የሚገባው ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ የመም (ትራክ) ተወዳዳሪ አትሌቶቻችን የውድድር ዓመቱ ሲጀምር ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩን እና ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ አቋማቸው እየወረደ ይመጣል፡፡ አሰልጣኞቻቸው ለእነዚህ አይነቶቹ አትሌቶች ወደትልቅ ውድድር ሲቃረቡ ብቃታቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ የሚረዳቸውን የልምምድ ፕሮግራም ቢያዘጋጁላቸው መልካም ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች ላይ በተለይ በወንዶች አሁንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፎካከሩ አትሌቶችን ለማፍራት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል፡፡

Continue Reading

Articles

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች የመጀመሪያ ሁለት ቀናት

Published

on

በሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በቶኪዮ ኦሊምፒክ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የኢትዮጵያ አትሌቶች የተሳተፉባቸው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል፣ 800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፣ እንዲሁም የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያዎች ሌላኛዎቹ የኢትዮጵያውያን የትኩረት ማዕከል የነበሩ ውድድሮች ናቸው፡፡ ቀጣዩ ዘገባ የኢትዮጵያውያኑን የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ እና ውጤቶች አንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ይዟል፡፡

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል

በአትሌቲክስ ውድድሩ የመክፈቻ ቀን (ዓርብ ሐምሌ 23/2013) ጠዋት ላይ በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ከምድብ አንድ ለሜቻ ግርማ (8፡09.83) በአንደኛነት፣ ከምድብ ሁለት ጌትነት ዋለ (8፡12.55) በሁለተኛነት ለፍፃሜው ሲያልፉ በምድብ ሶስት የተወዳደረው ታደሰ ታከለ (8፡24.69) ስምንተኛ ወጥቶ ለፍፃሜው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ለሜቻ ጃፓናዊው ሚዩራ ዩጂን እና ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪይገንን በማስከተል ከምድቡ ያሸነፈበት 8:09.83 በኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የተመዘገበ የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኗል፡፡ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ የሜዳልያ ፉክክር በዋናነት በኬንያውኑ ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት፣ በኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ እንዲሁም በሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በ1980ው የሞስኮ ኦሊምፒክ በሻምበል እሸቱ ቱራ አማካይነት ካስመዘገበችው የነሐስ ሜልያ ድል ወዲህ በርቀቱ በወንዶች ምንም አይነት የኦሊምፒክ ሜዳልያ ድል የላትም፡፡ ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታዩ የመጡ መሻሻሎች እና በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበው የብር ሜዳልያ ድል በቶኪዮም ሌላ ሜዳልያን ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳን ሆኗል፡፡ ዘግይቶ የተሰላፊ አትሌቶች ለውጥ ከተደረገባቸው ርቀቶች አንዱ በሆነው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል በተጠባባቂነት የተመዘገበውና በዋናነት በ5000 ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቅ የነበረው ጌትነት ዋለ ወደመጀመሪያ ተሰላፊነት የመጣ ሲሆን ኃይለማሪም አማረ በመጨረሻ ሰዓት በለሜቻ ግርማ መተካቱም አነጋጋሪ የሆነ ሌላኛው ለውጥ ነው፡፡ ጌትነት በ3000 ሜትር መሰናክልም ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌት ሲሆን በዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በፍፃሜው ውድድር በ2019 የርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን ጌትነት ዋለ እና በወቅቱ የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊስት ለሜቻ ግርማ የሚወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በቶኪዮ የኬንያውያኑን የበላይነት ለመግታትና አዲስ የስኬት ታሪክ ለማፃፍ እንደሚበቃ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡                     

በ1984 በሎስ አንጀለስ ከተከናወነው የኦሊምፒክ ውድድር አንስቶ በተከታታይ በዘጠኝ የኦሊምፒክ ውድድሮች ወይም ላለፉት 36 ዓመታት የኦሊምፒክ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳልያ ድል በኬንያውያን ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ በዓለም ሻምፒዮናም ተመሳሳይ የበላይነት ያላቸው ኬንያውያን ከ17 የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች በ14ቱ የወርቅ ሜዳልያው አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ከኢትዮጵያውያን እና ከሞሮኮ አትሌቶች የገጠማቸው ተግዳሮት ለመሸነፍ እጅግ አቅርቧቸው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በአንድ ማይክሮ ሰከንድ ልዩነት አሸናፊነታቸውን ባረጋገጡበት በዶሀው ውድድር የተፈታተኗቸው ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ እና ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮው ፍፃሜ ለሌላ ብርቱ ፉክክር እየጠበቋቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት የዓለም ሻምፒዮናዎች በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያን ያገኘው ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካሊ በቶኪዮ ከሚወዳደሩት በሙሉ የላቀና 7፡58.15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ነው፡፡

ኬንያ በቶኪዮ ያለፈው ውድድር ሻምፒዮንነቱን ክብር የሚያስጠብቅላትን አትሌት ይዛ መቅረብ ሳትችል ቀርታለች፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በሪዮ የኦሊምፒክ እንዲሁም ከሁለት ዓመት በፊት በዶሀ የዓለም ሻምፒዮን የሆነው ኮንሰስለስ ኪፕሩቶ ባለፈው ወር በኬንያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ውድድሩን ባለማጠናቀቁ የኦሊምፒክ ሻምፒዮንነት ክብሩን ለማስጠበቅ በቶኪዮ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አሁን የረጅም ግዜ የበላይነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ በ2019ኙ የዶሀ የዓለም ሻምፒዮና ላይ በቅደም ተከተል ስድስተኛ እና ሰባተኛ ሆነው ባጠናቀቁት ቤንጃሚን ኪገን እና አብራሀም ኪቢዎት ላይ ወድቋል፡፡  

የሴቶች 800 ሜትር

ከአትሌቲክሱ የጀመሪያ ቀን የጠዋት መርሀግብሮች አንዱ በነበረው የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሶስት በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ2 ደቂቃ ከ01.20 ሰከንድ ሁለተኛ የወጣችው ሀብታም አለሙ ለግማሽ ፍፃሜው ያለፈች ሲሆን በሁለተኛው ቀን ምሽት ላይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይም በአሜሪካዊቷ አቲንግ ሙ ተቀድማ በ1:58.40 ሁለተኛ በመሆን በኦሊምፒክ የውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በርቀቱ ለፍፃሜ ውድድር የበቃች ኢትዮጵያዊት ሆናለች፡፡ ሀብታም ከውድድሩ በኋላ በቶኪዮ ለሚገኘው ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው በሰጠችው አጭር ቃል ‹‹ውድድሩ ትንሽ ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለሀገሬ ስል ያለኝን አቅም ሁሉ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም በመጨረሻም አሪፍ ውጤት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ለኦሊምፒክ የፍፃሜ ውድድር ሳልፍ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ከኢትዮጵያ ለፍፃሜ የደረሰ ያለ አይመስለኝም እና አሁንም መጨረሻዬን ያሳምርልኝ ነው የምለው›› ብላለች፡፡  

በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ በምድብ አራት በ2.01.98 አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ነፃነት ደስታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መቀላቀል ሳትችል ስትቀር በጀማሪዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሟ ተካቶ በምድብ አንድ እንደምትሮጥ ስትጠበቅ የነበረችው ወርቅውሀ ጌታቸው ግልፅ ባልተደረገ ምክንያት ውድድሩን ሳትጀምር ቀርታለች፡፡

የወንዶ 800 ሜትር

የወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊው መለሰ ንብረት ከምድብ ሶስት በ1:47.80 ሰባተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በመሐመድ አማን ስኬቶች በመነቃቃት ላይ የነበረው የወንዶች 800 ሜትር ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ሶስት ሰዓት የሚያሟሉ ተወካይ አትሌቶችን ለማግኘት እየተቸገረችበት የምትገኝ ርቀት እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ሚኒማ ማሟላት የቻለ አንድ አትሌት ብቻ ይዘን የቀረብንበት የቶኪዮ ኦሊምፒክም ይህ ችግር እንዳልተቀረፈ የታየበት ሌላኛው አጋጣሚ ሆኗል፡፡  

የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ

በአትሌቲክሱ የመጀመሪያ ቀን ሐምሌ 23/2013 ምሽት ላይ በተደረት የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ ለሚደረገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ ሰንበሬ ተፈሪ (14፡48.31) እና እጅጋየሁ ታዬ (14፡48.52) የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሳን (14፡47.89) እና ኬንያዊቷ አግነስ (14፡48.01) ቲሮፕን ተከትለው በቅደም ተከተል ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው ሲያልፉ ከምድብ ሁለት ጉዳፍ ፀጋዬ (14፡55.74) ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ (14፡55.77) አስከትላ በአንደኛነት አልፋለች፡፡


ሐምሌ 26/2013 ምሽት ላይ በሚደረገው የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ የሚፎካከሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

በሄንግሎ በተከናወነው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ምርጫ ውድድር ላይ ባስመዘገበችው የራሷ ምርጥ 14:13.32 የርቀቱ የወቅቱ ፈጣን አትሌት ሆና ወደ ቶኪዮ ያቀናችው ጉዳፍ ለወርቅ ሜዳልያ ድል ከሚጠበቁት መካከል ናት፡፡ በሄንግሎው ውድድር ላይ ጉዳፍን በመከተል በቅደም ተከተል 14:14.09 እና 14፡15.24 በሆነ ሰዓት የጨረሱት እጅጋየሁ እና ሰንበሬም በዓለም የምንግዜም ምርጥ ዝርዝር ውስጥ የስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ለመያዝ የበቁ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው፡፡ የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 5000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ሶስቱን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከዓለም የምንግዜም ምርጥ አስር የርቀቱ ሯጮች አምስቱን ያካተተ ነው፡፡ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ ከምንግዜም ምርጥ አስሮቹ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆኑ በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሳንም የቶኪዮውን የፍፃሜ ፉክክር በጉጉት እንዲጠበቅ የምታደርግ ብርቱ አትሌት ናት፡፡

Continue Reading

Articles

ሰለሞን ባረጋ ለአስራ ሶስት ዓመት የራቀንን የወንዶች 10,000 ሜትር ድል በቶኪዮ ወደ ኢትዮጵያ መልሶታል

Published

on

218076583_1010892909482678_1235421043554241523_n

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአትሌቲክስ ውድድር በተጀመረ በሁለተኛው ቀን በወንዶች አስር ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያንን እጅግ ያስደስተው ድል በወጣቱ ሰለሞን ባረጋ አማካይነት ተመዝግቧል፡፡   
በ1980 ሞስኮ ላይ ምሩፅ ይፍጠር በርቀቱ ለመጀመሪያ ግዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ካስገኘ በኋላ ከተደረጉት አስር የኦሊምፒክ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ኢትዮጵያ አምስቱን በበላይነት ለመጨረስ ችላለች፡፡ የርቀቱ ንጉሶች ሀይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ከ1992 እስከ 2008 ዓ.ም. በአራት ተከታታይ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ በማሸነፍ የርቀቱ የወርቅ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ እንዲመስለን አድርገውንም ነበር፡፡ ከ2008ቱ የቤይጂንግ ኦሊምፒክ የቀነኒሳ በቀለ ድል በኋላ በተከሰተው የሞ ፋራህ የበላይነት ምክንያት ተመሳሳዩን ድል በቶኪዮ ለማየት 13 ዓመታትን መጠበቅ ግድ ብሎናል፡፡ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በጉጉት ስንጠብቀው የቆየነውን የ10 ሺህ ሜትር የኦሊምፒክ ድል በመጨረሻም ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ አጎናፅፎናል፡፡ የሰለሞን የቶኪዮ የወርቅ ሜዳልያ ድል ኢትዮጵያ ካለፉት አስራ አንድ ኦሊምፒኮች በርቀቱ ለስድስተኛ ግዜ የበላይ ሆና እንድትጨርስ ያስቻለም ነው፡፡ ድሉ በቶኪዮ የአትሌቲኪስ ውድድሮች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ድል ሆኖም ተመዝግቧል፡፡ ሰለሞን ባረጋ በ2018 የበርሚንግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር እና በ2019 የዶሀ ዓለም ሻምፒዮና ላይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ካገኘ በኋላ በመጀመሪያ የኦሊምፒክ ተሳትፎው ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ድል ለማሳካት በቅቷል፡፡

‹‹የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት››
ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድል በኋላ

ሰለሞን ባረጋ ከቶኪዮው ድሉ በኋላ በስፍራው ከሚገኘው የስራ ባልደረባችን አብይ ወንድይፍራው ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ብሏል ‹‹ረጅም ርቀት የእኛ ስፖርት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሆኖም በኦሊምፒክ ውድድር ላይ ወርቅ ሜዳልያ ከወሰድን ብዙ ግዜ አልፎናል፡፡ ይህን ነገር ለመጨረሻ ግዜ ያሳካውም ቀነኒሳ ነበረ፡፡ ዛሬ በቶኪዮ ድሉን በማሳካቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በተለይ ለእኛ ከቶኪዮ ጋር አበበ ቢቂላን የምናስታውስበት ድል ስለሆነ ያንን በማሳካቴም በጣም ተደስቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ከኡጋንዳ የዓለም ሪኮርድ የሰበረው ቼፕቴጌይ እና የዓመቱን ፈጣን ሰዓት የሮጠው ኪፕሊሞ ነበሩ፡፡ እናም ውድድሩ በጣም ይፈጥናል ብዬ ነበር የጠበቅኩት ግን አልተሮጠም፡፡ ውድድሩን የጨረስነውም 27 ቤት ነው፡፡ የ200 ሜትር እና 400 ሜትር አጫጨር የፍጥነት ሩጫ ልምምዶችን ስሰራ ስለነበረ ሁለት ዙር ሲቀር ውድድሩን እንደማሸንፍ ለራሴ ነገርኩት፡፡ ኡጋንዳውያኑ አትሌቶች ዛሬ ብዙም አልታገሉም፡፡ አብዛኛውን ሰዓት ከኋላ ነው የቆዩት እና እንደዚህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ እነርሱን ካሜራ ላይም እያየኋቸው ስለነበር ስለነሱ ብዙም አልተጨነቅኩም እንደውም ከእነሱ ይልቅ የእኛን ልጆች ነበረ ይወጣሉ ብዬ የጠበቅኩት፡፡ በውድድሩ መሀል ተጠባቂ የሆኑት ኡጋንዳውያን ወደኋላ ቀርተው ሶስተኛው የቡድን አጋራቸው ወደፊት ወጥቶ በሰፊ ልዩነት ሲመራ እኛ እነሱን ስንጠብቅ እሱ አዘናግቶ እንዳያሸንፍ ልዩነቱን ለማጥበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ምናልባት እነሱ እኛን ሲጠብቁ አንተ ሂድ ያሉት ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በእንደዚህ አይነቱ ነገር ዳይመንድ ሊግ ላይ ስለተሸወድኩኝ ያንን እንዳይደግሙ ብዬ ነበረ ልዩነቱን ለማጥበብ የሞከርኩት፡፡ የአሰልጣኜንም ምክር እየሰማሁ ስለነበረ የምሮጠው እና ወደኋላ ተመለስ እያለኝ ስለነበር ወደኋላ ተመልሻለሁ፡፡ የእነርሱ እስትራቴጂ እሱን ወደፊት እንዲወጣ አድርገው እኛን ለማድከም ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ስንነጋገር ወደፊት ጠጋ በል እያልኩት ነበረ፡፡ ከበሪሁን ጋር ልምምድም አብረን ነበረ የምንሰራው፡፡ እኔ እንደውም ከአንድ እስከ ሶስት እንወጣለን ብዬ ነበር የጠበቅኩት አጋጣሚ ሆኖ አልተሳካም ነገር ግን ወርቁን ወደኢትዮጵያ በመመለሳችን በጣም ደስተኛ ነን፡፡›› ብሏል፡፡

Continue Reading

Trending